የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ በውጭ አገር የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄ የውጭ ዘርፍ አባላት ከጥር 27 እስከ ጥር 29 ፣ 2008 ዓም የዘረፉን 1ኛ ጠቅላላ ጉበኤ አካሂደው፣ የውጭ ዘርፍ አመራሩ ባለፈው አንድ አመት ያከናወነውን የስራና የፋይናንስ እንዲሁም የተለያዩ ኮሚቴዎች ያቀረቡትን ሪፖርት ማዳመጡን ገልጿል።
በበጎ የተሰሩ ስራዎችን በማጠናከር፣ መሰራት ሲገባቸው ባልተሰሩት ስራዎች ላይ ሰፋ ያሉ አስተያየቶችን መካሄዱን ንቅናቄው በመግለጫው ጠቅሶ፣ በዘረፉ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት በመወያየት ህገደንቡን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የንቅናቄውን የውጭ ዘርፍ ሊመሩ የሚችሉ የአመራር አካላትንም መምረጡን ገልጿል። ...
ንቅናቄው የጀመረውን የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ እና አገር የማዳን ትግሉን በድል ለመወጣት ትግሉን አጠንክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

No comments:
Post a Comment