Tuesday, February 16, 2016

የአርቲስት አድማሱ ብርሃኑ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
የታዋቂው የኪነጥበብ ሰው አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ። ለ36 ዓመታት ያህል በኪነጥበቡ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጉ የሚነገርለት አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ በተለይ በኦሮምኛ የኪነጥበብ ስራዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነት አትርፏል።
...
“አባ ለታ” በሚል ብዙዎች የሚጠሩት አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ያለፈው ሰኞ የካቲት 7 ፥ 2008 ዓ ም ሲሆን፣ የቀብር ስነስርዓቱ ማክሰኞ የካቲት 8 ፥ 2008 በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ሐምሌ 26 ቀን 1948 አም ከአባቱ አቶ ብርሃኑ መገርሳና ከእናቱ ከ ወ/ሮ ዘነበች ጎሹ በወለጋ ክፍለሃገር በቢላ ወረዳ የተወለደው አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ፣ ለ36 አመታት በተለያዩ የመድረክ ስራዎች እንዲሁም በፊልሞች የኪነጥበብ ስራዎችን ለኢትዮጵያውያን ሲያበረክት ቆይቷል።
የሶስት ሴቶችና የሁለት ወንድ ልጆች አባት የነበረው አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ ከዚህ አለም በሞት የተሰናበተው በተወለደ በ60 አመቱ ነው። ኢሳት ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆቹና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

No comments:

Post a Comment