Thursday, July 19, 2018

የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010)በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀውን ችግር በንግግር ለመፍታት ከአዲስ አበባ የተወከሉት የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል።
ልዑካኑ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት በቤተመንግስት ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተወያይተዋል።
ከአዲስ አበባ የመጡት የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ማለዳ ዋሽንግተን ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ የሚገኙ አባቶችና ምዕመናን ከፍተኛ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በዚህ ሳምንት የሚጀመረው የእርቅ ሒደት የሩብ ክፍለ ዘመን የዘለቀውን ችግር ይፈታል በሚል ታላቅ ተስፋ የተጣለበት ሲሆን ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ወደ አሜሪካ ሲመጡ በዋሽንግተን ዲሲ ቆይታቸው ከፓትርያሪክ አቡነ መርቆሪዎስና ከሌሎች አባቶች ጋር እንደሚገኙም መረዳት ተችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አባቶቹን በቤተመግስት ባነጋገሩበት ወቅት ታዋቂ ኢትዮጵያውያንም አብረዋቸው እንደነበሩም መረዳት ተችሏል።
ከዚህ ውስጥ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ግርማ ዋቄ፣ ባለሐብቱ አቶ ሳሙኤል ታፈሰና ታዋቂው አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment