Friday, June 1, 2018

ከቄለም ወረዳ ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠየቁ

(ኢሳት ዜና ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) በደርግ ዘመን በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ወረዳ ሰፍረው የነበሩ ከ400 በላይ የአማራ ተወላጆች በአካባቢው ባለስልጣናት ጫና እንዲፈናቀሉ መደረጉን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ቆቦ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ ሁሉም ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። ተፈናቃዮች እንደሚሉት ካለፉት 7 ወራት ወዲህ የአካባቢው ወጣቶች፣ ፖሊሶችና ሌሎች የደህንነት አባላት አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ ብለው ባዘዙዋቸው መሰረት መውጣታቸውን ተናግረዋል። ከቡኖ በደሌ እንዲሁም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ባህርዳር ከተማ ውስጥ ሰፍረው ይገኛሉ። የለማ አስተዳደር ማንም ሰው ከኦሮምያ ክልል መፈናቀል እንደለሌለበት በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል።

No comments:

Post a Comment