(ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶክተር አብይ አህመድ በዳላሱ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ጥያቄ የቀረበው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቁጥር ዋሸ 09-620-2010 በጻፈው ደብዳቤ አማካይነት ነው።የማህበሩ አመራሮች ይህን ጥያቄ ተከትሎ ባሰባሰቡት ድምጽ 65 በመቶ ያህሉ ድምጽ ሰጭ እንዲገኙ ፍላጎቱን የገለጸ ቢሆንም፣ አንዳንድ ወሳኝ ጉዳዩችን በማጤን በራሳቸው ውሳኔ ለማሳለፍ መገደዳቸውን ገልጸዋል። ይህን ተከትሎ በሰጡት ድምጽ በተቀራራቢ ውጤት በዘንድሮው ዝግጅት መገኘት የለባቸውም የሚለው አሸናፊ ሆኗል።ማህበሩ ውሳኔውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የዶክተር አብይ አህመድን ጥያቄ በአክብሮት እንደተቀበለው ሆኖም፣ ጥያቄው የቀረበው ዝግጅቱ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ሲቀረው ከመሆኑ አኳያ በስቴዲየም ውስጥ ሊኖር የሚችለውን ጭንቅንቅ ታሳቢ በማድረግ ፣ለታዳሚው ህዝብ ደህንነት የሚፈጸመውን ክፍያ ፌዴሬሽኑ ከፍሎ ያጠናቀቀ በመሆኑ ጥያቄውን ለመቀበል እንደተቸገረ ገልጿል። አክሎም ወደፊት በሚደረጉ ዝግጅቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚጋበዙበትን መንገድ እንደሚያጤነው አስታውቋል። ዶክተር አብይ መጋበዝ አለባቸው ብለው ድምጽ የሰጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በማህበሩ ውሳኔ ላይ ተቃውሞ ሲሰነዝሩ የዋሉ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በውሳኔው ቅር ብንሰኝም በዲሞክራሲ እንደሚያምን ዜጋ የማህበሩን ውሳኔ አክብሮ ከመቀበል ውጭ ውዝግብ ውስጥ መግባት አያስፈልግም ብለዋል።
Thursday, May 31, 2018
የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት 1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሆን ወሰነ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የክልሉ ምክር ቤት ለክልሉ ፋይናንስ ክፍል በላከው ደብዳቤ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ህክምናቸውን በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ ለውጥ ሊታይ ስላልቻለ ወደ ውጭ አገር ሄደው የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ 1 ሚሊዮን ብር እንዲሰጣቸው የክልሉ መንግስት ካቢኔ በሙሉ ድምጽ መደገፉን ገልጿል። ገንዘቡ ከመጠባበቂያ በጀት በክልሉ የግዢ የስራ ሂደት አስተባባሪ በሆኑት አቶ ማቲዎስ ገለታ ስም ወጮ ተደርጎ ለርዕሰ መስተዳደሩ እንዲከፈልም ደብዳቤው ያዛል።
የአፋር ክልል ገዥ ፓርቲ አብዴፓ አዲሱን የአቶ አብይ አህመድን አስተዳደር እንዳይቀበል በህወኃት በኩል አፍራሽ ተግባራት እየተፈጸሙ ነው ሲሉ በአውሮፓ የአፋር ማህበረሰብ ተወካይ ገለጹ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ተወካዩ አቶ ገአስ አህመድ ዛሬ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ላለፉት 27 ዓመታት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅሙ ክፉኛ የደቀቀው የአፋር ህዝብ እውነተኛ ለውጥ እየጠየቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ገዥው የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ -ከህወኃት መሪዎች ጋር በመሆን የህዝብን ጥያቄ በማፈንና ጅምሩን ለውጥ በመቀልበስ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል። ሰሞኑን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተቃውሞ ሰልፍ ማደረጋቸውን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት የአብዴፓ ዋና ጸሀፊ በጉዳዩ ዙሪያም ለማነጋገር የአፋር ወጣቶችን ስብሰባ ቢጠሩም፣ ወጣቶቹ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ባልተገኙበት ሁኔታ ብቻችንን አንሰበሰብም በማለት ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን አቶ ገአስ ተናግረዋል። የወጣቶቹ የለውጥ እየጨመረና ተቃውሞው እየባሰ በመምጣቱ የህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በሆኑት በአቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይ የሚመራ ልኡክ ዛሬ መግባቱን የጠቀሱት ተወካዩ፣የጉዟቸው ዓላማ በአብዲ ኢሌ እንደሚመራው ሶህዴፓ ፓርቲ የአፋሩን አብዴፓንም በአቶ አብይ አመራር ላይ ማነሣሳት እንደሆነ የደረሷቸውን መረጃዎች ዋቢ አድርገው ገልጸዋል። እነ ጎበዛይ አብዴፓዎችን “ህወኃት ከሌለ የእናንተም ህልውና የለም” እንደሚሏቸው ያወሱት አቶ ገአስ፣ ልክ መቀሌ ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ “የተሸነፉ ሀሳቦች እያቆጠቆጡ ነው”እንዳሉ ሁሉ ፣ግንቦት 20 በአባላ ከተማ ሲከበርም የአብዴፓው አሊ አብደላ “ደርግ እየተመለሰብን ነው”ብለው ንግግር ማድረጋቸውን አመልክተዋል። ህወኃት የነ አሊ አብደላ የነፍስ አባት መሆኑን የአፋር ህዝብ ያውቃል የሚሉት አቶ ገአስ፣ ሕዝቡ፣ ያነሳው የለውጥ ጥያቄ ከዳር እስኪደርስ ድረስ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ እንዲሁም አዲሱ የአቶ አብይ አስተዳደር በአፋር አካባቢ በህወኃትና በክልሉ ገዥ ፓርቲ እየፈጸመ ያለውን ደባ እንዲታገሉት ጥሪ አቅርበዋል።
የአብዲ ኢሌ የደህንነት አባላት በዱልሚዲድ አመራር ላይ ያደረጉት የአፈና እርምጃ ከሸፈ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ትናንት ምሽት የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በመቃወም ዱል ሚዲድ እየተባለ በሚጠራው በኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች የተቋቋመውን ድርጅት ከሚመሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑትን አቶ ካድር አዳንን ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በፌደራል የደህንነት መስሪያ ቤትና በአሜሪካ ኢምባሲ አማካኝነት ሊከሽፍ ችሎአል። አቶ ካድር ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለዲያስፖራው ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ወደ አገራቸውን በቅርቡ የገቡ ናቸው። አፈናውን ለማካሄድ ከተላኩት የደህንነት አባላት መካከል የጄ/ል ገብሬ ዲላ ቀኝ እጅ የሆነው ሃሰን አህመድ የሚገኝበት ሲሆን፣ ሌሎች አፋኞች ደግሞ በማምለጣቸው ክትትል እየተደረገባቸው ነው። አብዲ ኢሌ ለአፈና ያሰማራው ሀሰን አህመድ በተለምዶ ሀሰን ገብሬ የሚባለው ግለሰብ በሱማሌዎችና በኦሮሞዎች ዘንድ ተደጋጋሚ አፈናዎችንና ግድያዎችን ከማካሄዱም ባሻገር ፣ ናይሮቢ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ ሆኖ በሰራበት ወቅትም ለበርካታ ለኦሮሞና ሶማሊ ተወላጆች ግድያና አፈና ተጠያቂ ነው። ከአፈና እቅዱ ጀርባ ጄኔራል ገብሬ እንዳለበት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ። አቶ ካድር በሰጡት መግለጫ፣ እንዲህ አይነቱ የአፈና ሙከራ በእርሳቸው ላይ እንዲያበቃ ጠይቀዋል። አፈናው እንዲጨናገፍ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበው ስለ አፈናው ሂደት ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ በመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በመወያዬታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
አቶ አንዳርጋቸው ነገ ጧት ለንደን ይገባሉ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የግንቦት 7 ዋና ጸሀፊና የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው ባለፉት አራት አመታት በእስር የቆዩት አቶ አንዳርጋቸው ትናንት ከቀትር በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለሁለት ሰዓታት የዘለቀ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ “መሰረታዊ ባሏቸው” ጉዳዮች ዙሪያ ስለደረጓቸው ውይይቶች ለጊዜው ለመገናኛ ብዙሀን መግለጽ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል። ይህን ተከትሎ ማህበራዊ ሚዲያው ዶክተር አብይና አቶ አንዳርጋቸው በፈገግታ ተሞልተውና እጅ ለእጅ ተጨባብጠው በሚታዩበት ፎቶ የተጥለቀለቀ ሲሆን፣ ክስተቱን እንደ ትልቅ የለውጥ ጅምር ምዕራፍ የወሰዱት ጥቂቶች አይደሉም። በኢትዮጵያውያኑ ከስተሰጡት አስተያየቶች መካከል፦ “የጥልና የጠላትነት መጋረጃ ተቀደደ፣ ይህን ፈጽሞ ማመን አንችልም! አምላክ የሀገራችንን ጸሎት ሰማት ማለት ነው? ሳቃችንን ያስመሽልን!ለውጡን የምር ያርግልን!”የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው። ላለፉት 27 ዓመታት ሥር ከሰደደው የጠላትና የመገዳደል ፖለቲካ አኳያ የትናንት ምሽቱን ክስተት ተአምር
የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።
(ኢሳት ዲሲ– ግንቦት 23/2010)
ምክትል ገዢው ዶክተር ዮሃንስ አያሌው በይፋ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ታውቋል።
በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ውስጥ የአፍሪካ ሃላፊ አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት መጠየቃቸውም ተሰምቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የሃገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚበቃ መሆኑም ተመልክቷል።
የብሄራዊ ባንክ ገዢዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲያገግም ለማድረግ የገንዘብ አቅርቦትን በተመለከተ የተዛባ ሪፖርት እንዲወጣ ምክንያት እንደሆኑም ተገልጿል።
እንዲሁም ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አልቻሉም በሚል የባንኩ ገዢዎች ከሃላፊነት እንዲነሱ የተወሰነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንበረ ስልጣኑን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ነው።
ምክትል ገዢው ዶክተር ዮሃንስ አያሌው በዚህ ሳምንት በይፋ ከስልጣን ተነስተው ወደ ሌላ ስፍራ ሲመደቡ፣ዋናው ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በተመሳሳይ እንዲነሱ የተወሰነ ቢሆንም፣ተስፋ የተጣለባቸው ዕጩ ጥያቄውን ባለመቀበላቸው ሰው እስኪተካ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ለጥቂት ሳምንታት በስልጣን ላይ ሊቆዩ እንደሚችሉ መረዳት ተችሏል።
የሀና ማርያም ነዋሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 23/2010) በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ሀና ማርያም በተባለ አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ2ሺህ በላይ አባወራዎች በቤተመንግስት አቤቱታ ለማቅረብ ሄደው በፖሊስ መደብደባቸው ተገለጸ።
ትላንት ማምሻውን ወደ ቤተመንግስት ያመሩት የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቤቱታ ለማቅረብ ያደረጉት እንቅስቃሴ በወከባና ድብደባ ተበትኗል።
አቤት የምንልበት ቦታ አጣን በሚል በምሬት የሚገልጹት ተፈናቃዮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረስልንም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የሃና ማርያም አካባቢ መኖርያ ቤትን ማፍረስ የተጀመረው ዛሬ አይደለም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች። ከአንድ መት በፊትም ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች ያፈናቀ ርምጃ ተወስዷል ሲሉ ያክላሉ።
ያንን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭትም 10 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ያስታውሳሉ። ዛሬም ያ እጣ ፋንታ ለኛ ደርሶናል ይላሉ።ቁጥራቸው 2 ሺ የሚሆነው የሃና ማርያም አካባቢ ነዋሪዎች።
ነዋሪዎቹ ጎጆ ቀልሰው በአካባቢው ኑሮ ከመሰረቱ ከ10 አመት በላይ ማስቆጠሩንም ይናገራሉ።
ከአለም ሕጻናት ከግማሽ የሚበልጡት በጦርነትና በድህነት እየተሰቃዩ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 23/2010) ከአለማችን ሕጻናት ከግማሽ የሚበልጡት በጦርነትና በድህነት በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ሴቭ ዘ ችልድረን የተባለው አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ገለጸ።
መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ሴቭ ዘ ችልድረን ትላንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት በትንሹ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአለማችን ሕጻናት ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። 1 ቢሊየን ያህል ሕጻናት የሚኖሩት ድህነት በተስፋፋባቸው ሀገራት ነው።
240 ሚሊየን ሕጻናት ደግሞ ግጭት በቀጠለባቸው ሀገራት የሚኖሩ መሆናቸውን ሴቭ ዘችልድረን አስታውቋል።
እንደ አለም አቀፉ ግብረሰናይ ድርጅት ሪፖርት ከሆነ 575 ሚሊየን ሕጻናት የጾታ አድሎ በሚካሄድባቸው ሃገራት ውስጥ ይኖራሉ።
Wednesday, May 30, 2018
የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር በመለቀቃቸው የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን እንዳሉት የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለእንግሊዝ መንግስት ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ ከእስር ለማስፈታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።
እናም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከረጅም እስር በኋላ ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መገናኘቱ ለእንግሊዝ መንግስት ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል።
በአንዳርጋቸው ጽጌ መለቀቅ በርካታ ሰዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከየመን ታፍነው በኢትዮጵያ ደህንነቶች ከተወሰዱ በኋላ የእንግሊዝ መንግስት የእስር ርምጃውን በማውገዝ ከኢትዮጵያው አገዛዝ ጋር ሲወዛገብ ቆይቷል።
በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች ኢትዮጵያ በመጡ ቁጥር ቀዳሚ አጀንዳቸው በማድረግ ከሀገሪቱ አገዛዙ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል፣ከፍተኛ ጫና ለማድረግም ሞክረዋል።
በኢትዮጵያ አገዛዝ ባላስልጣናት በኩል ግን የሕዝብ ተቃውሞ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ ጉዳዩን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ነው የቆዩት።
የፌደራል ፖሊስ ሶስት ከፍተኛ ሃላፊዎች ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010) የፌደራል ፖሊስ ሶስት ከፍተኛ ሃላፊዎች ከስልጣን ተነሱ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ወደ ፌደራል ፖሊስ ሲዛወሩ፣ የቤተመንግስት አስተዳደር ሃላፊም ተሽረው ፣በምትካቸው አዲስ ሃላፊ ተሹሟል።
ከሁለት ዓመት በፊት ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ሃላፊነት የተባረሩት ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ የአንድ ኤጀንሲ ሃላፊ ሆነው መሾማቸውም ታውቋል።
በአዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ አዲስ ፎርቹን እንደዘገበው በፌደራል ፖሊስ ውስጥ ለረጅም አመታት የወንጀል መከላከል ሃላፊ በመሆን ሲሰሩ የቆዩትና በተግባር እውነተኛው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ሃላፊ ተደርገው የሚጠቀሱት ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል ግርማይ ከበደ ወይንም ግርማይ ማንጁስ ተነስተው በምትካቸው መላኩ ፈንታ ተሹመዋል።
መላኩ ፈንታ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩ መሆናቸውም በዘገባው ላይ ተመልክቷል። በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ የወንጀል ምርመራ ዋና ሃላፊ ረታ ተስፋዬ ተነስተው በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሃላፊንት ላይ የነበሩት ተኮላ አይፎክሩ ተሹመዋል።
በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ነው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማፈን ነባር የብአዴን እና የህወሃት አባላት በሙሉ ሃይላቸው እየተንቀሳቀሱ ነው። ለውጥ የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት ቁጥራቸው እየጨመረ ቢሆንም፣ ነባር የኢህአዴግ አመራሮች ከአዲሶቹ የድርጅቱ አመራሮች ጋር ተስማምተው ለመጓዝ ተቸግረዋል። ህወሃት በብአዴን ውስጥ ያለውን ክፍፍል ለራሱ ጥቅም ለማዋል እየተንቀሳቀ ሲሆን በተለይ የለውጡን እንቅስቃሴ አይደግፉም የሚባሉትን ነባር የድርጅቱን አመራሮችና አንዳንድ ወጣት አመራሮችን በመያዝ፣ ለውጡን ለመቀልበስ እየሰራ ነው። በብአዴን ውስጥ የለውጡ እንቅስቃሴ አገራዊ በሆነና የህዝቡን ፍላጎት በሚያሟላ መንገድ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ቡድኖች እየጎለበቱ ቢመጡም፣ አቶ በረከት ስምዖን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ከበደ ጫኔና የመሳሰሉ ነባር አመራሮች የለውጡን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ ከህወሃት ጎን ተሰልፈው ስራዎችን እየሰሩ ነው። የህወሃት መሪዎች ከደህዴን የተወሰኑ አመራሮችን ከጎናቸው ማሰልፍ ቢችሉም በኦህዴድ በኩል የሚከተሉዋቸውን ሰዎች ማግኘት አለመቻላቸው እንዲሁም በርካታ የብአዴን ወጣት አመራሮች የህወሃትን ሴራ ቀድሞ በመገንዘብ ለመተባባር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህወሃት እንደልቡ መንቀሳቀስ አልቻለም። ለውጥ ፈላጊ የብአዴን አመራሮች የእነ በረከትን ፍላጎት ለማስፈጸም ፈቃደኛ አለመሆናቸው እነ አቶ በረከት የመጨረሻ የሚሉትን እድላቸውን ለመጠቀም ላይ ታች እያሉ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ። በድርጅቶች ውስጥ ያለው የሃሳብ ልዩነት እየሰፋ መሄዱ ኢህአዴግን ከ2 ሊከፍለው ይችላል ተብሏል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በለውጥ ፈላጊዎች እንጅ በነባር አመራሮች ዘንድ ድጋፍ የላቸውም። አንዳንድ ነባር አመራሮችን በጡረታ አሰናብተው የግል ስራ እየፈለጉ እንዲቀጠሩ ለሌሎች ደግሞ በቦርድ አባልነት እየሾሙ የግል ህይወታቸውን እንዲመሩ ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ነባር አመራሮች ግን ከአመራር ቦታ መገለላቸውን በጸጋ አልተቀበሉትም። ህወሃት በመከላከያው እና ደህንነቱ ያለው የበላይነት እንዳይነካበት ጥረት እያደረገ ነው።
ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የመፍትሄ ያለህ እያሉ ነው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በመቶዎች የሚቆጠሩ ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ከኦሮምያ ክልል ቡኖ በደሌ ወረዳ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በአሁኑ ሰዓት በባህርዳር ከተማ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው በምግብ ዋስትና ግቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። በምግብ ዋስትና ግቢ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት ተፈናቃዮች፣ ከሳምንታት በፊት ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲሄዱ ቢደረግም፣ በቦታው ሲደርሱ የዞኑ አስተዳዳሪዎች ሊቀበሉዋቸው እንዳልቻሉና ተመልሰው ወደ ባህርዳር መሄዳቸውን ተፈናቃዮች ተናግረዋል። የአማራ ክልል አስተዳደር ተፈናቃዮች ወደ መጡበት ክልል እንዲመለሱ ወይም ወደ ተወለዱበት ቀዬ ሄደው እንዲኖሩ ሃሳብ ማቅረቡ ይታወቃል። ተፈናቃዮች ወደ ተፈናቀሉበት ክልል መመለስ እንደማይልጉ፣ ክልሉ መሬት ከሰጣቸው በየትኛውም ቦታ ሄደው መስራት እንደሚችሉ ሲገልጹ ቆይተዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቀረቡ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ/ም) የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያን ላዳረጉት ድጋፍ ቤተሰቦቻቸው ምስጋናቸውን ገልጸዋል። የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ሃይለማርያም እንዲሁም ታላቅ እህቱ ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ፣ ደስታቸውን በመግለጽ፣ ላለፉት 4 አመታት ህዝቡ ሲያደርገው ለነበረው ትግል ደስታቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አርበኞች ግንቦት7 በአቶ አንዳርጋቸው መፈታት የተሰማውን ደስታ ገልጿል። ንቅናቄው “ በጓዳችን መፈታት ደስ ብሎናል፤ የሚጠብቀን ብዙ መሆኑን እናውቃለን” በሚለው መግለጫው፣ “አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ ተፈቶ በጉጉት ከሚጠብቀው ሕዝብና ቤተሰቦቹ ጋር ሲቀላቀል ‘ሰው እየሳቀ ለመብቱም ለሕዝቡም መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ’ ብሎ መናገሩን የጠቀሰው መግለጫው፣ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ለሁሉም የህሊና እስረኞች መፈታት የበርካታ ዜጎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መታሰራቸውን ፣መደብደባቸውን፣ መሰደዳቸውንና ሰቆቃ የተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጿል። ትግሉ እሚፈለገው ግብ ላይ ለመድረስ ገና ብዙ መንገድ እንደሚቀረው የገለጸው የድርጅቱ መግለጫ፣ በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ የለውጥ ኃይሎች ለዚህ ድል ከፍተኛ
Tuesday, May 29, 2018
በአፋር ሰመራ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010)በአፋር ክልል ሰመራ ህዝባዊ ተቃውሞ ተደረገ።
የሰመራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በአፋር ያለው የመልካም አስተዳደር እጦት በመባባሱ ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
እስራትና ማፈናቀል በአፋሮች ላይ እየተጠናከረ መሆኑን በመጥቀስም ህዝቡ ተቃውሞውን ሲያሰማ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በአፋር ክልል ሰመራና ሌሎች ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ጥሪ የሚያደርግ በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል ነው የኢሳት የመረጃ ምንጮች የገለጹት።
ብረት ያነሱ አርበኞች ስርነቀል ለውጥ እስከሚመጣ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010) በኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ እስከሚመጣ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ብረት ያነሱ አርበኞች ገለጹ።
በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በተለያዩ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል በማድረግ በአገዛዙ የተለያዩ ወታደራዊና መንግስታዊ ተቋማት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ላይ የሚገኙት አርበኞች ሰሞኑን በአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እየቀረበ ያለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባብለዋል።
ሁለት የአርበኛ መሪዎች ወደ አገዛዙ የገቡበት ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ ነው ያሉት አርበኞች ትግሉን ከድተው እንደገቡ ተደርጎ የሚቀርበው ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን ለማደናገር ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነው ሲሉ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።
አሁንም በረሃ ላይ ነን፡ በኢትዮጵያ እውነተኛ ለውጥ እስከሚመጣ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ እስከሚመጣ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ብረት ያነሱ አርበኞች ገለጹ።
በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በተለያዩ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል በማድረግ በአገዛዙ የተለያዩ ወታደራዊና መንግስታዊ ተቋማት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ላይ የሚገኙት አርበኞች ሰሞኑን በአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እየቀረበ ያለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባብለዋል። ሁለት የአርበኛ መሪዎች ወደ አገዛዙ የገቡበት ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ ነው ያሉት አርበኞች ትግሉን ከድተው እንደገቡ ተደርጎ የሚቀርበው ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን ለማደናገር ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነው ሲሉ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። አሁንም በረሃ ላይ ነን፡ በኢትዮጵያ እውነተኛ ለውጥ እስከሚመጣ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል።
በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በሲዳማና ጋሞጎፋ 32 ሰዎች ሲሞቱ፣ በሶማሌ ክልል ደግሞ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በአካባቢዎቹ በጣለው የማያቋርጥ ዝናብ ምክንያት በደረሰ የመሬት መደርመስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል። በሶማሌ ክልል ብቻ በጎርፍ አደጋ ወደ 200ሺህ የሚጠጋ ህዝብ መፈናቁሉም ታውቋል። በስልጤ ዞንም 1ሺህ ነዋሪ በተመሳሳይ አደጋ ከ1ሺህ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ዓለማዓቀፉ የግጭት ዘጋቢ ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት ላይ ተመልክቷል።
አቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋና ጃዋር መሀመድ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ማቋረጡ ተነገረ።
በሁለት መገናኛ ብዙሃን ማለትም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) እና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ኤም ኤን)፣ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስም አቃቤሕግ ማንሳቱ ታውቋል። ይሕ በእንዲህ እንዳለ ግን በአርበኞች ግንቦት 7 ስም የተከሰሱ በርካታ ተከሳሾች ክስአሁንም አልተቋረጠም። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በእነ ዶክተር መረራ ጉዲና ክስ መዝገብ በሁለት መገናኛ ብዙሃንና ሁለት ታዋቂ ግለሰቦች ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስ ማንሳቱን ምንጮች ገልጸዋል። በእነ ዶክተር መረራ ክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ኤም ኤን)፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር ሞሃመድ ክሳቸው ተቋርጧል። ሁለቱ ታዋቂ ሰዎች በሌሉበት በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው አይዘነጋም። የዶክተር መረራ ጉዲና ክስ ቀደም ብሎ በመቋረጡ ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። ዐቃቤ ሕግ የ137 ተከሳሾችን ክስ እንዳነሳ ነው የተገለጸው። ይሕ በእንዲህ እንዳለ ግን በግንቦት 7 ተከሰው በማዕከላዊ ስቃይ የደረሰባቸው፣ ብልታቸው የተኮላሸው አስቻለው ደሴ እና ዮናስ ጋሻው ክሳቸው እንዳልተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል። በተያየዘም የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህሩ ጌታ አስራደን ጨምሮ የበርካታ አማራ ተወላጆች ክስ አለመቋረጡን ምንጮች ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ያሉትን ክስ ከማቋረጥ ይልቅ ቀደም ብሎ ክሳቸው የተቋረጠላቸውን ስም በማካተት የብዙ ተከሳሾች ክስ እንደተቋረጠ ነው የተነገረው። ከአሁን ቀደም ከእስር የተፈቱን አስቻለው አብርሃምና ሌሎች ተከሳሾችን ስም በማካተት ዐቃቤ ሕግ ክሳቸውን አቋርጫለሁ ማለቱ የቁጥር ማሟያ ለማድረግ ነው መባሉን አዲስ አበባ የሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል።
ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች እርዳታ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊዘጋጅ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት21/2010) ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉና በባህርዳር ለሚገኙ የአማራ ተወላጆች እርዳታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ታዋቂ ድምጻውያን ገለጹ።
አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ፥ አርቲስት ፍቅርአዲስ ነቃ ጥበብ እና አርቲስት አምሳል ምትኬ ተፈናቃዮቹ ወደሚገኙበት ባህርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በማምራት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በአሜሪካ የሚገኘው አርቲስት መሐሪ ደገፋውም 30 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ለተፈናቃዮቹ ልኮ በአርቲስቶቹ በኩል እንዲደርስ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።
አርቲስቶቹ በቤተክርስቲያኒቱ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ምግብ ከማብላታቸው በተጨማሪ በጠቅላላ 90 ሺህ ብር የሚገመት ገንዘብ መስጠታቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም እርዳታውን የሰጡት ታዋቂ ድምጻውያን ከቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቅለው በባህርዳር ለሚገኙ የአማራ ተፈናቃዮች የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
ኮንሰርቱ መቼና በምን ሁኔታ እንደሚካሄድ አርቲስቶቹ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።
Monday, May 28, 2018
ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ አደረጉ ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ አደረጉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) የረሃብ አድማው “ግንቦት 20 ለባርነት የተዳረግንበት ቀን ነው፣ እየተሰቃየን ያለነው በግንቦት 20 ቀን ወደ ስልጣን በወጡት ነው” በሚል ምክንያት መሆኑን ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል። እስረኞቹ ከቂሊንጦ እስር ቤት የሚሰጣቸውን ምግብ “አንቀበልም” በማለት መልሰዋል። በአሁን ሰዓት ከ250 በላይ የክስ ሂደታቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ቂሊንጦ ውስጥ ይገኛሉ። የ”ሽብር” ክስ ከተመሰረተባቸው እስረኞች መካከል አብዛኛዎቹ በማዕከላዊ እና በቂሊንጦ እስር ቤት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል።
የጅማ ከተማ ህዝብ በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጀግና አቀባባል አደረገ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) እጅግ በርካታ የከተማዋ ህዝብ በጅማ ስቴዲየም ተገኝቶ አህመዲን ጀበልን የተቀበለው ሲሆን፣ ከህዝቡ የተዋጣውን የገንዘብ ስጦታም አበርክቶለታል። ኡስታዝ አህመዲን “ ከዚህ በሁዋላ ውሸታም መሪ፣ አስመሳይ አስተዳደር የኢትዮጵያ ህዝብ አይፈልግም። እኔ ሁሉንም ዘር ሃይማኖት ሳልለይ እውዳለሁ። ኦሮሞ ነኝ፣ ሙስሊም ነኝ፣ ሰው ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ከሁሉም ፋር የምጋራቸው ነገሮች ስላሉ ሁሉንም እወዳለሁ። በዘር ፣ በብሄር፣ በሃይማኖት አንለያይም” በማለት የህዝቡን ስሜት የገዛ ንግግር አድርጓል። ኡስታዝ አህመዲን ይህንን ህዝብ ፍቅር እንጅ ክላሽ አይገዛውም ያለው አቶ አህመዲን፣ ባለፈው ተቃውሞ ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 20 ሺ ብር በአጠቃላይ 100 ሺ ብር ለግሷቸዋል።
የሶማሊ ልዩ ሃይል ሚሊሺያዎች በአሮምያ ክልል አዋሳኝ ከተሞች በመግባት ጥቃት ፈጸሙ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ-ሶማሊ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ ፐሬዚዳንት አቶ አብዲ አሌ ሚሊሺያዎችን ወደ ጭናክስን በመላክ ቢያስን 4 ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል። ከ100 ያላነሱ ሰዎች አካባቢውን ጥለው ሲሸሹ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ደግሞ መቃጠላቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው አቶ አብዲ አሌ የፌደራል ባለስልጣናት እርሳቸውን ከስልጣን ለማውረድ የሚሞክ ከሆነ ጅግጅጋን ሞቃዲሾ እንደሚያደርጓት ሰሞኑት ከተለያዩ የክልሉ አመራሮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ መዛታቸውን የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።
በኮሬና ጉጂ ብሄረሰቦች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) መቋጫ ያልተገኘለት በአማሮ ወረዳ በሚኖሩ የኮሬና አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ጉጂዎች መካከል ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከ11 ወራት በላይ የወሰደው ደም አፈሳጭ ግጭት ሰሞኑን አገርሽ 6 የኮሬ ብሄረሰብ አባላት ሲገደሉ ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። እስካሁን ባለው ግጭት በከሮ በኩል ከ50 ያላነሱ ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ደግሞ ቆስለዋል። በጉጂ በኩል የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም። በአካባቢው የተሰማሩት የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አዛዦች ግጭቱን ለማስቆምና የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ምንም አይነት እርምጃ ባለመውሰዳቸው የአካባቢው ማህበረሰብ ተስፋ አስቆርጧል። የአገሪቱ መንግስትም ሆነ ሚዲያዎቹ ስለ ግጭቱ አለመዘገባቸው የአካባቢው ማህበረሰብን እያበሳጨ ነው። ከ2 ሺ በላይ ዜጎች እርዳታ አጥተው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ከአራት ዓመታት በፊት የዓለምአቀፍ ሕግን በሚጻረር መልኩ ከየመን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ታግተው የተወሰዱት የነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንደተፈቱ በስፋት ቢነገርም ከመንግስት፣ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ዘንድ ማረጋገጥ አልተቻለም።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በህገወጥ መንገድ ከታገቱበት ጊዜ አንስቶ በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞ ሰልፎችና በተለያዩ መድረኮች ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። ከዚህም ባሻገር አንዳርጋቸውን ለማስለቀቅና እርሳቸው የታሰሩለትን ዓላማ ከዳር ለማድረስ በተደረገ ትግል የህይወት መስዋዕት ድረስ የከፈሉ ጥቂቶች አይደሉም። ከሳምንት በፊት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቤተመንግስት ባደረጉት ንግግር አንዳርጋቸው በመታሰሩ መንግስታቸው ከጉዳት በስተቀር ያገኘው ጥቅም እንደሌለ በመጥቀስ የነጻነት ታጋዩ በተያዘው ሳምንት እንደሚፈታ መናገራቸው ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስተው እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተስፋ ሲጠባበቁ ሰንብተዋል። በተለይ እንዲፈታ መወሰኑ ከተነገረበት ካለፉት ሦስት ቀናት ወዲህ ብዙ ቁጥር ያለው ሕዝብ በየእለቱ ቃሊቲ ድረስ በመጉረፍና በመኖሪያ ቤቱ በመታደም በከፍተኛ ጉጉትና ደስታ ባረገዘ ምጥ ሲጠብቀው ቆይቷል። የኢሳት ወኪሎች ከአዲስ አበባ እንደዘገቡት በዛሬው ዕለት ለአንዳርጋቸው አቀባበል ለማድረግ ብዛት ያላቸው ታክሲዎችና የቤት መኪናዎች በቃሊቲ የተገኙ ሲሆን፣ ከተማው የአንዳርጋቸው ምስል ያለበትን ቲሸርት በለበሱ ወጣቶች ተሞልቶ ውሏል። ነገረ ፍችው ከተሰማበት ጊዜ አንስቶም ለአቀባበሉ ግብረኃይል ያቋቋሙ የመዲናዋ ወጣቶች የወላጆቹን ቤት በማድመቅ፣ ቲሸርት በማሳተምና የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ሲደክሙ የሰነበቱ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በወላጆቹ መኖሪያ ቤት ላይ “የመርህ ሰው” በሚል ርዕስ ምስሉን በትልቁ ሰቅለዋል። በዛሬው ዕለት ሕዝቡ በከፍተኛ ስሜት ሆኖ በቃሊቲ በር ላይ እየተጠባበቀ ባለበት ጊዜ ከእስር ቤቱ ውስጥ በጥቁር መስተዋት የተሸፈኑ ወደ አምስት የሚሆኑ “ቪ8″ መኪናዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወጥተው የተጓዙ ሲሆን፣ በስፍራው የነበሩ ኢትዮጵያውያን የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድኛው መኪና ውስጥ ሆነው ሳይወጡ እንዳልቀሩ ገምተዋል።
Saturday, May 26, 2018
ስንት አከሰሩን? Getachew Shiferaw
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአቶ አንዳርጋቸው እስር ብቻ 11 ቢሊዮን ዶላር እንደቀረ ተናግረዋል። 11 ቢሊዮን በጊዜው ዶላር ተመን ወደ 308 ቢሊዮን ብር ይደርሳል!
