( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነዋሪነታቸውን በጣሊያኗ ቶሪኖ ከተማ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን በጋራ በመሆን የመደመር ቀንን በአዳራሽ ውስጥ በማክበር ለሰላም ጥሪው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ላለፍት ሃያ ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሰላም እንዲፈታ በተሾሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድንና አጋሮቻቸውን አመስግነዋል። ለሰላሙ ጥሪ እጃቸውን በመዘርጋት ለመደመሩ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂና ፓርቲያቸውንም አድናቆት ለግሰዋል። ለቀጣይ ካለፈው በመማር ልዩነቶችን በሰላም በመፍታት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ቃል በመግባት ዝግጅቱ በሰላም ተጠናቋል።
No comments:
Post a Comment