Tuesday, June 5, 2018

በኢትዮ-ሶማሊ ክልል ከ100 በላይ ወጣቶች ታሰሩ

(ኢሳት ዜና ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ ማግስት፣ የአብዲ አሌ አገዛዝ ከ100 በላይ የሚሆኑ በጅጅጋ ዞን የሚኖሩ ወጣቶችን ይዞ አስሯል። ወጣቶቹ በእስር ቤት ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ የሚታዬውን የለውጥ እንቅስቃሴ በመስጋት የህወሃቶችን ድጋፍ ለማግኘት ታች ላይ በማለት የሚገኘው አብዲ ኢሌ፣ በህወሃት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ቃል የተገባለት ቢሆንም አሁንም አለረመጋጋት እየታዬበት ነው። የህወሃት ነባር አመራሮች የአብዲ ኢሌ አገዛዝ እንዲያበቃላቸው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ በማቅረብ ላይ ያሉትን የአገር ሽማግሌዎች ከአብዲ አሌ ጋር ለማስታረቅ ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን ተከትሎ፣ የአገር ሽማግሌዎችን አፍኖ ለመውሰድ ወይም ለማስፈራራት ሙከራ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በሶማሊ ክልል የሚተገበር ማንኛውም ፖሊሲ ህወሃት ያወጣውና ህወሃት እውቅና የሰጠው ብቻ መሆኑን ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጋር አብረው በቅርብ የሰሩና ስልጣን አንፈልግም በማለት ከአገር የተሰደዱ የቀድሞ ባለስልጣናት ይገልጻሉ። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በሶማሊ ክልል ስለሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እስካሁን የተናገሩት ነገር የለም።

No comments:

Post a Comment