ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፋር የታየውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ 70 አርብቶአደሮች ከብቶቻቸውን ወደ ስኳር እርሻ ልማት ውስጥ አስገብተዋል በሚል ተይዘው ። ከታሰሩት መካከል አንደኛው ሰው በድብደባ መሞቱን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ሟቹ ሰዲቅ ዳውድ ለመብቱ የሚታገል ሰው እንደነበር የሚናገሩት ምንጮች፣ ይህንን ተከትሎ ውጥረት መንገሱንና መንግስት ኤሌክትሪክ ነው የገደለው በማለት ህዝቡን ለማረጋጋት እየሞከረ ነው።
"አርሶደሮቹ መሬታቸውን ተቀምተዋል፤ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሄደው ከብቶቻቸውን እንዳይመግቡ እንኳን አካባቢው ድርቅ ነው፣ በዚህ ተስፋ በመቁረጥ ከብቶቻቸውን ወደ ስኳር እርሻ ልማቱ ማስገባታቸውን" የአፋር ሰብአዊ መብቶች ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ ተናግረዋል።
"አርሶደሮቹ መሬታቸውን ተቀምተዋል፤ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሄደው ከብቶቻቸውን እንዳይመግቡ እንኳን አካባቢው ድርቅ ነው፣ በዚህ ተስፋ በመቁረጥ ከብቶቻቸውን ወደ ስኳር እርሻ ልማቱ ማስገባታቸውን" የአፋር ሰብአዊ መብቶች ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment