(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/የጦር ኮማንደር ትላንት ከወህኒ ተለቀቁ።
የኦብነግ የጦር አዛዥ የነበሩት አብዱከሪም ሼክ ሙሳ አምና በነሐሴ ወር በሶማሊያ ጋልካዩ ታፍነው ወደ ሞቃዲሾ ከተወሰዱ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው መሰጠታቸው ይታወሳል።
አምና በነሐሴ 2009 ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር የጦር አዛዥ ኮማንደር አብዱከሪም ሙሳ ላለፉት 11 ወራት በኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ቆይተዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 28/2017 ከሶማሊያ ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው በሶማሊያ ፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ ክርክር ማስከተሉም ይታወሳል።
15 አባላት ያሉት የሶማሊያ ፓርላማ ቡድን ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በመስከረም ወር 2009 እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም 2017 ተላልፈው መሰጠታቸውን አውግዟል።
የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኮማንደርን አብዱልከሪም ሼክ ሙሳን በተመለከተ የሶማሊያ የደህንነት ክፍል የተሳሳተ መረጃ መስጠቱንም አጋልጧል።
አብዱከሪም ሼክ ሙሳ በማዕከላዊ ሶማሊያ ጋልካዩ ከአንድ ሆቴል ውስጥ መያዛቸው ይታወሳል።
ከ11 ወራት እስራት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ትላንት በምህረት አሰናብቷቸዋል።
No comments:
Post a Comment