ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ይህን ያሉት በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ የኢትዮጵያ
እና የኤርትራ መንግስት የሰላም ማብሰሪያ መድረክ ላይ ነው።
እና የኤርትራ መንግስት የሰላም ማብሰሪያ መድረክ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሲለያዩ ግንጥል ጌጥ ናቸው፤ አንድ ሲሆኑ ግን ከራሳቸው አልፈው ለአፍሪካም ፈርጥ ይሆናሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመልክ፣ በአንድነታችን ተመሳሳይ ነን፤ ይህን አንድ የሆነ ህዝብ ማንም ሀይል ሊለያይ አይችልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ አክለውም፥ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር፣ ከቁርሾ ይልቅ ይቅርታ፣ ከመገፋፋት ይልቅ መሳሳብ፣ ስለመረጣችሁ በጣም በምወደው ህዝብ ፊት ዝቅ ብዬ ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ ብለዋል
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰላም እና የነፃነት ዋጋን ከጤና ጋር ያመሳስሉታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ፥ ሰላም ሲኖር የረከሰ ሲጠፋ ግን ዋጋ የሚያስከፍል ነው ብለዋል።
ሰላም የነፃነት ነፃነት ደግሞ የብልጽግና እናት ነች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ከሰላም እና ነፃነት ውጭ ብልፅግና ህልም ብቻ ነው ሲሉም ገልፀዋል።
ልዩነት ካወቁበት አትራፊ ነው፤ በሀሳብ መፋለምን ሳይሆን ከወንድምና ከእህት ጋር የጥፋት ጦርነት ማወጅና ለዛ ጭካኔ የተሞላበት ጀግነነት መሰለፍ ግን ከንቱ ነው ብለዋል።
ችግር ለምን ተፈጠረ ሳይሆን ምን ትምህርት አገኘን፣ እንዳይደገም ምን እንስራ ብሎ በይቅርታ ልብ ለሚበጀው፣ ለሚሻለው፣ ለሚያለማው እና ለሚያተርፈው መትጋት ይበጃል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተናግረዋል።
ይቅር መባባል ከሚቀጥል ኪሳራና ውድቀት ይታደጋል፤ ይቅር ስንባባል ኪሳራው አይዝለቅ ማለት ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
ከ100 ሚሊየን ህዝብ ክፉ የሚያስብ የለም ባይቻልም ክፉን ካልተጋራን ግን መክኖ ይቀራል ያሉት ጠቅለላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ፥ አደገኛው ነገር ክፉን ነገር ብዙዎች ሲጋሩት ነው፤ ክፉ ክፉዉን የማንጋራ ይሁን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ መደመርን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያም፥ የምንደመረው ለፍቅር እና ለይቅርታ ብቻ ይሁን፤ ለክፋት ለመግደል አንደመርም ብለዋል።
የኛ የመደመር ለሌሎች ተስፋ እንጂ ጭንቀት አይሆንም ሲሉም ተናግረዋል።
የኛ የመደመር ለሌሎች ተስፋ እንጂ ጭንቀት አይሆንም ሲሉም ተናግረዋል።
የኛ የመደመር እሳቤ ከሂሳባዊ ቀመር የላቀ ነው፤ የኛ የመደመር ስሌቶች የመጀመሪያው የጥላቻን ግንብ ማፍረስ ነው፤ እኛ ስንደመር እንደ ሂሳብ ቀመር ሁለት ሳይሆን አንድ እንሆናለን ብለዋል።
የኛ መደመር መካፈልም አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የምንካፈለው አሰብ ይሆናል ብለዋል።
No comments:
Post a Comment