Thursday, December 4, 2014

የእንግሊዝ ኤምባሲ ተወካይ በሰሜን ጎንደር ዞን ከአንድነት የዞን ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

ፍኖተ ነፃነት
የሰሜን ጎንደር ዞን የአንድነት ፓርቲ ህዳር 23 ቀን 2007 ዓ.ም ከእግሊዝ ኤምባሲ ተወካይ ጋር ፓርቲው በአካባቢው በሚያደርገው እንቅስቃሴና በመንግስት እየተወሰደ ባለው ህገ ወጥ እርምጃ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አቶ አለላቸው አታለል የሰሜን ጎንደር ዞን አንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ከኤምባሲው ተወካይ ጋር ባደረጉት ውይይት በፓርቲው በዞኑ እያደረገ ስላለው ጠንካራ እንቅስቃሴ ማስረዳታቸው ታውቋል፡፡ ሰብሳቢው አክለው እንዳስረዱት መንግስት አንድነት ፓርቲ በአካባቢው ጠንካራ መዋቅር መዘርጋቱና በህዝብ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ስላሰጋው በፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ የሚያደረገው እስር እንግልት፣ አፈና እና እስር የከፋ ነው ብለዋል፡፡

በሰሜን ጎንደር የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሌለ፣ በአጠቃላይ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎችም ፊት አውራሪነት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን በማሰር ከሽብር ጋር እያገናኙ ህብረተሰቡን በማሸማቀቅ ፓርቲው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመግታት እየሰሩ እንደሆነ በሰፊው ለኤምባሲው ተወካይ ማብራራታቸውን ከዞኑ ለፍኖተ ነፃነት ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመለከተ፡፡


No comments:

Post a Comment