(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 16/2010) በውጭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ላለፉት 24 ዓመታት በጨለማ እስር ቤት የሚገኙት የሃይማኖት መምህር እንደስራቸው አግማሴ መኮንን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ።
ሲኖዶሱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው ከ24 ዓመት በፊት ተይዘው ጨለማ እስር ቤት ውስጥ ያለርህራሄ ታስረው የሚገኙት የሃይማኖቱ ሊቅ እንደስራቸው በህይወት መኖራቸ
ው የታወቀው በቅርቡ ነው።
እኚህ መምህር የቤተክርስቲያኒቱ ትልቅ ባለውለታ የሆኑና ያለጥፋታቸው በእስር የሚማቅቁ በመሆናቸው በአስቸኳይ ተፈተው ቤተሰቦቻቸውን እንዲቀላቀሉ ሲኖዶሱ ጥሪ አድርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉዳዩን አጢነው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡም ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው ጠይቋል።
በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራውና መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ያደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫው የቤተክርስቲያኒቱ ሊቅ እንደስራቸው አግማሴ ላለፉት 24 አመታት በወህኒ ቤት ማሳለፋቸውን አስታውቋል። በሕይወት መኖራቸው የታወቀው በቅርቡ እንደሆነም ሲኖዶሱ ገልጿል።
እኚህ የሃይማኖት አባት በአስቸኳይ እንዲፈቱም ሲኖዶሱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጥያቄ አቅርቧል።
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሚያደርጓቸውን በጎ ምግባራት እያደነቅን በሱዳንና በኬንያ ብሎም በሳውዳረቢያ ያሉ እስረኞችን ለማስፈታት ያደረጉትን እንቅስቃሴ ብናመሰግንም በራሳችን የጉድጓድ እስር ቤት ውስጥ ያለፍርድ እየተሰቃዩ ለሚገኙት ቅድሚያ መስጠት የፍትህ ፈላጊነት አንዱ መገለጫ ነው ብለን እናምናለን”ይላል የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ።
መላው ፍትህ ፈላጊ ኢትዮጵያውያንም እኚህን ታላቅ ሊቅ ለማስፈታት የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪውን አቅርቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም እኚህን ታላቅ የቤተክርስቲያን ሊቅ እንደስራቸው አግማሴን ለቤተክርስቲያኒቱ ክብር ሲሉ ቅድሚያ ሰተው እንዲፈቱ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።
ወንጀለኞቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው ጠይቋል። በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችም ዜጎች በዘራቸው ሳቢያ እየተካሄደባቸው ያለው መፈናቀልም እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶሱ አሳስቧል።
No comments:
Post a Comment