(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 29/2010) ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ3ሺህ በላይ የሚሆኑ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው ጠየቁ።
ህጻናት ልጆቻችን በረሃብ እየተቀጡ ነው፣ ጸሃይና ዝናብ እየተፈራረቁ ለከፍተኛ የጤና ችግር ተጋልጠናል የሚሉት የሃና ማርያም ተፈናቃዮች የሚሰማን የመንግስት አካል ባለመኖሩ የኢትዮጵያ ህዝብ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉ ተማጽነዋል።
በሁለት ቀናት ውስጥ መጥተን እናያችኋላን ተብለን እየጠብቅን ነው፡፡
ስራ የለንም፣ ልጆቻችን ከትምህርትም ከምግብም ከራቁ ቆይተዋል ሲሉ ምሬታቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment