Tuesday, May 22, 2018

በሽንሌ ዞን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ አለመላኩን የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ

(ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በኢትዮ-ሶማሊ ክልል በሽንሌ ዞን ፣ በሃርዋ ፣ ገሚ፣ አይሎሶና ሌሎችም ቦታዎች አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ የተጎዱ ዜጎች እስካሁን ድጋፍ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለችግር ተዳርገዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤቶች መፍረሳቸውን፣ አንድ ሺ የሚሆኑ የእርሻ ማሳዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። የሶማሊ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ተጎጂዎችን በመርዳት በኩል እስካሁን የወሰደው እርምጃ ባለመኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። በሽንሌ ዞን የሚገኙ የሶማሊ ተወላጆች ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት የአብዲ ኢሌን አገዛዝ በመቃወም ሰልፍ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment