(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 26/2010) የደቡብ ሱዳን መንግስት የፕሬዝዳንት ሳልቫኪርን የስልጣን ዘመን በ3 አመታት ለማራዘም እቅድ ማጣቱ ተሰማ።
የሳልቫኪርን ስልጣን እስከ 2021 እንዲቆይ ያደርገዋል የተባለው ይህ እቅድ ከወዲሁ ከተቃዋሚዎች ዘንድ ህገ መንግስታዊ አይደለም በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል።
እንደ ሀገር ራሷን ከቻለች ትንሽ እድሜን ያስቆጠረችው ደቡብ ሱዳን በተቃራኒ አንጃዎች የተነሳ የርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከገባች ቆይታለች።
ይህንን የእርስ በርስ ግጭት ለማስቆምም በተደጋጋሚ የሚደረጉ ስምምነቶች ከዳር መድረስ አቅቷቸው መሃል ላይ ሲቀሩ ባየት የተለመደ ሆኗል።
ከትላንቱ ልምድ በመነሳት በቀጣይ ምን እንደሚከሰት ባይታወቀም ሁለቱ ባላንጣዎች በተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ከ3 ቀናት በፊት ከምምነት መድረሳቸውን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።
ለብዙ ሺ ዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል የተባለውን ይህንን የርስበርስ ግጭት አቁመው ወደሰላሙ መንገድ እንዲመጡ የሰላም ስምምነቱንም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲፈርሙ የተባበሩት መንግስታት ማስጠንቀቂያ ያስተላለፈው በቅርቡ ነበር።
ሁለቱም ወገኖች ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን የጦር መሳሪያን ጨምሮ ከበድ ያለ ማዕቀብ ይጠብቃቸዋል ሲልም ማስጠንቀቂያውን አጠናክሮታል።
ያ ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ደሞ 72 ሰአታት ብቻ ቀርተውታል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ታዲያ ሁለቱ ወገኖች በተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ብቻ ከስምምነት መድረሳቸው የተሰማው።
ይህም ሳያበቃ ደሞ ዛሬ ላይ የፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የስልጣን ዘመን በሶስት አመት ሊራዘም ይገባል የሚል የማሻሻያ ሃሳብ ይዘው ብቅ ያሉት።
እንደ አፍሪካ ኒውስ ዘገባ ከሆነም ሰኞ ለፓርላማ ቀርቦ የነበረው ይህ የማሻሻያ እቅድ በዚህ ወር መጨረሻ ከውሳኔ ላይ ይደርሳል ።
ይህ የማሻሻያ ሃሳብ ደግሞ በተቀናቃኛቸው በሬክ ማቻር በኩል ህገ መንግስቱን የጣሰ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ በተቀሰቀሰ ግጭት 18 ንጽሃን ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
No comments:
Post a Comment