Tuesday, February 16, 2016

በምዕራብ አርሲ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ተዛምቶ ከፍተኛ ግጭት ተካሄደ

ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
በምዕራብ አርሲ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አጎራባች ቀበሌዎች መዛመቱንና በአካባቢው ከፍተኛ ግጭት በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞችን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ማክሰኞ ዘግቧል።
...
ይኸው ተቃውሞ በሻላ፣ ሲራሮ፣ አጄና፣ ሻሸመኔ ከተማ ተዛምቶ የሚገኝ ሲሆን፣ የፀጥታ ሃይሎችም ከነዋሪዎች ጋር ግብግብ ውስጥ መሆናቸውን መጽሄቱ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አቅርቧል።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃዎች በሻሸመኔ ከተማና በአቅራቢያዋ ባሉ አካባቢዎች በትንሹ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች አስረድተዋል።
በሻሸመኔ ከተማ ከሞቱ ሁለት ሰዎች መካከል አንደኛዋ እድሜዋ በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኝ ነፍሰጡር መሆኗን የከተማዋ ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎም በሻሸመኔ ከተማ የመንግስትና የግል ተቋማት ተዘግተው የሚገኙ ሲሆን፣ በከተማዋ ወደተለያዩ አካባቢዎች የሚወስዱ መንገደኞችም መዘጋታቸውን ለመረዳት ተችሏል።
የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ሃይሎችም በሻሸመኔ ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በመስፈር ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል።
አካባቢው የተረጋጋ ባለመሆኑ የሟቾች ቁጥር በአግባቡ ማወቅ እንዳልተቻለ የሚናገሩት ነዋሪዎች በርካታ ሰዎችም ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው በአካባቢው የተፈጠረውን ግጭት ምክንያት ለማወቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ማክሰኞ ምሽት አስታውቀዋል።

No comments:

Post a Comment