(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010) ጣሊያን 450 ስደተኞች በሲሲሊ እንዲያርፉ ፈቀደች።
ጣሊያን ውሳኔውን ያሳለፈችው ፈረንሳይ፣ፖርቹጋል፣ማልታ፣ጀርመንና ስፔን እያንዳንዳቸው 50 ስደተኞችን እንወስዳለን ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
በሲሲሊ ደሴት በፖዛሎ የወደብ ዳርቻ እንዲያርፉ የተደረጉት 57 ሕጻናትና ሴቶች ብቻ መሆናቸው ታውቋል።
በደሴቷ እንዲያርፉ የተደረጉት ስደተኞቹ በሁለት ጀልባዎች ተጭነው ሲጓዙ የነበሩና በነፍስ አድን ሰራተኞች ከሜዲትራኒያን ባህል ላይ ሕይወታቸው የተረፈ መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ አዲሱ የጣሊያን አስተዳደር ከስደተኞች ጋር በተያያዘ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ከባድ ናቸው።
No comments:
Post a Comment