(ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ በሰጠው መግለጫ ፣በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ስም- ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል አደም መሀመድ ሲ- 130 የጦር አውሮፕላንን በማበርከቱ ሂደት – አምባሳደር ሚካኤል ሬይኖር ተሳትፈዋል። ሲ-130 አውሮፕላን፣ ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ የተቀበለችውን ተልዕኮ በብቃት እንድትወጣ፣ የሰብዓዊ እርዳታ በሚያስፈልግባቸው በማናቸውም አካባቢ አቅርቦቱን በፍጥነትና በሰዓቱ ለማድረስ እና በግጭት አካባቢዎች በግጭት አካባቢዎች የሲቪሎችን ህይወት ለመታደግ እንደሚረዳት ኤምባሲው ገልጿል። “ይህ የአውሮፕላን ስጦታ በመካከላችን ያለውን ጥልቅና ጠንካራ ግንኙነት እና በዓለማቀፍ ደረጃ ገንቢ የአመራር ሚና ለመጫዎት ያለንን እምነት ያሳያል” ብለዋል-አምባሳደር ሬይኖር። ዩናይትድ ስቴትስ ትብብሯን ለማጠናከር አሁን የያዘችው ቁርጠኝነት ከእስካሁኑ በበለጠ ጠንካራ እንደሆነና በመቺዎቹ ጊዜያትም የሀገራቱ ግንኙነት ይበልጥ በሚጠነክርበት መንገድ ዙሪያ እንደሚሰሩ አምባሳደሩ ጠቅሰዋል። በሥነ ስርአቱ ላይ በአሜሪካ አየር ኃይል የአውሮፓና አፍሪካ ኃላፊና የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል አባላት ተገኝተዋል።
No comments:
Post a Comment