አንድ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰራ ወዳጄ እንዳጫወተኝ፣ አንድ እስከ 6 ሺህ ሰራተኛ የሚቀጥር ፋብሪካ ለመገንባት እስከ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ይጨርሳል። 308 ቢሊዮን ብር ደግሞ 123 ፋብሪካዎችን ይገነባል። እነዚህ ፋብሪካዎች ደግሞ 739, 200 ያህል ሰራተኞችን ይቀጥራሉ። እነዚህ ሰራተኞች በአማካይ 3 ቤተሰብ ቢያስተዳድሩ 2,196,600 ህዝብ ኑሮ ተሻሻለ ማለት ነው። 123 ፋብሪካዎች ሲያመርቱ ለህዝብ የሚያበተክቱትን አቅርቦት፣ የውጭ ምንዛሬ በቀላሉ ማሰብ ይቻላል። ለሀገር ጥቅም ቢውል ኖሮ ከሚል መነሻ
Friday, May 25, 2018
በአርባምንጭ ከተማ በፌደራል ፖሊስና በነዋሪው መካከል ግጭት ተፈጠረ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010)በአርባምንጭ ከተማ በፌደራል ፖሊስና በነዋሪው መካከል ግጭት መፈጠሩ ተገለጸ።
ጉርባ በተሰኘው የከተማው ክፍል መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ የተሰማራውን ግብረሃይል ነዋሪው ማስቆሙን ተከትሎ በመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ወደ ጉርባ የገባው የፌደራል ፖሊስ ህዝቡ ላይ መተኮሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ከ20 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውም ታውቋል። ከ4ሺህ በላይ ነዋሪ በላዩ ላይ ቤት መፍረሱ ሌላውን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪን እንዳስቆጣም ለማወቅ ተችሏል።
ሻራ በተሰኘውም መንደር በተመሳሳይ የአፍራሽ ግብረ ሃይል መሰማራቱ ታውቋል።
ጉርባ በአርባምንጭ ከሚገኙ መንደሮች አንዱ ነው። አካባቢው በቀድሞው መንግስት ለወታደራዊ ካምፕ አገልግሎት እንዲውል ታስቦ እንደነበረ ይነገራል።
ይሁንና የህወሃት አገዛዝ ስልጣን ከያዘ ወዲህ በአካባቢው በህጋዊ መንገድ ሰዎች መኖሪያ ቤት ገንብተው የሞቀ መንደር አድርገውት ቆይተዋል።
ላለፉት 20 ዓመታት ጉርባ በተሰኘው መንደር መኖሪያቸውን ቀልሰው ልጅ ወልደው ቤተሰብ መስርተው የሚኖሩት ከ4ሺህ በላይ አባወራዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ የመብራትና የውሃን ጨምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን ሲፈጽሙ ቆይተዋል።
ከ900 በላይ የአማራ ተወላጆች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010) ከኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ደጋ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ900 በላይ የአማራ ተወላጆች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ።
ተፈናቃዮቹ በአማራና ኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ትብብር በወልዲያና በጭፍራ መካከል በሚገኝ ሃሮ ተብሎ በሚጠራ በረሃ ላይ ሰፍረው የሚገኙ ሲሆን ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱም በመከላከያ ሰራዊት እየተጠበቁ መሆናቸውም ተገልጿል።
አካባቢው ደረቅ መሆኑና ውሃ ማግኘት አለመቻሉ ህጻናት ለበሽታ እየተጋለጡ መሆናቸውን ከስፈራው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ተፈናቃዮቹ በደርግ የአገዛዝ ዘመን በ1972 በሰፈራ ወደ አካባቢው መሄዳቸውን ይናግራሉ ።
በሰፈሩበት አካባቢም ለዘመናት መኖራቸውንና ሃብት ንብረት አፍርተው በሰላም ይኖሩ እንደነበር በስፍራው ተግኝቶ ለነበረው ታዛቢ ቡድን ተናግራዋል ።
መሬቱ የእናንተ አይደለም ልቀቁና ሄዱ ተብለው አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውንም ይናገራሉ።
በኢሉባቡር የአማራ ተወላጆችን ማፈናቀሉ በአምስት ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን የቡኖ በደሌ ግን የከፋ እንደሆነ ተገልጿል።
ተፈናቃዮቹ በፖሊስ ታስረው ከቆዩ በኋላ ጥቅምት 9/2010 የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች ባለስልጣናት በመተባበር አሁን ወደሚገኙበት በወልዲያና ጭሮ መካከል በሚገኘው ሃሮ በረሃ ላይ እንዲሰፍሩ ተደርገዋል።
ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሜቴክ የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17 /2010) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሜቴክ የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ።
በቅርቡ የኢንደስትሪ ሚኒስተር ሆነው የተሾሙት ዶክተር አምባቸው መኮንን አቶ ደመቀ መኮንንን ተክተው የቦርድ ሊቀመንበር ሆነዋል።
የሕወሃቱ አቶ አስመላሸ ወልደ ስላሴም የሜቴክ ቦርድ አባል ሆነዋል። ከፖለቲካ መድረኩ የተገለሉ ሰዎች ተመልሰው ወደ ሃላፊነት መምጣታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
የሕወሃቱ አቶ አስመላሸ ወልደ ስላሴም የሜቴክ ቦርድ አባል ሆነዋል። ከፖለቲካ መድረኩ የተገለሉ ሰዎች ተመልሰው ወደ ሃላፊነት መምጣታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
በመንግስት 10 ቢሊዮን ብር በጀት የተቋቋመው የመሰረታዊ ብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ከፍተኛ የሃገር ሃብት ምዝበራ የሚካሄደበት ተቋም መሆኑ ሲጠቀስ ቆይቷል።
የዚህ ተቋም ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ጄነራል ክንፈ ዳኘው የሕወሃት ታጋይ የነበሩ ናቸው።
የነ አቶ መላኩ ፈንታ ክስ ተቋረጠ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010)አቶ መላኩ ፈንታና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ በሌብነት ወንጀል የተከሰሱ ታዋቂ ባለሀብቶች ክሳቸው መቋረጡን ፋና ዘገበ።
የእነ እቶ መላኩ ክስ መቋረጥ የሕወሃት ንብረት በሆነው ፋና በሮድካስቲንግ በይፋ ከተዘገበ በኋላ ዜናው ከድረገጹ እንዲነሳ መደረጉ ታውቋል።
ከአንድ ሰዓት በኋላ ደግሞ ክሳቸው እንዲቋረጥ አቃቤ ህግ ጠየቀ ሲል ሌላ ዘገባ አቅርቧል።
በሌብነት ወንጀል ተከሰው የነበሩት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ክሳቸው መቋረጡን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።
Thursday, May 24, 2018
በዘጠኝ ወራት ውስጥ የቆዳ ውጤቶችን ለውጭ ገበያ አቅርቦ 181 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ዕቅድ ቢያዝም ማግኘት የተቻለው 99 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ተባለ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) ይህም ከተያዘው ዕቅድ የተሳካው ግማሽ ያህሉ ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲት ዩት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ፍሪደሞ አመልክተዋል። ዕቅዱን ማሳካት ያልተቻለበት ዋነኛ ምክንያት የቆዳና ሌጦ ጥራት አለመሻሻሉ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። እንዲሁም ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሎ የነበሩ ፋብሪካዎች ሥራ አለመጀመራቸው፣ ፋብሪካዎች ከአቅም በታች ማምረት መጀመራቸወና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አለመጠቀማቸው በተጨማሪ ምክንያትነት ተጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በተከሰተው ከፍተኛ የኃይል እጥረት ሳቢያ በርካታ ፋብሪካዎች ከአቅም በታች ለማምረት መገደዳቸውና አንዳንዶችም ጨርሶ እስከመዘጋት መድረሳቸው ይታወቃል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ 32 የቆዳ ፋብሪካዎች፣ 23 የጫማ ፋብሪካዎች፣ አራት የቆዳ ጓንት ፋብሪካዎች እና 19 የቆዳ አልባሳትና እቃዎች ማምረቻ ፋብሪካዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ ያቀረቡት 26 የቆዳ፣ 14 የጫማ እና ሁለት የቆዳ ጓንት አምራቾች ብቻ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም የገበያ ዋጋ ተመን ያለመሸጣቸው ሁኔታ ሌላው ዘርፉ የተጋረጠበት ችግር ነው ያሉት አቶ ብርሃኑ፤ለዋጋ ልዩነቱም አንድኛው ምክንያት የፋብሪካዎቹ ዋጋ የመደራደር አቅም ውስንነት እንደሆነ መናገራቸውን ከአዲስ ዘመን ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።
በአፋርና አማራ ክልል ድንበር ላይ በተፈጠረው ግጭት የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በአፋርና በአማራ ክልል አቅራቢያ በደቡብ ወሎ አካባቢ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግጭት የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። ሁለቱ ክልሎች ችግሮቻቸውን በውይይት እንደፈቱ በመገናኛ ብዙሃን ተናግረው የነበረ ቢሆንም፣ ግጭቱ እንደገና አገርሽቶ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል። በግጭቱ ዙሪያ የሁለቱ ክልል ባለስልጣናት እስካሁን የሰጡት መግለጫ የለም።
መከላከያው ከእነ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ እጅ እየወጣ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) ወታደራዊ ምንጮች እንደሚገልጹት-አብዛኞቹ ከጄኔራልነት በታች ማዕረግ ያላቸው መኮንኖችና ወታደሮች ፣ጄ/ል ሳሞራ የኑስ የሚመራውን በ8 ጄኔራሎች የተዋቀረውን ወታደራዊ እዝ ለመቀበል ፍላጎት እያጡ ነው። የበታች መኮንኖችና ወታደሮች ለውጥ እየፈለጉ መምጣታቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ በዚህም ሳቢያ ቁንጮ ሹመኞቹ ትዕዛዞችን እንደ ወትሮው ማስፈጸም እየተቸገሩ ነው ይላሉ። ለውጡ ወታደራዊ ተቋማቱንም እንዲነካ የሚጠይቁት ወታደሮችና መኮንኖች፣ በቅርቡ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር መከላከያውን የማዋቀር ዘመቻ ካላደረጉ በመከላከያው ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። በሳሞራና በህወሃት ወታደራዊ አዛዦች እንደተማረሩ የሚናገሩት የሰራዊቱ አባላት፣ በሰራዊቱ ውስጥ አጠቃላይ መዋቅራዊ ለውጥ ይመጣል ብለው ተስፋ እያደረጉ መሆናቸውን አልሸሸጉም። መዋቅራዊ ለውጡ ሁሉንም አካባቢዎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ያስተናግዳል ብለው እየጠበቁ እንደሆነም ገልጸዋል። “ በህዝቡ ላይ እርምጃ ውሰዱ ፣ ሽብርተኞች እና ገንጣዮች ገብተዋል እየተባልን እርምጃ እንድንወስድ ስንታዘዝ የአገር አንድነትን
በሶማሊ ክልል አብዲ ኢሌን በመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል
(ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በሊበን ዞን በዶሎ አዶ ትናንት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ አብዲ ኢሌ ሚሊሺያዎቹን በማዘዝ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጉን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። ተቃውሞውን ለመበተን ልዩ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ እስካሁን ድረስ 3 ሰዎች መገደላቸውንና ከ10 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ተወላጆቹ ተናግረዋል። ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የገጠመው አብዲ ኢሌ የትኩረት አቅጣጫ ለማሳትና ችግሩን ከጎሳ ግጭት ጋር ለማያያዝ በሶማሊ ክልል በጃርሶና እና ገሪ ጎሳዎች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ እያደረገ ነው። ትናንት በቱሊጉሌድ ከተማ በገሪና ጀርሶ ጎሳዎች መካከል የተጀመረውን ግጭት ተከትሎ እስካሁን የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ተዋላጆች ይናገራሉ። የህወሃት ነባር አመራሮች አብዲ ኢሌ ከስልጣን እንዲነሳ ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙትን የአገር ሽማግሌዎች- ከአብዲ አሌ ጋር ለማስታረቅ እየተመላላሱ ቢሆንም ዛሬም አልተሳካለቸውም። በአንድ በኩል የሽምግለና ጥረት እየተደረገ በሌላ በኩል ደግሞ ግድያውና እስሩ ተጠናክሮ መጠሉን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ አብዲ ኢሌ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ የፌደራል ባለስልጣናት እንዲደግፉት የማሳመን ስራ እየሰራ ነው። በኢህአዴግ ውስጥ ከአብዲ አሌ ገንዘብ ያልተቀበለ ነባር አመራር እንደሌለ የሚገልጹት ምንጮች፣ አሁንም ድረስ ብዙ ባለስልጣናት አብዲ ኢሌ በስልጣን እንዲቆይላቸው ይፈልጋሉ ብለዋል። ከህወሃት ጄኔራሎችና ነባር አመራሮች በተጨማሪ እነ አምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚዓብሄርና ጌታቸው አምባዬ የአብዲ ኢሌ ተከፋዮች መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በዚህም የተነሳ አብዲ አሌ በክልሉ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ሲፈጸም አይተው እንዳላዩ ሲያልፉት መቆየታቸውንና አሁንም አዲሱ የዶ/ር አብይ አስተዳደር ይህንኑ አካሄድ እንዲከተል ጫና እያሳደሩ መሆናቸውን የቅርብ እማኞች ተናግረዋል
Wednesday, May 23, 2018
አቶ እውነቱ ብላታ ከሃላፊነታቸው ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010) በብራስልስ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በቅርቡ ተሹመው የነበሩት አቶ እውነቱ ብላታ ከሃላፊነታቸው ተነሱ።
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ምክንያቶች የአምባሳደሮች ጥሪና ሽግሽግ ማካሄዱን አስታወቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎም በሪያድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተነስተው በሌላ እንዲተኩ መደረጉ ተሰምቷል።
ወይዘሮ አስቴር ማሞና አቶ እውነቱ ብላታ ከእነ ባለቤቶቻቸው በአንድ ኤምባሲ እንዲሰሩ መመደባቸውም ጥያቄ አስነስቷል።
ይህንኑ ተከትሎም በብራስልስ የኢፌድሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በቅርቡ ተሹመው የነበሩት አቶ እውነቱ ብላታ ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል። በተያያዘ ዜናም አምባሳደር አሚን አቡዱል ቃድር ከሪያድ ወደ አልጄሪያ ተዛውረው ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተመድበዋል።
አቶ በላይነህ ክንዴ በዳሎል ባንኩ ውስጥ ድርሻ የለኝም አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2010) የትግራይ ተወላጆች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን ባቋቋሙት ዳሎል ባንክ ውስጥ ባለድርሻ ተደርገው ስማቸው የተጠቀሰው የአማራው ባለሃብት አቶ በላይነህ ክንዴ በባንኩ ውስጥ ምንም ድርሻ እንደሌላቸው ገለጹ።
ይህም የትግራይ ተወላጆች በባንኩ ወስጥ ያላቸውን የ 63 በመቶ ድርሻ ይበልጥ ከፍ የሚያደርገው ሆኖ ተገኝቷል፥ባንኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃብት ለመንቀሳቀስ በመወሰን መቁቋሙንም ኢሳት ምንጮችን በመጥቀስ ባለፈው መጋቢት ወር መጨረሻ ዘገባ ማቅረቡም ይታወሳል።
በኢትዮጵያ 17ኛው የግል ባንክ ለመሆን በመንቀሳቀስ ላይ ያለው ዳሎል ባንክ ከመነሻው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተርስቲያን አማካኝነት ሊቋቋም የነበረ ነው፣ብሄራዊ ባንክ የዕምነት ተቋማት ባንክ እንዲያቋቋሙ አይፈቀድም የሚል ምላሽ ሲሰጥ፣ ቤተክህነት ከትግራይ ባለሃብቶች ጋር ባንኩን ወደ ማቋቋም አምርታለች፣በዚህ ባንክ ወስጥ የትግራይ ባለሃብቶች 63 በመቶ ድርሻ ሲይዙ ፣ቤተክህነት 19 በመቶውን ወስዳለች።
በዳሎል ባንክ ወስጥ ከፍተኛ ባለድርሻ ተደርገው የተጠቀሱት ብቸኛው የአማራ ባለሃብት አቶ በላይንህ ክንዴ በባንኩ ወስጥ ምንም ደርሻ እንደሌላቸወ በይፋ አስታውቀዋል።
አቶ በላይነህ ክንዴ በሳምንቱ መጨረሻ አዲስ አበባ ከተማ ከሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በዳሎል ባንክ ወስጥ ስላላቸው ድርሻ ተጠይቀው አንድ ብር እንኳን እንደሌላቸው በሚከተለው መልክ ገልጸዋል።
“ አክሲዮን እንድገዛ ተጠይቄ ፈቃደኛ አለመሆኔን ገልጫለሁ፡፡ እኔም በባንኩ ውስጥ እንዳለሁበት ተደርጎ ሲነገር ሰምቻለሁ፡፡ በአጠቃላይ ግን እኔ በአዲሱ ባንክ ውስጥ የአንድ ብር አክሲዮን የለኝም፡፡” ብለዋል።
የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ።
ዶክተር አብይ አሕመድ ትላንት በብሔራዊ ቤተመንግስት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ባካሄዱት ውይይት እንዳሉት ኢትዮጵያ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰሯ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር አጥታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተበላሸውን ኢሕአዴግ የማስተካከል ርምጃ እየወሰድኩ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በብሔራዊ ቤተመንግስት በተካሄደው ስነስርአት ላይ እንደተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ኢሕአዴግ ማሰሩ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም። እንዲያውም የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ኢትዮጵያን ጎድቷታል ነው ያሉት። ዶክተር አብይ እንደገለጹት ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰሯ ከእንግሊዝ መንግስት ልታገኝ የምትችለውን በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል፡፡ እናም አቶ አንዳርጋቸውን ማሰር ጥቅም ስለሌለው ከሌሎች ባለሃብቶች ጋር በሚቀጥለው ሳምንት ይፈታል ብለዋል። ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ጉዳይ ጋር በተያያዘም ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ብዙ ንትርክና ክርክር
Tuesday, May 22, 2018
በሽንሌ ዞን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ አለመላኩን የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በኢትዮ-ሶማሊ ክልል በሽንሌ ዞን ፣ በሃርዋ ፣ ገሚ፣ አይሎሶና ሌሎችም ቦታዎች አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ የተጎዱ ዜጎች እስካሁን ድጋፍ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለችግር ተዳርገዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤቶች መፍረሳቸውን፣ አንድ ሺ የሚሆኑ የእርሻ ማሳዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። የሶማሊ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ተጎጂዎችን በመርዳት በኩል እስካሁን የወሰደው እርምጃ ባለመኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። በሽንሌ ዞን የሚገኙ የሶማሊ ተወላጆች ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት የአብዲ ኢሌን አገዛዝ በመቃወም ሰልፍ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።
በረከት ስምዖን ህወሃትን ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ ጠ/ሚኒስትር ሆኖ መመረጡን ያልተቀበሉት አቶ በረከት ስምዖን፣ ከህወሃት ጋር በመሆን የእነ ዶ/ር አብይንና ለማን ቡድን ለመምታት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል። በኢሃዴግ ውስጥ ያላቸው ተቀባይነት እየተመናመነ የመጣው አቶ በረከት፣ በድርጅት አባልነት ከተመዘገቡበት ብአዴን ይልቅ ከህወሃት ጋር ጥምረት በመፍጠር እርሳቸውና በህወሃት ዙሪያ የሚገኙ ጓደኞቻቸው የሚቆጣጠሩትን ስርዓት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ ከህወሃት በስተቀር የሌሎች ድርጅቶች ነባር ታጋዮችን ድጋፍ ለማገኘት ባለመቻላቸው ሙከራው ሁሉ እየከሸፈበቸው ነው። ስልጣናን መልሶ የሚቆጣጠርበት መንገድ ለመተለም የተለያዩ አማራጮችን እያየ ያለው ህወሃት፣ በብአዴን ውስጥ ያለው ተቀባይነት እየቀነሰ የመጣውን አቶ በረከትን ፊት በማሰለፍ የ27 አመታት የበላይነቱን ለማስጠበቅ እንደ አንድ አማራጭ ወስዶታል። አቶ አባዱላ ገመዳ የጠ/ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሆነው በመሾማቸው ህወሃት በእርሳቸው በኩል ሊጫወት ያዘጋጀውን ካርድ እንደተበላ የሚገልጹት የኦህዴድ ምንጮች፣ አቶ በረከት ስምዖን ቀጣዩን ሂደት እንዲጫወትላቸው እያዘጋጁት ቢሆንም፣ እቅዳቸው ለውጥ በሚሹ የኢህአዴግ አባላት አስቀድሞ በመታወቁ እየከሸፈ መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ህወሃት በኢትዮ-ሶማሊ ክልል መሪ በኩል ሊፈጥር ያሰበውን ጫና የተረዱት ኦህዴዶች፣ ከሶማሊ ክልል ጋር ያለውን ጉዳይ አለሳልሰው በመያዝ ለህወሃት መግቢያ እንዳሳጡትም ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ወደ ተቃውሞ ተቀየረ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ በአካባቢው አመጽ መቀስቀሱ ተነገረ።
የሚዛን ቴፒ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት አመጽም ትምህርት ተቋርጧል።
በሚዛን ቴፒ ማጅ እና ጎጄብ መንገዶች ከመዘጋጋታቸው በተጨማሪ የንግድ መደብሮችም ተዘጋግተዋል።
የመከላከያ አባላትና የፌዲራል ፖሊስ አመጹን ለማርገብ በሕዝቡ ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸ ተነግሯል።
የሚዛን ቴፒ የሕዝብ ተቃውሞ ከጎጀብ ወንዝ በበቃ እንዲሁም ማሻ ይደርሳል። የተቃውሟቸው መንስኤ ደግሞ በተደጋጋሚ ጊዜ የጠየቋቸው የልማጥ ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው እንደሆነም ይነገራል።
የሜድሮክና ኢዛና የወርቅ አውጪ ኩባንያዎች ከመመሪያ ወጭ ወርቅ ሲሸጡ ነበር ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14 /2010 ) የሼህ መሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ሜድሮክ ጎልድ እንዲሁም የሕወሓት ንብረት የሆነው ኢዛና ጎልድ ከቤሄራዊ ባንክ መመሪያ ወጭ በልዩ ድጋፍ ወርቅ ሲሸጡ መቆየታቸው ተገለጸ።
በሌላም በኩል የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከብር ምንዛሪ ለውጥ ጋር በተያያዘ መገምገማቸው ታወቀ ።
ቤተሰቦቻቸውንም ወደ አሜሪካ አሽሽተዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሜድሮክ ጎልድ ባለፉት 20 ዓመታት ከሻኪሶ የሚያወጣውን ወርቅ በብሄራዊ ባንክ በኩል ማስተላለፍ የሚገባው ቢሆንም በልዩ ትዕዛዝ በቀጥታ ሲሸጥ መቆየቱ ተመልክቷል።
በዚህም ለተወሰኑ ግዚያት በተላያዩ መጠኖች ስለ ሽያጩ ለብሄራዊ ባንክ ሪፖርት ያደረገ ቢሆንም፣አጠቃላይ የንግድ ሂደቱን የተመለከተ መረጃ ግን በብሄራዊ ባንክ እንደማይገኝ ከኢሳት ምንጮች መረዳት ተችሏል።
የንግድ ልውውጡ ለምን በብሄራዊ ባንክ በኩል አልሆነም በሚል ከሚመለከታቸው የባንኩ ባለሙያዎች ለሚቀርበው ጥያቄ የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ተዉኣቸው በሚል ይከላከሉ እንደነበርም ተመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት የሆነው እና ከኤፈርት ተቋማት አንዱ የሆነው ኢዛና ጎልድ በሕገወጥ መንገድ ወርቅ ከሃገር እያወጣ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።
የሶማሌ ክልል የሃገር ሽየሶማሌ ክልል የሃገር ሽማግሌዎችን ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነውማግሌዎችን ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) የሕወሃት ጄኔራሎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ የገቡትን የሶማሌ ክልል የሃገር ሽማግሌዎችን እያስፈራሩ መሆኑ ታወቀ።
የሃገር ሽማግሌዎቹ ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ጫና እያደረጉ መሆኑም ታውቋል። የአብዲ ኢሌ አስተዳደር ለሕወሃት ጄኔራሎችና ለደህንነቶች ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ሽማግሌዎቹ ወደ ሶማሌ ክልል እንዲመለሱ ግፊት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።
ከአብዲ ኢሌ በድብቅ ገንዘብ ከተከፈላቸው ጄኔራሎቹ መካከልም ገብሬ ዲላና ማአሾ እንደሚገኙበትም የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል።
ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙት የሶማሌ ክልል ሽማግሌዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሳያገኙ አንድ ወር እንዳለፋቸው በምሬት በመገለጽ ላይ መሆናቸውንም መረጃው አመልክቷል።
150 የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ ከገቡ አንድ ወር አልፏቸዋል። እስከሁን ያናገራቸው የመንግስት ባለስልጣን የለም።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ደጅ በተደጋጋሚ ቢጠኑም የሚያስጠጋቸው አላገኙም። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ የህወሀት ጄነራሎችና የደህንነት ሰዎች ወከባ ውስጥ ወድቀዋል።
Monday, May 21, 2018
የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በማስፈጸም ረገድ በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት ተገለጸ፡፡
(ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የማስፈጸም ችግሩ በአንድ ሴክተር መስሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሴክተሮቻችን የሚታይ ችግር ነው የሚሉት የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን አብዛኛውን ነገር እያሰረ ያለው የማስፈጸሙ ችግር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከኢንቨስትመንት አኳያ ባለሃብት መማምጣት ላይ ችግር እንደሌለ ሚገልጹት ከፍተኛ አመራር ዋናው ችግር የመጡትን ባለሃብቶች በመጡበት ፍጥነት ወደ ስራ ያለማስገባት መሰረታዊ ችግር እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ በዚህ ዓመት በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመሰማራት የጠየቁ ከሁለት ሽህ በላይ ባለ ሃብቶች ቢኖርም ፣ከነዚህ ውስጥ ወደ ስራ የገቡት 591 ብቻ ናቸው።ባለሃብቱ እንደመጣ መሬት በማግኘት ወደ ስራ የሚገባበትን አሰራር የክልሉ መንግስት በግልጽ ማስቀመጡን የሚጠቅሱት ከፍተኛ አመራር ፍላጎቱንና የመሬቱን አቅርቦት አመጠጣጥኖ በመስራት በኩል መሰረታዊ ችግሮች በአመራሩ በኩል እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል፡፡ “ባለሃብቱ በክልሉ ላይ ያሉ ዕድሎችን በአመዛኙ አውቋቸዋል” የሚሉት ከፍተኛ አመራር ዋና ችግር ሆኖ የሚታየው በዚህ ክልል ላይ ማልማት አለብን ብለው የሚመጡትን ባለሃብቶች ከማስተናገድ ጋር ያለ ችግር መሆኑን አብራርተዋል፡፡”የተመዘገበው ባለሃብት ሳስተናገድ ሌላ ባለሃብት መሳብ ለምን ያስፈልጋል ?” የሚል አመለካከት ማራመዳቸውን የሚገልጹት ባለሰልጣን ፣በሁለተኛነት የሚያነሱት በበላይ አመራሮች በስፋት የሚታየው የአቅም ችግር መኖር የክልሉን ኢንቨስትመንት በተፈለገው ፍጥነት ለማራመድ እንቅፋት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅሟ በመዳከሙ የአጭር ጊዜ ብድር መውሰድ አቆመች
(ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢትዮጵያ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ የተበደረችውን ብድር በወቅቱ ለመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መምጣቱን ተከትሎ በአጭር የክፍያ ጊዜና በከፍተኛ የወለድ መጠን የሚሰጡ ብድሮችን መበደር ማቆሟን የገንዘብ ሚኒስትሩ ለሪፖርተር ተናግረዋል። አገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች በቂ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች ተብሎ ቢታቀድም እቅዱ ሊሳካ አለመቻሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በአጭር ጊዜ የሚመለስ ብድሮችን ከምዕራባውያን ባንኮች፣ ከቻይናና ከሌሎችም አገሮች በከፍተኛ ወለድ ስትበደር ቆይታለች። እነዚህ ብድሮች ብዙዎቹ የመክፈያ ጊዜያቸው በመድረሱ አገሪቱ ለወለድና ለዋናው ብድር ክፍያ ከፍተኛ ወጪ እያወጣች ነው። አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ የእዳ ጫና አሳሳቢ መሆኑን በመግለጽ፣ እጅግ ከፍተኛ የእዳ ጫና ካለባቸው አገሮች ተርታ የመደባት ሲሆን፣ መንግስት ብድር ለመውሰድ ያለውን ፍላጎት
የዋልያ ቢራ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በሆላንዱ ታዋቂ የቢራ ፋብሪካ ሃይነከን የተገነባው ቂሊንጦ በሚገኘው የቢራ ፋብሪካ ውስጥ በመጫንና በማውረድ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ500 የማያንሱ ሰራተኞች መብታችን አልተከበረልንም በሚል የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። አድማው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ በፋብሪካው የተመረቱ የቢራ ምርቶች ሳይሰራጩ ቀርተዋል። ሰራተኞቹን በኮንትራት የሚያሰራቸው ኤዶምያስ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግሉ ኩባንያ የተባለው ድርጅት የተለያዩ የሰብአዊ መብቶችን እንደሚጥስ የሚናገሩት ሰራተኞች፣ ዋናው ፋብሪካ ሰራተኞችን በቀጥታ ቀጥሮ እንዲያሰራቸው ጠይቀዋል። የሃይንከን ባለስልጣናት ችግሩን አይተው መፍትሄ እንደሚሰጡዋቸው ቃል እንደገቡላቸው ሰራተኞች ተናግረዋል። የተመረቱ ምርቶችም ሆኑ ከሽያጭ የተመለሱ የቢራ ሳጥኖች ሳይወርዱ መቅረታቸውን ሰራተኞች ተናግረዋል።
Friday, May 18, 2018
“ባለስልጣናቱ ወረው ለመብላት የተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ ከተሞች በሃላፊነት ቦታ የተቀመጡ የገዥው መንግስት አመራሮች የድሃውን ህብረተሰብ ችግር ከመፍታት ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም የቆሙ በመሆናቸው ፣ሰርተው ሃገሪቱን ከመለወጥ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ማሳደዳቸውን መቀጠላቸው እንዳማረራቸው በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ አሁን በአመራር ላይ ያለው ትውልድ በአመራር ላይ ሲቀመጥ ህዝብን ከማገልገል ይልቅ “በምን ዓይነት መንገድ ገንዘብ ማግኘት” እንደሚችል በማሰብ የሙስና መረብ በመዘርጋት እንደሚጠመዱ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ የበላይ አመራሮችም በጥቅም በመገናኘት የተበደሉትን በቸልታ በመመልከት ህዝብ ሲገፋ ዝምታን መምረጣቸውን በችግርነት ያነሳሉ፡፡ “የደርግ መንግስት ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ በማስተዳደር ወደር የሌለው ነበር” የሚሉት አስተያዬት ሰጪ ለደርግ ውድቀት ምክንያት የሆኑት በበታች አመራሮች የግፍ አሰራር መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡ አስተያዬት ሰጪው አክለውም፣ አሁን በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በአመራርነት የሚያገለግሉ የድርጅቱ ሰዎች “የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለምን አልፈጸማችሁም?”የሚል ጥያቄም ሆነ እርምጃ ባለመወሰዱ ሁሉም አሰራር ‘ልቅነት’ እንደሚታይበት ተናግረዋል። የበላይ አመራሮች ከበታቾቹ ጋር በሚያደርጉት የጥቅም ግንኙነት በመተሳሰር ፣ሰርቶ ከመብላት ይልቅ ‘ወሮ
የሐረሪ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣን ተነሱ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በሃረሪ ክልል የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ጥያቄዎች በአግባቡ አልመለሱም ሃላፊነታቸውንም በአግባቡ አልተወጡም በሚል ሲተቹ የቆዩት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ጨፌ ኦሮምያ ተዛውረዋል። በእርሳቸው ቦታ አቶ በቀለ ተመስገን የሐረሪ ክልል ኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ተመድበዋል። በሃረሪ ክልል የሚኖሩ የኦሮሞና የሌሎች ብሄር ተወላጆች በክልሉ ባለስልጣናት ተደጋጋሚ ጭቆናቸው ሲደርሱባቸው ቢቆዩም ፣ ለችግሩ መፍትሄ የሚሰጥ አካል አልነበረም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦሮሞ ተወላጆች ለጥያቄያቸው መልስ የማይሰጥ ከሆነ አንዳንድ የኦሮሞ ህዝብ በብዛት የሚገኝባቸውን ወረዳዎች ወደ ኦሮምያ ክልል እንዲገቡ ጥያቄዎችን እሰከማንሳት ደርሰው ነበር። በተለይ የኦህዴድ ተወካዩ ም/ል ፕሬዚዳንቱ ከሃብሊ ባለስልጣናት ጋር በመሆን የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ያዳፍናሉ በሚል ሲከሰሱ ቆይቷል። ሃረሪን የህበሊ በፕሬዚዳንትነት ኦህዴድ ደግሞ በም/ል ፕሬዚዳንትነት እንደሚያስተዳድሯት ይታወቃል። አብዛኛዎቹ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የስልጣን ቦታዎች በህብሊ ባለስልጣናትና ደጋፊዎቻቸው መያዛቸውን የክልሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የቤት ማፍረስ ዘመቻን ተከትሎ እስካሁን ከ20 ሺ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ መጠለያ የቀሩ ሲሆን፣ ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ ያደረጉ ነዋሪዎች ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ብዙዎቹ መደብደባቸውንና እስካሁን 2 ሰዎች መገደላቸውንና ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንደኛዋ ቤቷ ሲፈርስ እቃዋን ለማውጣት ስትገባ ቤቱን በላዩዋ ላይ አፍርሰው የገደሏት ሲሆን፣ አንደኛው ደግሞ በጥይት ተመትቶ መሞቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጥያቄያቸውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያቀርቡም መልስ የሚሰጣቸው አላገኙም። ጠ/ሚኒስትሩን ለማናገር ሙከራ አድርገው የሚያቀርባቸው ሰው ማጣታቸውንም ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚያዚያ አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ቀናት ከ5 በላይ የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ለአመታት በክልሉ በኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹት የአማራ ተወላጆች፣ ባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ ከ5 ያላነሱ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ብለዋል። ደባጢ ወረዳ ውስጥ የ14 አመት ታዳጊ የሆነው አበጠር ወርቁ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድቦና ብልቱ ተቆርጦ ከተገኘ በሁዋላ ለህክምና ከፓዊ ወደ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ተወስዷል። በማምቡክ ወረዳ ደግሞ ሁለት የቋሪት ተወላጆች ባልና ሚስት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ሚያዚያ 30 ቀን መቀበራቸውን፣ በአጠቃላይ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ 5 ሰዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው 4 ቱ ሲሞቱ አንዱ በህክምና ላይ ነው። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ባለስልጣናት በታዳጊ ወጣት አበጥር ላይ አሰቃቂ ድርጊት የፈጸሙት ሰዎች መያዛቸውን መግለጹን የአማራ ክልል የመገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የአማራ ተወላጆች ጥቃቱ የተፈጸመባቸው በአማራነታቸው የተወሰደ ነው ወይም ከባህላቸው ጋር በተያያዘ ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ተፈናቃዮች
በኢሕአዴግ የተዋቀሩት ግብረ ሃይሎች ፈረሱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010) በሃገሪቱ መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ በመግባት ስራዎችን እንዲመሩ እና እንዲያስተባብሩ በኢሕአዴግ የተዋቀሩት 12 ግብረ ሃይሎች እንዲፈርሱ መወሰኑ ተገለጸ።
እነዚህ ግብረሃይሎች በአቶ በረከት ስምኦን፣አቶ አባዱላ ገመዳ እና በሕወሃት ሰዎች የሚመሩ እንደነበሩም ታውቋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ የኢሐዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በታህሳስ ወር 2010 በወሰነው መሰረት ተዋቀረ የተባለው ኮሚቴ የካቢኔ ድልድልን ጨምሮ ፣በመንግስት ስራ ውስጥ በግልጽ ጣልቃ የሚገባ እና ሒደቶችን በበላይነት የሚያስተባብር እንደነበርም ተመልክቷል።
ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በአባይ ጉዳይ ላይ ተስማሙ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010)ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በአባይ ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ።
በሶስቱ ሃገራት መካከል ጊዜያዊ ስምምነት በመደረሱም በመካከላቸው የነበረው ውጥረት ረግቧል ተብሏል።
በጋራ ሚንስትሮቻቸው አማካኝነት ስምምነት ላይ የደረሱት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ ጉዳዩን የሚከታተል የሳይንቲስቶች ቡድን ጥናት እንዲያደርግ ነው ።
ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ በርካታ ውይይቶች ሲያደርጉ የነበረ ቢሆንም ስምምነት ለይ ሳይደርሱ ቆይተዋል።
በተለይ ደግሞ ከግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የተወሰነውን ሀይል ውሀ ለመሙላት እንቅስቃሴ ስትጀምር ከግብጽ በኩል ከፈተኛ ተቃውሞ ሲያጋጥማት ቆይቷል።
የመንግስት ሹማምንት የውጭ ጉዞ ሒሳባቸውን አያወራርዱም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010) የመንግስት ሹማምንት ለስራና ለህክምና ወደ ውጭ በሄዱበት ሀገር የተጠቀሙበትን ገንዘብ እንደማያወራርዱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ገንዘቡ ስለማይወራረድም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የኦዲት ጉድለት እንዳለበት አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ችግሩ ስላሳሰባቸው ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል ተብሏል።
የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያልተወራረዱ እና መከፈል ያለባቸው ሒሳቦች እንዳሉ ቢያሳውቅም መጠኑ ግን ይፋ አልተደረገም።
እናም የመንግስት ሹማምንት ለውጭ ሀገር ህክምና እና ለስራ በሄዱበት ሀገር የተጠቀሙበትን ዕዳ በአግባቡ ሊያወራርዱልኝ ባለመቻላቸው በኦዲት ግኝት ተጠያቂ እየሆንኩ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሕዥብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ችግሩ ስላሳሰባቸው ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል ተብሏል።
የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያልተወራረዱ እና መከፈል ያለባቸው ሒሳቦች እንዳሉ ቢያሳውቅም መጠኑ ግን ይፋ አልተደረገም።
እናም የመንግስት ሹማምንት ለውጭ ሀገር ህክምና እና ለስራ በሄዱበት ሀገር የተጠቀሙበትን ዕዳ በአግባቡ ሊያወራርዱልኝ ባለመቻላቸው በኦዲት ግኝት ተጠያቂ እየሆንኩ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሕዥብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡
ለደቡብ ሱዳን ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሊሰጥ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 9/2010) በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለመስጠት መወ ሰኑ ተቃውሞ አስነሳ።
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት በፌደራል መንግስቱ የተደረሰውን ስምምነት ለማስፈጸም ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።
ለደቡብ ሱዳናውያን በጅምላ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጣቸው የተወሰነበት ይፋዊ ምክንያት አልተገለጸም።
የጋምቤላ የመብት ተሟጋቾች ዜግነት የሚሰጣቸው ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥራቸው 400ሺህ እንደሚጠጋ ይገልጻሉ።
የኢትዮጵያውያን አኝዋኮችን ህልውና ለማጥፋት የሚደረገውን ሚስጥራዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያስቆም የመብት ተሟጋቾቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው ዓመት ነበር በኒውዮርክ የተባበሩት መንግስታት ስብስባ ላይ የተገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ችግር ለመፍታት የገንዘብ አቅም ባለመኖሩ በባህሪ፣በቋንቋ ከሚመሳሰሏቸው ጋር መቀላቀል በሚል በስደት ኢትዮጵያ ወስጥ ለሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለመስጠት የተስማሙት።
ለደቡብ ሱዳናውያን በጅምላ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጣቸው የተወሰነበት ይፋዊ ምክንያት አልተገለጸም።
የጋምቤላ የመብት ተሟጋቾች ዜግነት የሚሰጣቸው ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥራቸው 400ሺህ እንደሚጠጋ ይገልጻሉ።
የኢትዮጵያውያን አኝዋኮችን ህልውና ለማጥፋት የሚደረገውን ሚስጥራዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያስቆም የመብት ተሟጋቾቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው ዓመት ነበር በኒውዮርክ የተባበሩት መንግስታት ስብስባ ላይ የተገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ችግር ለመፍታት የገንዘብ አቅም ባለመኖሩ በባህሪ፣በቋንቋ ከሚመሳሰሏቸው ጋር መቀላቀል በሚል በስደት ኢትዮጵያ ወስጥ ለሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለመስጠት የተስማሙት።
Wednesday, May 16, 2018
በሶማሌ ክልል 11 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2010) በሶማሌ ክልል በቀጠለው ተቃውሞ በፊቅ ዞን በሁለት ከተሞች 11 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
ኢሳት የተገደሉት ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል። ፋይል ቡሳ እና ለጋሂዳ በተባሉ ከተሞች ግድያውን የፈጸሙት የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ ታጣቂዎች መሆናቸው ታውቋል።
ልዩ ሃይሉ ከየከተሞቹ እንዲወጣ ከፌደራል መንግስት ትዕዛዝ መሰጠቱን የሚጠቅሱት የኢሳት ምንጮች በህወሃት ጄነራሎች የሚደገፈው የክልሉ ፕሬዝዳንት ትዕዛዙን ተግባራዊ ለማድረግ እንዳልፈለገ ገልጸዋል።
አንደኛ ወሩን እየደፈነ ያለው የሶማሌ ክልሉ ተቃውሞ የንጹሃንን ግድያ እያስከተለ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች በመውጣት ላይ ናቸው።
ባለፈው ሳምንት በቀብሪዳሃር የአንዲት ወጣት ግድያ በክልሉ የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲጠናከር ማድረጉን ነው ለማወቅ የተቻለው።
የአብዲ ዒሌ አስተዳደር ከስልጣን እንዲወርድ በመጠየቅ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ እንደትላንት በርካታ ሰዎች የተገደሉበት ክስተት ከዚህ ቀደም አልተመዘገበም።
በሃና ማሪያም አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው ፈረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/ 2010) በአዲስ አበባ በተለምዶ ሃና ማሪያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ገለጹ።
ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ድንገት በአፍራሽ ግብረሃይል ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች በከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃችውን አመልክተዋል።
