Monday, February 29, 2016
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በታክሲዎች አድማ ምክንያት ተሰረዘ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 120ኛውን የአድዋ ድል በዓል በነገው እለት ለማካሄድ የያዘውን የፖናል ውይይት ከአ/አ ታክሲዎች አመጽ ጋር በተያያዘ ለመሰረዝ ተገዷል።
የጋይንት ህዝብ ስለወልቃይት ጉዳይ አትጠይቅም በመባሉ ስብሰባ ረግጦ ወጣ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን በጋይንት ከተማ የክልሉ ባለስልጣናት ህዝቡን ለማወያየት ትናንት እሁድ የጠሩት ስብሰባ፣ በተቃውሞ ተበትኗል።
የተቃውሞው መነሻ ደግሞ ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ፣ ህዝቡ ጥያቄ ማቅረብ በመጀመሩና ስብሰባውን የሚመራው ጋዜጠኛ ” ስለወረዳችሁ እንጅ ስለሌሎች አካባቢዎች ጥያቄ መጠየቅ አትችሉም” ማለቱን ተከትሎ ነው።
አርበኞች ግንቦት በበርን ስዊዘርላንድ የተሳካ ህዝባዊ ውይይት አደረገ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው አመራር የሆኑት አርበኛ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው ፣ የኢሳት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የጀርመን ሃገር ቃል አቀባይ ሃይሉ ማሞ፥ ተቀማጭነታቸው በስዊዘርላንድ የሆኑ የሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ የስዊዘርላንድ ከተሞችና ከሙኒክ ጀርመን ከተማ በመጡ ሃገርወዳድ ኢትዮጵያውያን በታደሙበት በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ውይይት ላይ የወቅቱ የሃገራችን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታ፣ የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል እንቅስቃሴ ፣ ላለፉት 4 ወራት በመላው የኦሮሚያ ከተሞች እየተካሄደ ስላለውና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ የኦሮሞ ተማሪዎች፣መምህራና ሰራተኞች ክቡር ህይወት መጥፋትን ስላስከተለው የህዝብ እምቢተኝነት ፣ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ስለታሰበውና ርዝመቱ ክ 1600 ኪሎሜትር በላይ ስለሆነው መሬት ፣ የነፃነት ታጋዩ አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ ወቅታዊ ሁኔታና የሱን ፈለግ ስለመከተልና ሰለሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
Saturday, February 27, 2016
ፍል ውሃ አካባቢ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ተቃውሞ ተካሄደ
ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)
በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱና በሃገሪቱ ያለን ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ አርብ ፍል ውሃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ተካሄደ።
የአርብ ልዩ የጾም (ጁምዓ) ስነ-ስርዓት ተከትሎ በተካሄደው በዚሁ ተቃውሞ የሙስሊም ማህበረሰብ መፈክሮች የተጻፉባቸው ፊኛዎችን ወደሰማይ መልቀቃቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኖርዌይ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተገዢ እንድትሆን ጠየቀ
ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)
የኖርዌይ መንግስት በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ያለፍላጎታቸው ወደሃገራቸው ለመመለስ የያዘውን እቅድ ተከትሎ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሃገሪቱ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተገዢ እንድትሆን አሳሰበ።
ሃገሪቱ በስደተኞች ላይ እየያዘች የመጣችውን አዳዲስ አቋሞች የተቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ኖርዌይ ለአለም አቀፍ ህግጋት ተገዢ ያለመሆን አቅጣጫ እየተከተለች እንደሆነም አስታውቋል።
ቤተ-እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ የወጣው እቅድ እንዲዘገይ ተደረገ
ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)
በቅርቡ የመጨረሻዎቹ ዘጠኝ ሺህ ቤተ-እስራዔላውያን ከኢትዮጵያ ወደእስራዔል ለማጓጓዝ ቃል ገብታ የነበረችው እስራዔል እቅዱ እንዲዘገይ ማድረጓን አርብ ይፋ አደረገች።
የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እቅዱ ከበጀት ጋር በተያያዘ እንደዘገይ መደረጉን ቢገልፅም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት ድርጊቱ በእስራዔል ጥያቄን አስነስቶ ካለው ከዘረኝነት ጉዳይ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገልጸዋል።
የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጄኔራል ዳይሬክተር የሆኑት ኤሊ-ግሮነር እቅዱ ከመነሻውም በጀት ሳይያዝለት መፅደቁን ይፋ ማድረጋቸውን ሃርቴዝ የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ አርብ ዘግቧል።
Friday, February 26, 2016
ህወሃት/ኢህአዴግ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ካለው ተቃውሞ ጀርባ የኤርትራ እጅ አለበት ሲል ከሰሰ
ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ካለው ተቃውሞ ጀርባ የኤርትራ እጅ አለበት ሲሉ አዲስ ተቃውሞ ማቅረባቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አርብ ዘገበ።
መነሻውን ከጎረቤት ኤርትራ ያደረጉ አካላት በተቃውሞ ስለመሳተፋቸውንና ችግሩን በማባባስ ላይ ስለመሆናቸው በቂ ማስረጃ አለን ሲሉ የመንግስት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ ለዜና አውታሩ ገልጸዋል።
በወሊሶ ከተማ ተቃውሞ ተካሄደ
ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)
በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ዳግም ያገረሸው ህዝባዊ ተቃውሞ አርብ ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ወሊሶ መዛመቱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች በከተማዋ የተዘረጋን ዋና መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ሲያቀርቡ መዋላቸው ታውቋል።
በደብረብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ
ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)
በአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረ-ብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በትንሹ 14 ሰዎች መገዳላቸውን ፖሊስ አርብ አስታወቀ።
አንድ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከሌላ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው አደጋው ሊደርስ መቻሉንና፣ ሌሎች ሶስት ሰዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል።
በኦሮምያ ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎ ዋለ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት 4 ወራት በተከታታይ ሲደረግ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል።ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ሰራዊት በሰፈነበት ምእራብ ሃረርጌ፣ሀብሩ ወረዳ ዴፎ ከተማ ህዝቡ ለተቃውሞ በመውጣት፣ መሰረታዊ የሚባሉ የመብት ጥያቄዎችን ሲጠይቅ አርፍዷል።በወለጋ ሆድሮጉድሩ የሻምቡ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች የሚያወግዝ ተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት የሚመራው የትግራይ ክልል፣ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ግልሰቦችን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎችን ዛሬም በሁመራ ከተማ አዘጋጅቷል።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አካሄዱ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መብታቸው እንዲከበርላቸው ለአመታት ሲጠይቁ የቆዩት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከአርብ ቀን ጸሎት በሁዋላ የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎችን በመልቀቅ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።ፍልውሃ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ በተካሄደው ተቃውሞ “ጭቆናን እንታገላለን፣ ኮሚቴው ይፈታ ፣ ድራማው ይብቃ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ተለቀዋል።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የእሰረኞች ሰንድ እንዳይወጣ አገደ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፌደራል አቃቤ ህግ ይግባኝ ተጠይቆባቸው ጉዳያቸውን ከከቃሊቲ እስር ቤት በመመላለስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት የቀድሞው አንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ማዕከል፣ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ማስረጃ ላይ የሰነድ አስተያየታቸውን ለማቅረብ ያዘጋጁትን ጽሁፍ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳይወጣ እንደከለከላቸው ገለጹ፡፡
ቻይናዊያን በሕገወጥ የችርቻሮ ንግድ ላይ በመሰማራታቸው ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች መስራት አልቻልንም አሉ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመዲናችን አዲስ አበባ በቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች በቻይናዊያን የሕገወጥ ንግድ ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳልቻሉ ተናገሩ። ባለፉት ሶስት ዓመታት የውጭ ዜጎች በሚበዙበት በቦሌ ሩዋንዳ ለምግብ ፍጆታዎች የሚውሉ ምርቶች በማቅረብ ስራ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች በሕገወጥ የቻይኖች ዜጎች አካባቢያችን ተወሮ ሱቃቸውን ለመዝጋት እየተገደዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በቦሌ ሩዋንዳ በሚኒ ማርኬት ተሰማርተው የሚገኙት ወ/ሮ ትክክል ተበጀ ሁኔታውን ሲያስረዱ ” በሰው ሀገር መንደር ውስጥ ገብቶ ጎመን፣ አሳ፣ አሳማ እና ዶሮ ዘርግቶ ይቸረቸራል እንዴ? መንደራችን ዘልቀው የሚቸረችሩ ከሆነ እኛ ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች የት ሄደን እንሰራ? አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ከ2 መቶ ሽህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ውስጥ እንጂ ችርቻሮ ውስጥ መግባት አይችልም። ጎመን ቸርቻሪ ቻይና አጠገባችን ሱቅ ከፍቶ የገበያ ስርዓቱን ሲያፋልሰው መመልከት በእውነት አስተዳደር አለ ወይ ብለን ለመጠየቅ ተገደናል። ያላንኳኳነው የመንግስት አካል የለም ወዴት ሄደን አቤት እንደምንል ግራ ገባን?” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።
