ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንጐ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦገስቲን ማታታ ፖኖዮ ካይሮን ሲጎበኙ ከግብጹ አቻቸው ከሸሪፍ ኢስማኢል ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፤ ከአባይ ወንዝ የምታገኘው ድርሻ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያመጣብኛል ብላ መስጋቷ አግባብ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ለዚህ የካይሮ አቋም ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡
የኮንጎው ጠቅላይ ሚኒስትር አክለውም፦" የኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ ያለንን አቋም በግልጽ አሳውቀናል፤ ሁለልጊዜም ድጋፋችን ለግብጽ ነው" ብለዋል፡፡
የግብጹ አቻቸው ሸሪፍ ኢስማኤል በበኩላቸው ኮንጎ- በኮንጎ ወንዝ ላይ እየገነ...ባች ላለው ታላቅ ግድብ ግብጽ ድጋፏን እንደምትሰጥ አማረጋገጣቸውን የ አህራም ኦንላይን ዘገባ ያመለክታል።
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ ከአባይ ተፋሰስ ሀገሮች አንዷ ናት። ግብጽ -ኢትዮጰያ በአባይ ወንዝ ላይ እየሰራችው ያለው ግድብ በውሃ ድርሻዋ ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድርባት በተደጋጋሚ ስታሳውቅ ቆይታለች።
ኢትዮጰያ በበኩሏ ግድቡ ግብጽን ጨምሮ በተፋሰሱ ሀገራት ላይ የሚያመጣው ጉዳት እንደሌለ ነው በተደጋጋሚ የገለጸችው።
አንድ ስምምነት ላይ ሊደርሱ ባለመቻላቸውም ኢትዮጰያ፣ ግብጽና ሱዳን በጉዳዩ ዙሪያ እየተነጋገሩ ይገኛሉ።
የኮንጎውና የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሀገሮቻቸው በሚኖራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር ዙሪያም መነጋገራቸው ተዘግቧል።
በርካታ የ ኢኮኖሚና የፕሮቶኮል ስምምነቶችን መፈራረማቸውም ታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፖኒዮ ከዚህም ባሻገር የግብጽ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን የጎበኙ ሲሆን፤ ከአፈ-ጉባ አሊ አብደል አል ጋር ተነጋግረዋል።

No comments:
Post a Comment