የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በሻሰመኔ ስር በሚገኘው በአጄ ወረዳ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል። አንዳንድ ምንጮች የሟቾቹን ቁጥር እስከ 3 ያደረሱታል። ይሁን እንጅ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት 2 የፌደራል ፖሊስ አባላትና 7 ሰዎች ተመትተው ሆስፒታል ገብተዋል።
ግጭቱ ትናንት ከምሽቱ 2 እስከ 5 ሰአት ቀጥሎ ፣ በምሽት የብሄር ግጭት ይፈጠራል በሚል ያካባቢው ሰዎች ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸው ነበር። ይሁን እንጅ ዛሬ በነበረው ተቃውሞ ህዝቡ የመብት ጥያቄዎችን እያነሳ ከፖሊሶች ጋር ሲፋጠጥ ውሎአል።
በኦሮምያ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ነው። መንግስት ተቃውሞውን መቆጣጠጠሩን በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ይህን አያሳይም።

No comments:
Post a Comment