Wednesday, February 24, 2016
የአቶ ሃይለማርያም ዛቻም ሆነ የሃይማኖት አባቶች ተማጽኖ በኦሮምያ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ አላስቆመውም
የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ወታደሮች ለተቃውሞ በሚወጡት ወጣቶች ላይ በቀጥታ እንዲተኩሱ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል፣አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም መንግስታቸው የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ በአደባባይ ዝተዋል። የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚወክሉ የሃይማኖት አባቶች፣ በመንግስትና በህዝቡ መካከል መነጋጋር እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ሁሉ ዛቻና ምክር እየተሰጠ ቢሆንም፣ የክልሉ ወጣቶች የሚያቆመን የለም በማለት ዛሬም ትግላቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ኦህዲኅ/ ም/ሊቀመንበር ተፈቱ
የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ም/ል ሊቀመንበሩ አቶ ዓለማየሁ መኮንን በትናንትናው ዕለት ‹‹የፍትህ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው›› በማለት ስለዞኑ ፍትህ መናገራቸውን ተከትሎ ታስረው ነበር፡፡ ‹‹ፍትህ በሌለበት፣ነጻነት አይኖርም ፣ነጻነት በሌለበትም ፍትህ አይኖርም ›› ብለው ተናግረዋል በሚል በዳኛ ዳዊት አድማሱ ጥሩነህ በቀረበባቸው አቤቱታ መታሰራቸው በፖሊስ የእለት መዝገብ ላይ ሰፍሮ ቢገኝም፣ ማንም ቀርቦ ስለሁኔታው ሊያስረዳ ባለመቻሉ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሸጎሌ ሾዴ ከታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመምጣት እንዳስፈቷቸው ለማረጋጋጥ መቻሉን ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ ገልጿል።
አቶ ዓለማዬሁ በአካባቢያቸው የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በድፍረት በማጋለጥ ይታወቃሉ።
የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው
የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ጉብኝቱን መቼ እንደሚያካሂዱ ባይገለጽም፣ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ወቅት የስደተኞች ጉዳይ ዋና አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በጉብኝታቸው በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ አንስተው ከኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ይነጋገሩ አይነጋገሩ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን በማካሄድ ጫና መፍጠር ከቻሉ፣ ጠ/ሚኒስትሩ ለጉዳዩ ትኩረት ሊሰጡ ይችላሉ ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።
Tuesday, February 23, 2016
የድርቅ አደጋው በቀጣዩ ወር ወደረሃብ ሊቀየር ይችላል ተባለ
ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው ኬር ኢንተርናሽናል ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ወደረሃብ ደረጃ ለመቀየር አንድ ደረጃ ብቻ እንደቀረው ማክሰኞ ይፋ አድርጓል።
በቅርቡ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የጎበኙት የድርጅቱ ሃላፊዎች አሁን ያለው የሃገሪቱ ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ በደረጃ አራት ላይ መቀመጡንና ወደረሃብና (ደረጃ አምስት) ለመድረስ ከጫፍ መቃረቡን አስረድተዋል።
የድርጅቱ ዋና ሃላፊ የሆኑት ሎሪ ሊ ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ አፋጣኝ ምላሽን ካላገኘ በቀጣዩ ወር አስከፊ ጉዳት ሊከሰት እንደሚችል አሳስበዋል።
ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለው ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የእርዳታ ጉድለትም ከ10 ሚሊዮን በሚበልጡ ተረጂዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን አሳድሮ እንደሚገኝ ሃላፊው አክለው ገልጸዋል።

በሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ያሳፈረ ተሽከርካሪ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት ደረሰበት
ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ ወታደሮች አሳፍሮ በደቡባዊ ሶማሊያ ይጓዝ የነበረ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ በተቀበረ ቦንብ ጉዳት እንደደረሰበት የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዘገቡ።
