የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ወደ ክልሉ በማምራት የኑዌርና የአኝዋክ የአገር ሽማግሌዎችን በማነጋጋር ላይ ቢሆኑም፣ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
ሁለቱም ብሄረሰቦች በሰፈሩባቸው ኣካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደማይቻልና፣ አንዱ ብሄረሰብ ወደ ሌላው አካባቢ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ እንደሚገደል ምንጮች ተናግረዋል።
የክልሉ አስተዳደር አሁንም ወደ ቦታው አልተመለሰም። ክልሉን የሚያስተዳድሩት የመከላከያ ሰራዊተት አዛዦች ሲሆኑ ፣ የሁለቱ ፕሬዚዳንቶች እጣ ፋንታ አልታወቀም። የክልሉ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች መሳሪያቸውን እንዲፈቱ ከተደረገ በሁዋላ፣ ተሃድሶ በሚል እየተገደመገሙ ነው። ከግምገማው በሁዋላ እርምጃ የሚወሰድባቸው የልዩ ሃይል አባላትማ የክልሉ ባለስልጣናት ...ይታወቃሉ።
ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በአበቦና በኢታንግ 5 የንዌር ተወላጆች መገደላቸው ታውቋል። አኝዋኮች በገዢው ፓርቲ የሚካሄደውን የሽምግልና ጥረት እንዳልወደዱት ምንጮች አክለው ገልጸዋል። መንግስት አንዱን ብሄረሰብ በመደገፍ በሌላው ላይ እንዲነሳ እያደረገነው በማለት ክስ ያቀርባሉ።
ደቡብ ሱዳናውያን ከክልሉ የማስወጣቱ ስራም እንደቀጠለ ነው።

No comments:
Post a Comment