(ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ሜቴክ የሚሰራው ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የመልካ ሰዲ የእንፋሎት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከማጠናቀቂያ ጊዜው 2 ዓመት ቢዘገይም እስካሁን የተሰራው ከ25 በመቶ እንደማይበልጥ መረጃዎች አመለከቱ። ፕሮጀክቱን የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በዋና ተቋራጭነት እንዲሁም ግሬስ ኢንጂነሪንግ በንጹስ ተቋራጭነት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢንጂነሪን ቢሮ ደግሞ በአማካሪነት ይሰሩታል። ፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪው በመንግስት በሚሸፈን 4 ቢሊዮን 160 ሺ ብር የተጀመረ ሲሆን ፣ ሰኔ 9 ቀን 2006 ዓም ተጀምሮ፣ ሰኔ 2008 ዓም ይጠናቃል ተብሎ ታቅዶ ነበር። በተባለው ጊዜ ባለመጠናቀቁ ተጨማሪ የመጣናቂያ ጊዜ እስከ ጥር 2009 ዓም ተሰጥቷል። ከሁለት አመታት መዘግየት በሁዋላ በአሁኑ ሰዓት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸምም 27 በመቶ ብቻ ሲሆን፣ በሜቴክና በመንግስት መካከል የስራን አካሄድ በተመመለከተ መግባባት ላይ ሊደረስ አልቻለም።የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በውል ለመግለጽ እንደማይችልም መረጃዎች ያሳያሉ። ለችግሩ መፍትሄ ለመሻት የተደረገው ሙከራም በሜቴክ ባለስልጣናት መደናቀፉ ታውቛል። ከአዲስ አበባ በ270 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዞን ሶስት አሚባራ ወረዳ ላይ የእርሻና የግጦሽ መሬትን በስፋት በመውረር በግጦሽና በሰብል መሬት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረስ የሚገኘውን ፕሮስፒስ ደሊን ፕሎራ ተብሎ የሚጠራውን መጤ አረም መንጥሮ በማቃጠል የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚከናወን ፕሮጀክት ነው።
No comments:
Post a Comment