የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ጥያቄ ያቀረቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተቀባይነት አለማግኘታቸውንም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል። ከሳምንታተ በፊት በዩ ኤስ አሜሪካ በዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ላይ የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊታወጅ ነው የሚለውን ተባራሪ ወሬ አስተባብለው ፣የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንደማይታወጅ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣናት ማረጋገጫ ሰተው ነበር። ሆኖም ርሳቸው ወደ ኢትዮጵያ ሳይመለሱ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በኢትዮጵያ ይፋ ሆነ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተርወርቅነህ ገበየሁ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ አዋጁ የታወጀበት አሳማኝ የሆነ ምክንያት ስላለ መጥቼ ላስረዳ ሲሉ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውንም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ይገልጻሉ። ሆኖም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ወደ አሜሪካ መጓዝ አስፈላጊነት አልተቀበሉትም። በአፍሪካ ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ የተጓዙ የአሜሪካ ባለስልጣናት ስላሉ እነርሱ በኢትዮጵያ በኩል ሊያልፉ ስለሚችሉ አሳማኙን ምክንያት ለነርሱ
አስረዷቸው የሚል ምላሽ ተሰቷቸዋል። ልኡካኑ አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ቀጠሮ መጠየቃቸውን የሚገልጹት የዲፕሎማቲክ ምንጮች ፥በቀጠሯቸው መሰረት ከዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ሲገናኙ ፡እሳቸውም በጉዳዩ ላይ ይበልጥ ማብራሪያ ከሚሰጡ ባለስልጣናት ጋር ላገናኛችሁ በሚል ልኡካኑን ወደ ቀድሞዎቹ የሕወሃት መሪዎች እንደወሰዷቸው ከዲፕሎማቲክ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ለልኡካኑ ማብራሪያ ለመስጠት የተገኙት የሐወሃት መሪዎች አቶ ስብሃት ነጋ፣አቶ ስዩም መስፍን እና አቶ አባይ ጸሃዬ መሆናቸውም ተመልክቷል። የሕወሃት መሪዎቹ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሃገሪቱ ለወታደራዊ አገዛዝ አንዳትጋለጥ ሲባል የተወሰደ ርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ልንወደስ እንጂ ነቀፌታ ሊቀርብብን አይገባም ማለታቸውም ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ምክንያት በማድረግ ወታደሩ ሲቪል አስተዳደሩን አግዶ ወደ ስልጣን ለመውጣት በመወሰኑ ይህንን ለመከላከል ሲባል ከወታደሩ ጋር በመደራደር አዋጁ እንዲወጣ መወሰኑን አብራርተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት እያሉ ይፋዊ ስልጣን የሌላቸው የህወሃት መሪዎች ማብራሪያ የሰጡበት ምክንያት ለአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳልተገለጸላቸውም መረዳት ተችሏል። የነ አቶ ስብሃት ማብራሪያ በአሜሪካ መንግስት ተዓማኒ ባለመሆኑ እና ተቀባይነት ባለማግኘቱ አሜሪካ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንዲነሳ ወይንም እንዲሰረዝ የምታደርገውን ግፊት መቀጠሏንም መረዳት ተችሏል። በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሳምንቱ መጀመሪያ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በሰጠው መግለጫ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንዲነሳ ያወጣውን መግለጫ የሚያስለውጠው ምክንያት አለመኖሩን ገልጿል።አዋጁ እንዲነሳም በድጋሚ ጠይቋል ፤

No comments:
Post a Comment