(ኢሳት ዜና የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ሪፖርተር ጋዜጣ በቅርቡ በርካታ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቁጠባቸውን እያቋረጡ ነው በሚል የሰራው ዘገባ የአገዛዙ ባለስልጣናትን በእጅጉ አስቆጥቷል። ጋዜጣው ከ900 ሺ ዜጎች በላይ ቤት ፈላጊዎች የባንክ አካውንት ከፍተው ቁጠባ ቢጀምሩም፣ 624 ሺ ተመዝጋቢዎች ቁጠባ ማቆማቸውን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ዶ/ር አምባቸው መኰንንን በመጥቀስ ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል። ዶ/ር አምባቸው ቁጠባቸውን በትክክል እየቆጠቡ የሚገኙት ደግሞ ከ100 ሺሕ አይበልጡም በማለት መናገራቸው፣ ይህን ተከትሎም ገንዘቡን ለማውጣት የሚፍለገው ቆጣቢ በመጨመሩ እና በባንኩ ህልውና ላይ ስጋት በማሳደሩ፣ ዶ/ር አምባቸው ይቅርታ እንዲጠይቁና መረጃው እንዲስተባበል ትዕዛዝ መተላለፉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ባለፈው ሰኞ የመንግስት የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞችና የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ “በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች/የኮንዶሚኒየም/ ቤት ተመዝጋቢዎች ቁጠባቸውን እያቋረጡ ነው” በሚል የተዘጋጀው የሪፖርተር ዜና የሚኒስትሩ ዶ/ር አምባቸው የተሳሳተ መግለጫ ወይም የአፍ ወለምታ ስለሆነ፣ ይሄን የተዛባና የተሳሳተ መረጃ ራሱ የሚኒስትር ጽ/ቤቱ ሚኒስትር ዶ/ር አምባቸው ቀርበው ማረሚያ ወይም ይቅርታ እንዲጠይቁ እንዲሁም መረጃውም የውጭ ጠላቶች መጠቀሚያ እየሆነ በመሆኑ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ተነግሯቸዋል። የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች “እንዴት ሚንስትሩ ተሳሳቱ እንበል?” በሚል በመመሪያው ግራ ተጋብተው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሰሞኑን በርካታ ዜጎች ወደ ንግድ ባንክ በመሄድ ገንዘባቸውን ለማውጣት
No comments:
Post a Comment