ፋይል በሌላ በኩል የስራ ማቆም አድማ ከመቱ አራተኛ ቀናቸውን ያስቆጠሩት የቦሌ ለሚ የኢንንዱስትሪ ዞን ሰራተኞች በፌደራል ፖሊስ ሲዋከቡ መዋላቸው ተገልጿል ።
አዲስ አበባ ሃና ማርያም በዳግም መፈናቀልና የነዋሪው ኋይታ ሰሞኑን ውዝግብ ተነስቷል።
3ሺህ የሚጠጉ የሃና ማርያም ነዋሪዎች መውደቂያ ሳይመቻችላቸው በድንገት በተኙበት ቤታቸው ላያቸው ላይ መፍረሱን በምሬት ይገልጻሉ።
ህጋዊ ለመሆናቸው የሚመሰክሩ ማስረጃዎችን ይዘዋል። መብራትና ውሃ በመንግስት በኩል ሲገባላቸው ህጋዊ ሂደቱን ተከትሎ ለመሆኑ የሚያሳዩ ወረቀቶችን ቢያቀርቡም የሚሰማቸው፡ የሚቀበላቸው አላገኙም።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ አስተዳደር ላለፉት 10 ዓመታት ጎጆ ቀልሰው፣ መብራትና ውሃ ሲጠይቁም ተቀብሎ የሞቀ ኑሮ ጀምረው ልጆች ወልደው ቤተሰብ መስርተው ሲኖሩ አንድም ቀን የህጋዊነት ጥያቄ ሳያነሳባቸው ለባለሀብት ቦታው በተፈለገ ጊዜ ድንገት ማፈናቀሉ ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው በማለት ተፈናቃዮቹ ያማርራሉ።
አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል ተፈቱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2010)በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊና አማካሪ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል ከእስር ተፈቱ፡፡
ከ2006 ጀምሮ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ በማረሚያ ቤት የነበራቸው ባህሪና ሌሎች መሥፈርቶች ታይተው በአመክሮ መፈታታቸው ተነግሯል፡፡
በሙስና ሰበብ የተከሰሱት የብአዲኑ አቶ መላኩ ፋንታ ግን እስካሁን አለተፈቱም። በሙስና ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ከእስር የተፈቱት ከሁለት ሳምንት በፊት ነው፡፡
ለእስር ያባቃቸው ምክንያት ከዚህ ቀደም ይሠሩበት ከነበረው የደህንነት መሥሪያ ቤት ይከፈላቸው ከነበረው ደመወዝ ጋር በማይጣጣም መልኩ በ175 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ባለ ሦስት ፎቅ ሕንፃ ገንብተው በ50 ሺህ ብር አከራይተው በመገኘታቸው ነው።
አለማቀፍ የኡንዲስትሪያል ህብረት የኢትዮጵያ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ዘመቻ ጀመረ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ውስጥ በጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ለማድረግ ኢንዳስትራያል ግሎባል ዩኒየን የተባለው የሰራተኞች ማህበር ዘመቻ ጀምሯል። በእነዚህ እንዱስትሪዎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን በወር 20 ዶላር አካባቢ የሚከፈላቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ሰራተኞቹ የመጨረሻ ክፍያቸው በወር 121 ዶላር ወይም 3 ሺ 373 ብር እንዲሆን ለማድረግ ዘመቻ ጀምሯል። ዘመቻው በቦሌ ለሚ ፣ ሃዋሳና መቀሌ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ማዕከል አድርጓል። 90 በመቶ የሚሆኑ በፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ሴቶች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና የቤት ወጪያቸውን ለመሸፈን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር አይችሉም። እነሱ የሚያመርቱዋቸው ምርቶች በአውሮፓ፣ አሜሪካ እና እስያ ገበያዎች በውድ እየተሸጡ ባለሃብቶቹ ከፍተኛ ገቢ ያገኙባቸዋል። የሰራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ጣሪያ ለማሻሻል የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበርና የአለማቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ከገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ጀስት ስታይል ዘግቧል። በቦሌ ለሚ እንዱስትሪ ፓርክ የሚሰሩ ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ለመጠየቅ ትናንት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ በፖሊሶች ሲዋከቡ አርፍደዋል።
የመቱ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አድማ በማድረግ ላይ ናቸው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ተማሪዎቹ አድማውን የጀመሩት ከጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ተፈናቅለው በመቱ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተደረጉት ተማሪዎች ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ መወሰኑን ተከትሎ ነው። ተማሪዎቹ አስተማማኝ ሰላም በሌለበትና ለህይወታችን ዋስትና በማናገኝበት ሁኔታ ወደ ጅግጅጋ ለመመለስ አንችልም በማለት በማለት ለዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ቢያሳውቁም፣ ባለስልጣናቱ ግን የተማሪዎችን ጥያቄ የሚቀበሉት አልሆነም። በዚህም ተነሳ ዛሬ ሁሉም የግቢው ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ፈደራል ፖሊሶች ወደ ግቢ በመግባት በተማሪዎች ላይ ድብደባ አካሄደዋል። አንድ ተማሪ ግንባሩ ላይ በጽኑ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷል። በርካታ ተማሪዎች መጠነኛ ጉዳት እንደደደረሰባቸው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከጅጅጋ
የአፋር ወጣቶች የጅቡቲን መስመር ዘግተው አመሹ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ወጣቶቹ እርምጃውን የወሰዱት ከህዳር 26 ጀምሮ በደህንነት አባላት ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ እስከዛሬ ድረስ ያለበት ያልታወቀው የሰመራ ዩኒቨርስቲ የሰው ሃይል አስተዳደር ሃላፊ አቶ ሳሊህ ረሺድ እንዲፈታ ለመጠየቅ ነው። ወጣቶቹ በሌሊት የጅቡቲን መንገድ በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስተጓጎል ያደረጉ ሲሆን፣ የክለልዩ ልዩ ሃይል ወደ ስፋረው በመጓዝ መንገዱን አስከፍቷል። ወጣቶች መንገዱን ከዘጉ በሁዋላ በመሰወራቸው ሳይያዙ ቀርተዋል። የሰመራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግቢያቸው ውስጥ አቶ ሳሊህ እንዲፈታ የሚጠይቁ መፈክሮችን በብዛት ለጥፈው በማደራቸው፣ ዘይኑ ጆሃር፣ ከድር አሊና የሰመራ ዩኒቨርስቲ የጥበቃ ሃላፊ መታሰራቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። ወጣቶች ወደ አብዴፓ ጽ/ቤት በመሄድ አቶ ሳሊህ እንዲፈታ የጠየቁ ቢሆንም እስካሁን መልስ አላገኙም። አቶ ሳሊህ ባለፈው ህዳር ወር በአፋር የተከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አስታኮ የተያዙ ናቸው። የህወሃት የመከላከያ አዛዦች በክልሉ ውስጥ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወማቸው ወታደራዊ አዛዦቹ ሲዝቱባቸው እንደነበር ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የአካባቢው ተዋላጆች ገልጸዋል።
ከ100 ሺ በላይ የሚቆጠሩ የጌዲዮ ተወላጆች ከጉጂ ዞን ተፈናቅለው ገደብ ከተማ ገቡ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሳምንታት በፊት በጉጂ ብሄረሰብ አባላትና በጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት መካከል ተነስቶ የነበረው ግጭት ተከትሎ ከ200 ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው የነበረ ቢሆንም፣ ግጭቱን በሽምግልና ለመፍታት በተደረገው ሙከራ ብዙዎቹ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ ተመልሰው ነበር። ይሁን እንጅ ግጭቱ ካለፈው እሁድ ጀምሮ እንደገና በማገርሸቱ ከ 100 ሺ በላይ የጌዲዮ ተወላጆች ዞኑን ለቀው ወደ ገደብ እና ቀረጫ ወረዳዎች በመግባት ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት ጎጥጢ አካባቢ ግጭት እንደነበረ የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ግጭቱን በመፍራት ዛሬም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ገደብ ገብተዋል። የወረዳው አመራሮችም ሆኑ ለጋሽ ድርጅቶች ለተፈናቃዮች በቂ እርዳታ ባለማድረጋቸው አብዛኞቹ ለልመና እየተዳረጉ ነው። በጉጂ እና በጌዲዮ ብሄረሰበች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ከሁለቱም ወገን የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 200ሺህ መድረሱን የመንግስታቱ ድርጅት በቅርቡ አስታውቆ ነበር። ከሳምንታት በፊት ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ መረጃዎች ያሳያሉ። በአሁኑ ግጭት ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ አልታወቀም። ግጭቱን ተከትሎ የኦሮምያ ክልል ልዩ ሃይል አባላት የማረጋጋት እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን፣ ጥቃቱንም የኦነግ አባላት እንዳስነሱትና የተወሰኑት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢናገሩም፣ የጊዲዮ ተወላጆች ግን የሚቀርበውን ምክንያት የሚቀበሉት አልሆነም። ተፈናቃዮቹ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግፊት እንዲያደርጉ ተፈናቃዮች ጠይቀዋል።
Tuesday, May 15, 2018
በባለስልጣናት የውጭ አካውንቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር አብይ ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለተሰበሰቡ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በውጭ አገራት ባንኮች የባንክ ሂሳብ ደብተር ያላቸው ባለስልጣናት ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። የካቢኔ ስብሰባቸውን ከአርብ ወደ ቅዳሜ እንደተለወጠና ጊዜን በስራ ሰዓት በስብሰባ ማባከን እንደሚያስቀር ተናግረዋል። ባለስልጣናት አሰራራቸውን ከህዝብ ሳይደብቁ መረጃ እንዲሰጡ የተናገሩት ዶ/ር አብይ፣ አገሪቱ እስከዛሬ የመጣችበት መንገድ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የማይችል በመሆኑ ሊቀየር ይገባል። ዶ/ር አብይ ለአዲሱ አሰራር አይመጥኑም ያላቸውን ነባር የመንግስት አመራሮች በጡረታ ማሰናበታቸውንም አስታውቀዋል። ከተሰናበቱት መካከል የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ስብሃት ነጋ፣ የፖለሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዶ/ር ካሱ ኢላላ፣ ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም፣ ዕቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት አቶ በለጠ ታፈረ፣ በንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሲ ዕቅድ አፈጻጸምና ክትትል ሃላፊ አቶ ታደሰ ኃይሌ እንዲሁም ፣ከፖሊሲ ምርምር ማዕከል አቶ ማን ያዘዋል መኮንን ተነስተዋል።
ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከእስር ተለቀቁ
የ66 አመት እድሜ ያላቸው ስዊዲናዊውው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከ5 አመታት እስር በኋላ ከቃሊቲ ወህኒ ቤት ወጥተዋል።
በቅሊንጦ ቃጠሎ በግድያ ወንጀል ተከሰው ከነበሩት 38 ሰዎች ክሳቸው እንዲነሳ ሲወሰን አራቱ በነጻ ተለቀው ቀሪዎቹ ደግሞ የፍርድ ሂደታቸው እንዲቀጥል መባሉ ይታወሳል።
በእነመቶ አለቃ ማስረሻ ስጤ መዝገብ አግባው ሰጠኝን ጨምሮ 62 ሰዎች በይቅርታ ከእስር ተለቀዋል።
ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በመጀመሪያ የታሰሩት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ሰበብ ነው።
የልብ ሕክምና ልዩ ሐኪም ሆነው የአዲስ የልብ ሕክምና ሆስፒታልን በመክፈት በርካታ ኢትዮጵያዊንን የረዱት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ያለቀረጥ የሕክምና መሳሪያ አስገብተዋል በሚል በሙስና ተወንጅለው ከ5 አመታት በላይ ታስረዋል።
በጠምባሮ ዞን 10 መምህራን ቆስለው ሆስፒታል ሲገቡ በርካቶች ደግሞ ታሰሩ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን የሚገኙ መምህራን ለልማት በሚል ያለፍላጎታቸው ከወር ደሞዛቸው ላይ መቆረጡን በመቃወማቸው 10 መምህራን በፖሊሶች ድብደባ ተፈጽሞባቸው ሆስፒታል ሲገቡ፣ 20 መምህራን ደግሞ የለምንም ጥያቄ ተስረዋል። በዚህም የተነሳ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ትምህርት ተቋርጧል። መምህራኑ ከዚህ በፊት ለአባይ ግድብ በሚል የወር ደሞዛቸው እንደተቆረጠባቸው ገልጸው በድጋሜ ለከተማ ልማት በሚል እንዲቆረጥባቸው የተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉት አስታውቀው ነበር። ይሁን እንጅ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ መምህራኑ ገንዘብ ከደሞዛቸው ላይ መቆረጡን በማየታቸው አቤቱታቸውን ለክልል ባለስልጣናት አቅርበዋል። የክልሉ ባለስልጣናት ከመምህራኑ ላይ የተቆረጠው ገንዘብ እንዲመለስ ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ የዞኑና የወረዳው ባለስልጣናት ግን ትዕዛዙን እንደማይቀበሉት በማስታወቅ ከሚያዚያ ወር ክፍያ ላይ ገንዘብ ቆርጠዋል አስቀርተዋል። መምህራኑ በተወካዮቻቸው አማካኝነት በድጋሜ ለወረዳው አስተዳዳሪ ጥያቄ ሲያቀርቡ ተደብድበው እስር ቤት እንዲገቡ መደረጋቸውን፣ ካለፈው አርብ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ታስረው እንደሚገኙ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ መምህራን ተናግረዋል። በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መምህራን ህክምና እያገኙ መሆኑን የገለጹት መምህራን፣ በተወሰደው እርምጃ በመምህራኑና በተማሪዎች ላይ የሞራል ውድቀት እንዳሳደረ ተናግረዋል።
የኢንደስትሪያል ዞን ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2010)በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ዞን በሚገኙ ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መምታታቸው ተገለጸ።
አድማ በመምታታቸው ከመንግስት በኩል ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው ነው። ፋይል በሌላ በኩል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ደሞዝ ሳይከፈላቸው ከአንድ ወር በላይ እንደሆናቸው ተገልጿል ።
አዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ዞን ባለፉት ሶስት ቀናት ባልተለመደ መልኩ ውጥረት ታይቶበታል።
በርከት ያሉ በውጭ ባለሀብቶች የሚንቀሳቀሱ ፋብሪካዎች ከወትሮው ተግባራቸው ተገተዋል። ሰራተኞች አድማ ላይ መሆናቸውን ይገልጻሉ።
የኢሳት ወኪል ያነጋገራቸው አንዳንድ ሰራተኞች የደረሰባቸውን ግፍ ሲገልጹ እንባ ይቀድማቸዋል። በአረብ ሀገራት ኢትዮጵያውያን ላይ ከሚደርሰው በደል የከፋ ነው ይላሉ።
ሰራተኞችን ለአድማ ያበቃቸው የደሞዝ ክፍያ እጅግ ያነሰ፣ የኑሮ ደረጃን የማይመጥን፣ ዝቅተኛ ነው በሚል የተነሳው ጥያቄ ቢሆንም በፋብሪካው ባለቤቶች የሚፈጸመው የጉልበት ብዝበዛና የሚፈጸመው በደልም ተጠቅሷል።
Monday, May 14, 2018
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ጋር ተወያየሁ አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ከአቡነ ማትያስ ጋር በእርቅ ጉዳይ ላይ መነጋገርቸውን አስታወቁ።
በውጭ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ሰላም በሚወርድበት ሁኔታ ላይ ከፓትሪያርኩ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ዶክተር አብይ አሕመድ የደርግ ባለስልጣናት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ጭምር ይቅርታ አድርገንላቸው በሃገራቸው መኖር ይኖርባቸዋል ማለታቸውም ተመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ይህንን የተናገሩት ባለፈው ቅዳሜ ከአማራ ክልል ከተለያዩ ዞኖች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር በቤተመንግስት ባደረጉት ውይይት ነው።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከነሱ ጎን መቆማቸውንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቅዳሜ ግንቦት 4/2010 ምሽት ላይ በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት ከአማራ ክልል ተወላጆች ጋር የውውይት መድረክ አካሂደዋል።
በአርበኞች ግንቦት7 የተከሰሱት በፍርድ ቤት ውስጥ መፈክር አሰሙ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር ክስ መዝገብ በአርበኞች ግንቦት 7 ተከሰው ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑ ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ መፈክር አሰምተዋል። የህሊና እስረኞች “ የነፃነት ታጋዮች እንጅ አሸባሪዎች አይደለንም፣ እንደ ማዕከላዊ እስር ቤት ቂሊንጦም ይዘጋ፣ ግፍ ይብቃ፣ ስቃይ ይብቃ” ብለዋል። በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር ክስ መዝገብ ከተከሰሱት 77 ተከሳሾች መካከል ግማሾቹ አምነው በመከራከራቸው ከ15 እስከ 17 አመት ተፈርዶባቸዋል።
በቀብሪ ደሃር እስር ቤት ውስጥ በስቅላት የተገደለችውን የ24 አመቷ ወጣት ሞት ለማስተባበል እየተሞከረ ነው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) ዘመዶችሽ እኔን ሊከሱ ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል በሚል ምክንያት በኢትዮ-ሶማሊ ክልል መሪ በአቶ አብዲ ኢሌ ወታደሮች በቀብሪ ደሃር እስር ቤት ውስጥ ባለፈው ሃሙስ በስቅላት የተገደለችው የ24 አመቷ ወጣት ታሲር ኦማር ፎድን ግድያ ለማስተባበል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ወጣቷ ከተገደለች በሁዋላ ዘመዶቿ ወደ እስር ቤት ተጠርተው ወጣት ታሲር ራሷን እንዳጠፋች እንዲፈርሙ ቢጠየቁም፣ ቤተሰቦቿ ግን አንገቷ አካባቢ የሽቦ ምልክትና ሌሎችንም ሁኔታዎች በማየታቸው አንፈርም ማለታቸውን ምንጮቸ ገልጸዋል። መረጃው የደረሰው የከተማው ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲገልጽ ወታደሮች በህዝቡ ላይ በቀጥታ በመተኮስ ጉዳት አድርሰዋል። ነዋሪዎች በፖሊስ ጣቢያው ላይ ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። እስካሁን ባለው መረጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል። ከ60 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። ወጣቷ በተያዘች በሰዓታት ውስጥ መገደሉዋን የሚገልጹት ምንጮች፣ ድርጊቱ ብዙ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። የአብዲ ኢሌ አገዛዝ ወጣቷን በስውር የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት አባል አድርጎ እያቀረባት ቢሆንም፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የሚቀበሉት አልሆነም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የክልሉ ነዋሪዎች በአብዲ ኢሌ አገዛዝ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው። የህወሃት ድጋፍ እንዳለው የሚነገርለት አብዲ ኢሌ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን መግደሉን፣ በሺዎች የሚቆጠሩትን ማሰሩ፣ ለስደት መዳረጉን እንዲሁም ከ800 ሺ ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆችን ቢያፈናቅልም እስካሁን ለፍርድ አልቀረበም።
ኦዴግ ከሕወሃት መንግስት ጋር የተናጠል ድርድር ጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ከመንግስት ጋር የተናጠል ድርድር ጀመረ።
ቀጣዩን ድርድር በአዲስ አበባ ለማካሄድ የኦዴግ መሪዎች ሰሞኑን አዲስ አበባ እንደሚገቡም ተገልጿል።
በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ድርድሩን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ከመንግስት ከተላኩ ሁለት ልኡካን ጋር መወያየቱን ገልጿል።
የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ እንዳመለከተው ከመንግስት ልኡካን ጋር ድርድሩ የተካሄደው ባለፈው አርብና ቅዳሜ ነበር።
አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ ተበተነ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) በአሜሪካን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ መበተኑ ተገለጸ።
ባለፈው ቅዳሜ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ብሉሚንግተን ከተማ የተጠራውን ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ የተለያዩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች ባሰሙት ተቃውሞ ተቋርጧል።
በተለይም የሶማሌ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ስብሰባ አዳራሽ በመግባት እንዲቋረጥ ማደረጋቸውን በቪዲዮ ተደግፎ ከወጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከስብሰባ አዳራሹ በጓሮ በኩል እንዲሸሹ መደረጉንም ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ያለፈው ቅዳሜ የሚንሶታዋ ቡሉሚንግተን ከተማ ለህወሃት አገዛዝ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ ጥሪ የተደረገበት ስብሰባ ልታስተናግድ ቀጠሮ ተይዞላት ነበር።
ዓላማው በቅርቡ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ካሳ ተክለብርሃን የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመተዋወቅ፣ ስለሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ለመነጋገርና በዚያውም የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ለማድረግ ነበር።
ወደ አንድ ሺህ የሚጠጋ ታዳሚ በተገኘበት ስብሰባ ላይ የክብር እንግዳው አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ቦታቸውን ይዘዋል።
በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት ተባባሰ
(ኢሳት ዲሲ--ግንቦት 6/2010) በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት መባባሱ ተገለጸ
በጤፍ፣ በበርበሬ፣ በዘይት፣ በስኳር፣በቲማቲምና በተለያዩ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ኢሳት ወደ ተለያዩ ከተሞች በመደወል ካሰባሰበው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
በተለይም በከተሞች እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረው መሆኑም ታውቋል።
መንግስት የኑሮ ውድነቱን ነጋዴዎችን ተጠያቂ በማድረግ እንደሚቀጣቸው ሲያስጠነቅቅ ነጋዴዎች ደግሞ ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በመግለጽ የመንግስትን ወቀሳ ያጣጥላሉ።
በሌላ በኩል በዚህ ዓመት መንግስት ለብድር መክፈያ 16 ቢሊየን ብር እንደሚያወጣ ተገልጿል።
የአገሪቱ የብድር ጫና ከመካከለኛ ደረጃ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል ሲል አይኤምኤፍ ባለፈው ሳምንት ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል።
ነጭ ጤፍ በአማካይ ከ2500 ብር እስከ 3000 ብር እየተሸጠ ነው።
ከ500 እስከ 1000 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ነው የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው።
በርበሬ የ70 ብር ጭማሪ ያሳየባቸው ከተሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።
50ብር በአማካኝ ይሸጥ የነበረው በርበሬ 120 ብር ገብቷል።
በቀበሌ ከሚከፋፈለው ሌላ በየመደብሮች የሚሸጠው ዘይት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱም ታውቋል።
5ሊትር ዘይት 365ብር ደርሷል። 15 ብር ይሸጥ የነበረው ፉርኖ ዱቄት የ8ብር ጭማሪ አሳይቷል።
ስኳር ከቀበሌ ውጪ 1ኪሎ በ60ብር እየተሸጠ ሲሆን የ20ብር ጭማሪ እንደታየበትም ለማወቅ ተችሏል።
ቲማቲም የ7ብር ጭማሪ በማሳየት በ17 ብር እየተሸጠ ሲሆን አንድ ሊትር ወተት የወር ኪራይ 750 ብር መግባቱንም ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ስጋ በኪሎ 170 ብር በመሸጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ካሳዩት ምርቶች የሚጠቀስ ሆኗል።
በቆሎም እንዲሁ የ5ብር ጭማሪ እንደታየበት ለማወቅ ተችሏል።
በተለይም በከተሞች እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረው መሆኑም ታውቋል።
መንግስት የኑሮ ውድነቱን ነጋዴዎችን ተጠያቂ በማድረግ እንደሚቀጣቸው ሲያስጠነቅቅ ነጋዴዎች ደግሞ ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በመግለጽ የመንግስትን ወቀሳ ያጣጥላሉ።
በሌላ በኩል በዚህ ዓመት መንግስት ለብድር መክፈያ 16 ቢሊየን ብር እንደሚያወጣ ተገልጿል።
የአገሪቱ የብድር ጫና ከመካከለኛ ደረጃ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል ሲል አይኤምኤፍ ባለፈው ሳምንት ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል።
ነጭ ጤፍ በአማካይ ከ2500 ብር እስከ 3000 ብር እየተሸጠ ነው።
ከ500 እስከ 1000 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ነው የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው።
በርበሬ የ70 ብር ጭማሪ ያሳየባቸው ከተሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።
50ብር በአማካኝ ይሸጥ የነበረው በርበሬ 120 ብር ገብቷል።
በቀበሌ ከሚከፋፈለው ሌላ በየመደብሮች የሚሸጠው ዘይት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱም ታውቋል።
5ሊትር ዘይት 365ብር ደርሷል። 15 ብር ይሸጥ የነበረው ፉርኖ ዱቄት የ8ብር ጭማሪ አሳይቷል።
ስኳር ከቀበሌ ውጪ 1ኪሎ በ60ብር እየተሸጠ ሲሆን የ20ብር ጭማሪ እንደታየበትም ለማወቅ ተችሏል።
ቲማቲም የ7ብር ጭማሪ በማሳየት በ17 ብር እየተሸጠ ሲሆን አንድ ሊትር ወተት የወር ኪራይ 750 ብር መግባቱንም ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ስጋ በኪሎ 170 ብር በመሸጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ካሳዩት ምርቶች የሚጠቀስ ሆኗል።
በቆሎም እንዲሁ የ5ብር ጭማሪ እንደታየበት ለማወቅ ተችሏል።
Friday, May 11, 2018
Tuesday, May 8, 2018
ተከሳሾች በችሎት ውስጥ ተቃውሞ አሰሙ
ተከሳሾቹ የፍርድቤቱን ውሳኔ አልቀበልም በማለታቸው ችሎቱ ተረብሾ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
በችሎቱ የነበሩ ታዳሚዎችን ፌደራል ፖሊስ ሲበትን እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።
በቂሊንጦ ቃጠሎ ተከሰው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የነበሩት 38ቱ እስረኞች በችሎቱ ጥፋተኛ ሲባሉ ውሳኔውን በመቃወማቸው ረብሻ ተፈጥሮ ነበር።
በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት በተገደሉት ሰዎች ምክንያት ከተከሰሱትና እንዲከላከሉ ከተወሰነባቸው መካከል 34ኛ ተከሳሽ ፍጹም ጌታቸው የመረረ ተቃውሞ ማሰማቱ ተገልጿል።
የታገዱት የአየር ሃይል አብራሪዎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠየቁ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተካሄዱትን ተቃውሞዎች ተከትሎ ከ2 አመት ላላነሱ ጊዜ ከስራ የታገዱ የአማራ እና የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የአየር ሃይል አብራሪዎች ለምን እንደታገዱ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። በምስራቅ አየር ምድብና በማእከላዊ አየር ምድብ ያገለገሉ የነበሩት አብራሪዎች “ ጥፋታችን ምንድነው? ስራ እንድናቆም የታዘዝነውስ ለምንድነው?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። የስርዓቱ ደጋፊዎች የሆኑት የትግራይ ተወላጆች ሰላም ለማስከበር በሚል ወደተለያዩ አካባቢዎች በመጓዝ ከፍተኛ ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን፣ ሌሎች ግን በብሄራቸው ብቻ ጥቅማጥቆምችን እንዲያገኙ እንደማይደረግ ምንጮች ገልጸዋል። ባለፉት ሁለት አመታት በርካታ የአየር ሃይል አብራሪዎች ከስራቸው ታገደዋል። ሌሎች ደግሞ ስርዓቱን አናገለግልም በማለት ከአገር ወጥተዋል።
በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ከተከሰሱት የህሊና እስረኞች መካከል ብዙዎቹ በመደበኛ ወንጀል እንዲካላከሉ ተበየነ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ታስረው አሁንም ድረስ ጉዳያቸውን በፍርድ እየታየ ከሚገኙት መካከል መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ፣ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን፣ አግባው ሰጠኝን፣ ወልዴ ሞቱማን፣ ሚስባህ ከድርን፣ ፍቅረማርያም አስማማውን፣ ደረጀ መርጋንና፣ ከበደ ጨመዳን፣ ጨምሮ 28 ተከሳሾችን አመፅ በማደራጀት፣ በመምራትና በመሳተፍ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንቀፅ 464/2/ሀ፣ ለ፣ 461/ሀ እና 494 /2 ስር እንዲከላከሉ በይኖባቸዋል። ከተከሳሾች መካከል ጌታቸር እሼቴ፣ ቶፊቅ ሽኩር፣ ሸምሱ ሰኢድ እና ፍፁም ጌታቸው በተገደሉት ሰዎች ነፍስ እንዲከላከሉ ሲበየንባቸው፣ አብዱሉሂ አልዩ፣ እስማኤል በቀለ፣ ቃሲም ገንቦ፣ አንጋው ተገኘ፣ ሰይፈ ግርማ፣ ዲንሳ ፉፉ፣ ናስር ደጉና ናኦል ሻሜሮ በነፃ እንዲሰናበቱ ተበይኗል። 34ኛ ተከሳሽ ፍጹም ጌታቸው “በቃጠሎው የተገደለውኮ አብሮ አደጌ፣ የሰፈሬ ልጅ፣ ጓደኛዬ ነው። አባቴ የእሱን ሞት ሰምቶ በልብ ድካም ነው የሞተው” ብሎ ተናግሯል። ተከሳሾች የተሰጠውን ብይን እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። ወላጆች በውሳኔው ተባስጭተው ተቃውሞቸውን በለቅሶ ሲቃወሙ የፌደራል ፖሊሶች በጠመንጃ በማስፈራራት ችሎቱን በትነውታል።
በሶማሊ ክልል ጠንካራ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ አገዛዝ በመቃወም በሶማሊ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ በመምጣት ላይ ነው። በዛሬው እለት ከዚህ በፊት ተቃውሞ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ጠንካራ ተቃውሞ ሲካሄድ ውሎአል። የአብዲ ኢሌ ተጣቂዎች ተቃውሞአቸውን በሚገልጹ ዜጎች ላይ በወሰዱት እርምጃም ሰዎች ተገድለዋል። ቶጎ ወጀሌንና ጂግጂጋን ከመሃል አገር ጋር የሚያገናኘው መንገድም ተዘግቷል። በጅግጅጋ ዞን በቶጎ ወጀሌ በሚካሄደው ተቃውሞ የአብዲ ኢሌ ልዩ ሚሊሺያዎች በወሰዱት እርምጃ እስካሁን በትንሹ 3 ሰዎች ሲገደሉ ከ20 በላይ ደግሞ ቆስለዋል። ተቃውሞው በአይሻኣ፣ በሃሮረይስ፣ በቢኪ እና በጎብየር ከተሞች ተካሂዷል። ህዝቡ አብዲ ኢሌ ስልጣኑን ለቆ ለፍርድ እንዲቀርብ ጥያቄ እያቀረበ ሲሆን፣ የአብዲ ኢሌ አገዛዝ ተቃውሞውን በሃይል ለማፈን ጥረት እያደረገ ነው። የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ አሌ በእርሱ ላይ የሚካሄደውን ተቃውሞ የአቶ ለማ መገርሳና የዶ/ር አብይ አህመድ ቡድን ከጀርባ ሆነው እንደሚመሩት እየገለጸ ነው። በክልሉ ውስጥ የዶ/ር አብይ ፎቶ ግራፍ እንዲወርድ ወይም እንዲቀቀድ መደረጉን የሚገልጹት ምንጮች፣አቶ አብዲ” ኦሮምያ ክልል
በአዶላ የአጋዚ ወታደሮች እርምጃ መውሰድ ጀመሩ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሳምንት የቀጠለውን የምስራቅ ጉጂ ዞን ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች በህዝቡ ላይ በመተኮስ እርምጃ የወሰዱ ሲሆን፣ እስካሁን ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ በርካቶችም ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የኦህአዴድ ባለስልጣናት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውንና በአጋዚ ወታደሮችና በህዝቡ መካከል የሚካሄደው ፍልሚያ መቀጠሉን ተናግረዋል። ህዝቡ በድንጋይ ራሱን ለመከላከል ሲሞክር፣ አጋዚዎች ጥይት በቀጥታ በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አካባቢው ወደ ጦር ቀጠናነት መቀየሩን፣ ወጣቱ ማንኛውንም የህይወት መስዋትነት ለመክፈል ተዘጋጅቶ ትግል እያደረገ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ መብቶቻቸውን የጠየቁ ዜጎች ከእንግዲህ እንደማይገደሉ ቢናገሩም፣ የዛሬው ግድያ ንግግራቸውን በአየር ላይ አስቀርቶታል። በሻኪሶም ህዝቡ የንግድ ድርጅቶችን በመዝጋት፣ መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋትና ምንም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይኖር በማድረግ ተቃውሞውን እየገለጸ ነው። የተቃውሞው መነሻ ለሚድሮክ ወርቅ የተሰጠውን የ10 አመት ተጨማሪ የወርቅ ማውጣት ፈቃድ በመቃወም ቢሆንም፣ ኦሮምያ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት እስካሁን ህዝቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ አልሰጡም። የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት ሼክ ሙሃመድ ሁሴን አላሙዲን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ለወራት በሳውድ አረቢያ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ።
Wednesday, May 2, 2018
የወልዋሎ ቡድን ተጫዋቾች ከፈጸሙባቸው ድብደባ ይልቅ የሰደቧቸው ዘር ላይ ያነጣጠረ ስድብ ይበልጥ እንዳመማቸው ኢንተርናሽናል አልቢትር ኢያሱ ፈንቴ ተናገሩ።
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ ባደረጉት ንግግር ተጫዋቾቹ ሲደበድቧቸው ከአፋቸው ይወጣ የነበረውን ዘር ላይ ያነጣጠር ስድብ ለመግለጽ እንደማይፈልጉ በመጥቀስ “በምን ቋንቋ መናገር እንደምችል አልገባኝም። በእግርኳስ ቋንቋ ላውራ ብል ፖለቲካ ይባልብኛል” ብለዋል። “እኔ በወቅቱ ብቸኝነት ነው የተሰማኝ፤ ሁኔታው ሲፈጠር ሁሉም ቆሞ ከመመልከት ውጪ ሊገላግል የመጣ አንድም ሰው የለም።” ያሉት ዳኛ ኢያሱ ፋንታ፣ እገዛ ለማድረግ ሲጥር የነበረው አቶ ፍጹም ገብረማርያም ብቻ ነው”ሲሉ ተናግረዋል። “ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰው እንዴት ስደበደብ ቆሞ ይመለከታል?”ያሉት አርቢትሩ፣ ሰው የሰው መደብደብ የማይሰማው ከሆነ በጣም የሚያሳዝን ጊዜ ላይ ደርሰናል ማለት ነው ብለዋል። ” በብሔሬ ምክንያት ጨዋታውን ማጫወት የለበትም ከተባለ መነሳት ነበረብኝ” ያሉት አርቢትር ኢያሱ፣ ከጨዋታው አስቀድሞ ምንም ነገር ሳይነሳ ሜዳ ውስጥ ሢሰሙ የነበሩት ነገሮች በሙሉ ግን ዘግናኝ ነበሩ” ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም፦”ጨዋተው በሰላም እንዲያልቅ በሚል ብዙ ነገር ተቋቁሜ ነበር እስከ ድብደባው ድረስ የዘለቅኩት” ሲሉ በዙ ስድብና ዘለፋ እንደደረሰባቸውም ጠቁመዋል። አርቢትር ኢያሱ በመጨረሻም “ከዚህ በኋላ በዳኝነት እቀጥላለሁ›ወይስ አልቀጥልም? የሚለውን ፈጣሪ ነው የሚያውቀው ” ማለታቸውን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመለክታል። የወልዋሎ ቡድን ጠጫዋቾች እና የቡድን መሪ የዳኛን ውሳኔ በመቃወም አርቢትርን እስከመደብደብ የደረሱበት አሳፋሪ ድርጊት በቢቢሲ እና በሌሎች ዓለማቀፍ ሚዲያዎችም ሰፊ ሽፋን አግኝቷል።
አቶ አብዲ ኢሌ “ ኦሮሞዎች ጠላቶቻችን ናቸው” ሲሉ ፈረጁ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢትዮ-ሶማሊ ክልል መሪ አቶ አብዲ ኢሌ “ ኦሮሞዎች ጠላቶቻችን ናቸው” ሲል በጅጅጋ ከተማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ለተጠሩ ለክልሉ ሽማግሌዎች ተናግረዋል። በከፍተኛ የስሜት መረበሽ ውስጥ ሆነው ንግግር ያደረጉት አቶ አብዲ “ ዶ/ር አብይ እና ሌሎች ወደ ጅግጅጋ መጥተው የነበሩት ኦሮሞዎች ውሸታሞች ናቸው” ብለዋቸዋል። “በእኛ ላይ ስውር ጦርነት ከፍተውብናል” የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፣ “ከኦሮሞዎች ጋር ለመዋጋት ዝግጅት ማድረግ አለብን” ሲሉ አክለዋል። “በአንድ በኩል ለሰላም ዝግጁ ነን ይላሉ፣ በሌላ በኩል በክልሉ መንግስትና ህዝብ ላይ ጦርነት ለማወጅ በስውር ያሴራሉ” የሚሉት አቶ አብዲ ኢሌ ፣ የዶ/ር አብይን መንግስት እንደማያምኑትና የክልሉ ህዝብም ድጋፉን እንዳይሰጣቸው ጠይቀዋል። በቅርቡ እርሳቸውን በመቃወም በክልሉ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች የሴራው አካል ማሳያ መሆናቸውን የሚገልጹት አቶ አብዲ፣ ህዝቡ በብዛት ወደ አደባባይ እየወጣ ለክልሉ መንግስት ድጋፉን እንዲሰጥ ጠይቀዋል። እንደ ኦሮሞወች ሁሉ የሶማሊ ቄሮዎች መፈጠር እንዳለባቸውና ክልሉም በዚህ መንገድ የሶማሊ ቄሮዎችን እንዲያደራጅ አቶ አብዲ ለወረዳ አመራሮች ትእዛዝ እንደሚሰጡ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች “ልጆቻቸውን ይዘው በረሃ ለበረሃ መንከራተቱ እንዲያበቃላቸው” ጠየቁ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) ከተለያዩ የአማራ ክልል የገጠር አካባቢዎች ተጉዘው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእርሻ እና በሌሎችም ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች፣ በክልሉ ውስጥ የሚደርስባቸው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊ እየሆነ መምጣቱን ኢሳት ያነጋገራቸው የክልሉ ተወላጆች ገልጸዋል። “በአንዳንድ ወረዳዎች ብቻ በያመቱ ከ30-50 የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች በሰበብ አስባቡ ይገደላሉ” የሚሉት ነዋሪዎች፣ ችግሮቹን ሁሉ እየተቋቋሙ በክልሉ መቆየትን እንደመረጡ የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ “ ካራ እንደተሳለላት በግ ጊዜያችንን እየጠበቅን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ይናገራሉ። ህዝቡ እየተጎዳ ቢሆንም፣ ወደ ክልላችን መመለስ እንኳን አንችልንም የሚሉት የአማራ ተወላጆች፣ በክልላችን፣ “ እንኳንስ አርሰን ልንበላ የምንቀመጥበት መሬት እንኳን እያጣን ነው” ይላሉ “የአማራ ህዝብ መቀመጫ አላገኘም፣ ሁሌም ተሳዳጅ ሆኗል።
በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ግጭት ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010)በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ።
የፌደራል ፖሊስ ወደ ግቢ በመግባት በርካታ ተማሪዎችን በመደብደብ ጉዳት ማደረሱንም ለማወቅ ተችሏል።
የግለሰቦች ጸብ መነሻ እንደሆነ ቢገለጽም ግጭቱ ወደ እርስ በእርስ ተቀይሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቆም ማድረጉን ነው የኢሳት ምንጮች የገለጹት።
ባለፈው ሳምንት ከግቢው እንዲወጣ በተማሪዎች ተቃውሞ የደረሰበት የፌደራል ፖሊስ የዛሬውን ግጭት ተከትሎ ግቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩም ተገልጿል።
ተማሪዎች ከግቢያቸው እንዳይወጡ ተደርገዋል። የታሰሩም እንዳለ እየተነገረ ነው። የዛሬው ግጭት መነሻ የግለሰቦች ጸብ መሆኑን የኢሳት ምንጮች መረጃ ያመለክታል።
በአንዲት የዩኒቨርቲው ሰራተኛና በተማሪ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ሰፍቶ ወደ አጠቃላይ ግጭት የተቀየረ መሆኑን ነው ለመረዳት የተቻለው።
የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በማያባራ ግጭት ውስጥ ከገባ አንድ ወር እንደሆነው የሚገልጹት የኢሳት ምንጮች የግለሰቦች ጸብ ጭምር ወደ ከረረ ግጭት እየተለወጠ የመማር ማስተማር ሂደቱን አስተጓጉሏል ይላሉ።
ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች እየታፈኑ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010)ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች በደህንነቶች በመታፈን ላይ መሆናቸው ታወቀ።
ከ500 በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሆኑም የኢሳት ወኪል ያነጋገራቸው ገልጸዋል። በተለይ ከተፈናቃዮች መካከል ወንዶች እየተለዩ በመታፈን ላይ መሆናቸው ታውቋል።
ከህዝብ እንዳይገናኙ በህወሃት ደህንነቶችና በኮማንድ ፖስቱ ወታደሮች ወከባ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል።
ህወሀት የሰገሰጋቸውና በተፈናቃይ ስም የተደባለቁ የደህንነት ሰራተኞች ወደ መጣንበት እንመለስ የሚል ቅስቀሳ የጀመሩ በመሆኑ ተፈናቃዩ እንዳይታለል ጥሪ ተደርጓል።
ተፈናቃዮቹ የሚላስ የሚቀመስ በማጣታቸው ወደ ልመና መሰማራታቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወደ ባህር ዳር የገቡትና በቀናት ልዩነት የደረሱት ከ500 በላይ የአማራ ተወላጆች የድረሱልን ጥሪ ማቅረባቸውን ነው የኢሳት ወኪል በስፍራው ተገኝቶ ካነጋገራቸው ተፈናቃዮች መረዳት የቻለው።
እንደወኪላችን ዘገባ ከሆነ በቤንሻንጉል ጉምዝ የወረዳ አመራሮች ከጀርባ እንዳሉበትና የክልሉ ፖሊስ ድጋፍ ሰጥቶበታል በተባለው መፈናቀል ቀዬ መንደራቸውን ትተው ወደ ባህርዳር የሸሹት የአማራ ክልል ተወላጆች የወገን እጅ እየጠበቁ ነው።
በጉጂ ዞን የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010) የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ኩባንያ ኮንትራት መራዘሙ ያስቆጣቸው የጉጂ ዞን ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ለሶስተኛ ቀን መቀጠላቸው ታወቀ ።
በሃረቃሎ ዘጠኝ የካቢኔ አባላት በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ዛሬ በበርካታ የዞኑ አካባቢዎች ተቃውሞው ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ መሆኑም ተመልክቷል። በተቃውሞ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ሳይቀር መሳተፋቸው እየተነገረ ነው።
በአንዳንድ አካባቢዎችም የአገዛዙ ታጣቂዎች ህዝቡ ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማንኛውም የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የአካባቢውን ነዋሪ መጉዳት የለበትም ሲል ቅሬታውን ገልጿል። ካለፉት ሁለት ቀናት ይበልጥ የዛሬው ተቃውሞ ጠንካራ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።
በተለይ በሻኪሶ የዛሬው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች የተጎዱበት መሆኑ እየተነገረ ነው።
መጋቢት 20 ኮንትራቱ ያበቃው የሜድሮክ የወርቅ ኩባንያ ለተጨማሪ 10 ዓመት እንዳይራዘም በህዝብ ዘንድ የቀረበውን ተቃውሞ ወደ ጎን በማድረግ በህወሃት የሚመራው አገዛዝ ለኩባንያው ዳግም ፍቃዱን ማደሱ የፈጠረው ተቃውሞ በጉጂ ሁለቱም ዞኖች ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄን አስከትሏል።
ሕወሃት ኤርትራ ጥቃት ልትፈጽምብን ትችላለች የሚል ስጋት ውስጥ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች ኤርትራ ጥቃት ልትፈጽምብን ትችላለች የሚል ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ።
ጦርነቱ ቢነሳ በጦርነቱ አፍራሽ ሚና ሊኖራቸው ይችላሉ የተባሉ በርካታ መኮንኖች እየተመነጠሩ በመታሰር ላይ መሆናቸው ታውቋል።
ጥቂት ወታደሮችና የበታች ሹሞችም በተመሳሳይ መታሰራቸው ታውቋል።
የሰራዊቱን መኮንኖች እየመነጠሩ የማሰሩ ርምጃ የተከተለው በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተለይም በአማራ ክልል ከወልቃይት ጋር በተያያዘ ያልተጠበቀ ተቃውሞና አመጽ ሊከተል ይችላል በሚል ስጋት ጭምር መሆኑን የመከላከያ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
በዚህም የለውጥ አቀንቃኝ ተብለው የሚታመኑ እንዲሁም ለሕወሃት የጦር አዛዦች ቀና አመለካከት የላቸውም ተብለው የሚጠረጠሩትን ማሰር የተጀመረው ከወራቶች በፊት መሆኑ ታውቋል።
በአሁኑ ሰአት ደግሞ የእስር ርምጃው ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱ ተገልጿል።
Subscribe to:
Posts (Atom)