(ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው ከ9 ዓመታት እስር በሁዋላ በቅርብ የተፈቱት ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌና የአየር ሃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዲየር ጀኔራል አለምሸት ደግፌ፣ ወታደራዊ ማዕረጋቸው እንዲመለስላቸው መደረጉን የጠ/ሚኒስትሩ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትወተር ገጻቸው አስታውቀዋል። ሁለቱም ጅኔራሎች ማእረጋቸውን እንደያዙ የጡረታ መብታቸው እንዲከበርላቸው መደረጉንም ባለስልጣኑ ገለጸዋል። ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌን ጨምሮ ከ20 የሚበልጡ ጄኔራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች በመንግስት ግልበጣ ተወንጅለው የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ነበር።
No comments:
Post a Comment