Monday, December 1, 2014
ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ለተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ ትንታግ የሆኑትን ወጣት ፖለቲከኞች በሽብር ወንጀል ተካፍለዋል፣ ድርጊቱን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ ህዝብን ለአመጽ ቀስቅሰዋል በሚል የፈጠራ ክስ አጎሮ ስቃይ እየፈጸመባቸው ሲሆን የካንጋሮው ፍርድ ቤት አራቱ ወጣት ፓለቲከኞችን እና በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት ሌሎች 6 ተከሳሾች ለቀረበባቸው የፈጠራ ክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አገዛዙ በወጣት ፖለቲከኞች ላይ ያቀረበውን የፈጠራ ክስ እያወገዙ መቀጠላቸው ታውቋል። ወጣት ፖለቲከኞቹን ጨምሮ በአገዛዙ የፈጠራ ክስ ሰለባ ሆነው በእስር እየተሰቃዩ የሚገኙትን የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አገዛዙ በአስቸኳይ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የበይነ መረብ ዘመቻ መከፈቱም የታወቀ ሲሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ዘመቻውን በመደገፍ ፋሽስታዊው አገዛዝ ሁሉንም የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታ አበክረው እየጠየቁ እንደሚገኙ ዘጋቢያች አመልክቷል።በሌላ ዜና የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ እያደረሰባቸው ያለው ወከባ፤ አፈናና እስር ትግሉ እንደማይቆም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አስታወቀ። “ነጻነታችን በእጃችን” ነው የሚለው ትብብሩ፣ ፋሺስታዊው አገዛዝ እየወሰዳቸው ባሉት እርምጃዎች ፈጽሞ ወደኋላ እንደማይል በማሳሰብ እቅዱን በህጋዊ መንገድ ለማስቀጠል እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።በመጨረሻም አገዛዙ ከአፈና ድርጊቱ እንዲገታና ለቀረበው ህጋዊ የዕውቅና ጥያቄ በአስቸኳይ መልስ እንዲሰጥ የጠየቀው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግሉ አላማ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሆኑን በማመልከት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለቀጣዩ ትግል የሚቀርበውን ጥሪ በንቃት እንዲከታተሉና ከፓርቲዎች ጎን እንዲቆሙ፣ ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ፓርቲዎችም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment