(ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም) በሚቀጥለው ሳምንት ፓርላማው ያጸድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው የምህረት አዋጅ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ምህረት እንደሚደረግላቸው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ገልጸዋል። አዋጁ ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ቀድም ብሎ የተመራ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ እስካሁን መልስ አልሰጠበትም። ይሁን እንጅ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ አዋጁ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አርበኞች ግንቦት7 በዶ/ር አብይ አህመድ የቀረበውን የሰላም ጥሪ አወንታዊ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የንቅናቄው ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ በኢቲቪ ቀርበው ማብራሪያ ስጥተዋል። ዶ/ር ታደሰ ድርጅታቸው አርበኞች ግንቦት7፣ ከመጀመሪያውም ጀምሮ በአገር ውስጥ ገብቶ መታገል አላማው እንደነበርና አሁን በዶ/ር አብይ የተጀመሩት የለውጥ እንቅስቃሴዎች፣ ድርጅቱ ከሚታገልለት አላማ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ፣ ለተግባራዊነቱ አወንታዊ መልስ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። ዶ/ር ታደሰ ድርጅቱ ራስን የመከላከሉን እርምጃ ጥቃት እስካልተፈጸመበት ድረስ እንደሚያቆምም ገልጸዋል። ድርጅቱ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ አባል ዶ/ር ታደሰ ብሩ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንዲሰጡን አነጋግረናቸዋል፦
No comments:
Post a Comment