Wednesday, July 11, 2018

የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት በሌሉበት መሻራቸውን ተቃወሙ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱላሂድ እርሳቸው ባልተገኙበት ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓም የተደረገው የማእከላዊ ስብሰባ እና የፕሬዚዳንት ምርጫ እንደማይቀበሉትና አሁንም ክልሉን እሳቸው እንደሚመሩት አስታውቀዋል። ምክር ቤቱ አቶ ኦድሪን በድሪን ሊቀመንበር ፣ አቶ ነቢል ማሃዲን ደግሞ ምክትል ሊ/መንበር አድርጎ መርጦ ነበር። አቶ ሙራድ ከአዲስ አበባ ከተመለሱ በሁዋላ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶችና ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች ሰብስበው ክልሉን አሁንም እርሳቸው እያስተዳደሩት መሆኑንና ስልጣን አለመልቀቃቸውን ተናግረዋል። የአቶ ሙራድን ድርጊት የሰሙት አዲሱ ፕሬዚዳንትና ምክትሉ፣ አቶ ሙራድ ቅስቀሳቸውን እንዲያቆሙ ያስጠነቀቁዋቸው ሲሆን፣ ዛቸውን የፈሩት አቶ ሙራድ ዛሬ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል። በክልሉ ባለስልጣናት መካከል ያለው መከፋፈል መጨመሩን ተከትሎ አካባቢውን የብጥብጥ ቀጠና ያደርገዋል የሚል ስጋት መኖሩን ወኪላችን ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment