Tuesday, June 19, 2018

የወላይታ ህዝብ በህዝብ ላይ ለደረሰው ሞት የክልሉን መሪን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረገ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሰሞኑን በሲዳማ እና በወላይታ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዛሬ በጉታራ አዳራሽ የወላይታ ከተማ ነዋሪዎችን ባወያዩበት ወቅት ፣ ህዝቡ ግጭቱን ያስነሱት የደቡብ ክልል ባለስልጣናት ናቸው ብሎአል። ህዝቡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከስብሰባ አዳራሽ እንዲወጡ ቢጠየቁም እርሳቸው ግን ስብሰባውን እስከመጨረሻው ተካፍለዋል። የወላይታ ሶዶ ዪኒቨርስቲ የወላይትኛ ቋንቋ መምህር የሆኑት አልማዝ አንጁሎ “የጨምበላላ በአል በክልል በጀት መከበር የለበትም በማለት የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ በዞን በጀት እንዲከበር ስላደረጉ የሲዳማ ባለስልጣናት ጥርስ ነክሰዉ እያስገደሉ ነዉ” በማለት ተናግረዋል። “እኛ ወላይታዎችን እየገደሉ ያሉት ሲዳማዎች ሳይሆኑ፣ ዛሬ ከርሶ ጋር የመጡት የክልሉ ፕሬዝደንት ናቸው በማለት መምህርት አልማዝ አክለዋል። ስብሰባውን ከተከታተሉት መካከል አንዱን አነጋግረነዋል። ዶ/ር አብይ ሃዋሳ ላይ ከሲዳማ ማህበረሰብ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት ደግሞ ግጭት ያስነሱት ሃይሎች ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል ።

No comments:

Post a Comment