የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንዶሚኒየም እጣ በሚወጣበት ወቅት በባለትዳሮች መካከል የጥቅም ግጭቶች እየተከሰተ የፍቺ ቁጥር እንዲያድግ አስተዋጾ አድርጓል።
በሌላ በኩል ባልና ሚስት ሁለቱም ኮንዶሚኒየም ለማግኘት ተመዝግበው እጣ ሲወጣ ሁለት ቤት ስለማይፈቀድ በስምምነት የውሸት ፍቺ የሚፈጽሙበት ክስተቶች እየተበራከቱ መጥተዋል።በተጨማሪም ለዲቪ ጉዞ ተብሎ የሚደረግ መጠናናት የሌለበት ጋብቻ እንዲሁም የውሸት ጋብቻ በተጨማሪ ምክንያትነት ተጠቅሰዋል ።
ተጋቢዎች የሚፋቱበትን ምክንያት ያለመናገር መብት ያላቸው በመሆኑ ፍ/ቤቶች ሆን ብለው አጥፊዎችን ለመቆጣጠር አላስቻላቸውም ተብሎአል። በ2006 ዓም 941 ሰዎች በአ/አ ከተማ ፍቺ የፈጸሙ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2007 ወደ 3747 አሻቅቦአል።

No comments:
Post a Comment