(ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የቤት ማፍረስ ዘመቻን ተከትሎ እስካሁን ከ20 ሺ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ መጠለያ የቀሩ ሲሆን፣ ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ ያደረጉ ነዋሪዎች ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ብዙዎቹ መደብደባቸውንና እስካሁን 2 ሰዎች መገደላቸውንና ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንደኛዋ ቤቷ ሲፈርስ እቃዋን ለማውጣት ስትገባ ቤቱን በላዩዋ ላይ አፍርሰው የገደሏት ሲሆን፣ አንደኛው ደግሞ በጥይት ተመትቶ መሞቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጥያቄያቸውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያቀርቡም መልስ የሚሰጣቸው አላገኙም። ጠ/ሚኒስትሩን ለማናገር ሙከራ አድርገው የሚያቀርባቸው ሰው ማጣታቸውንም ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment