(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። የእርቅ ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ የሁለቱም አባቶች የተገናኙበት የጋራ የጸሎት ስነስርአት ተካሂዶ አንደነበር ታውቋል። ከሐገር ቤት የመጡት አባቶች በውጪ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት የጸሎት ስነስርአት ላይ ሲገኙ የውጪ ሲኖዶሱ አባላት ደግሞ በሐገር ቤቱ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ተሰምቷል። ስምምነታቸው በቀጣዮቹ ቀናት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። አባቶቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋርም ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።
No comments:
Post a Comment