ሊጎ ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው የቦንብ አደጋ በርቀት መቆጣጠሪያ የተቀነባበረ መሆኑና በተሽከርካሪው ላይ የቃጠሎ አደጋ መድረሱን ራዲዮ ሸበሌ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ አስደምጧል።
በወታደራዊ ተሽከርካሪው ላይ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎም በኢትዮጵያ ወታደሮችና በአልሻባብ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ ነው ተባለ
ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
ሰሞኑን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች ዳግም ያገረሸው ተቃውሞ ከሳምንቱ መገባደጃ ጀምሮ በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ አካባቢዎች በሚገኙ የገጠር ከተሞች መቀጠሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ምዕራብ ወለጋን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ በጸጥታ ሃይሎች በሚገደሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በስፍራው ያለው የጸጥታ ሁኔታ ባለመረጋጋቱም የሟቾችን ቁጥር በአግባቡ ማወቅ ያልተቻለ ሲሆን፣ የተለያዩ አካላት እስከ 20 የሚደርሱ ሰዎች በሳምንቱ መገባደጃ ብቻ መገደላቸውን ይገልጻሉ።

የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹና የኤምባሲው ሰራተኞች በአምቦና በሞጆ ሻሸማኔ በሚወስድ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አሳሰበ
ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል ተባብሶ የቀጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹና የኤምባሲው ሰራተኞች በአምቦና በሞጆ ሻሸማኔ በሚወስድ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አሳሰበ።
በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ ለደህንነት ስጋት እየሆነ በመምጣቱ ኤምባሲው የጉዞ ማሳሰቢያን ለማሰራጨት እንደተገደደም አስታውቋል።

ከ10 ሚሊዮን በላይ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች የምግብ አቅርቦት ሊቋረጥባቸው ይችላል ተባለ
ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
በኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቀጣዩ ወር የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ ሊቋረጥ እንደሚችል የአለም ምግብ ፕሮግራም ማክሰኞ አሳሰበ።
በቀጣዮቹ አስር ቀናት ውስጥ ተጨማሪ አለም አቀፍ እርዳታ ካልተገኘ በርካታ የእርዳታ ማቅረቢያ ጣቢያዎች አገልግሎታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የድርጅቱን ሃላፊዎች ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
ሃገሪቱ አለም አቀፍ ማህበረሰብ እየጠበቀች ያለው እርዳታ በአስቸኳይ መቅረብ ካልጀመረ የድርቁ አደጋ አስከፊ ጉዳትን ማድረስ እንደሚጀመር በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይ ጆን አይሌፍ ገልጸዋል።

ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቁ እየተባባሰ ነው ሲል ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
በተያዘው ወር ለበልግ ወቅት ሲጠበቅ የነበረው ዝናብ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክልሎች በበቂ ሁኔታ መዝነብ ባለመጀመሩ ድርቁ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታውቋል።
በሰሜንና ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሲጠበቅ የነበረው የበልግ ዝናብ በአግባቡ ባለመዝነቡም ድርቁ ቀጣይ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር ህወሃት/ኢህአዴግ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ
ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
በኦሮሚያ ክልል ለሶስተኛ ወር ቀጥሎ ያለውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማክሰኞ አስታወቀ።
በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በክልሉ በበርካታ አካባቢዎች እየተካሄደ ካለው ተቃውሞ ጀርባ የጥፋት ሃይሎች ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።

Wednesday, February 17, 2016
የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) ሳሙኤል ግደይ፣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በማብረር ከምስራቅ አየር ምድብ ድሬዳዋ በውሎ የጠፉት በ2007 ዓ.ም ሲሆን የህወሓት አገዛዝ የጦር ፍርድ ቤት የካቲት 4 2008 ዓ.ም በሌሉበት በሞትና እድሜ ልክ እስራት ቀጥቷቸዋል፡፡
የሄሊኮፕተሯ ዋና አብራሪ ሳሙኤል ግደይ በሞት ሲቀጣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡
ከእነ ሳሙኤል ግደይ በፊትም በ1993 ዓ.ም ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ኤል-39 ተዋጊ ጀት እያበረረ ከመቀሌ ተነስቶ ኤርትራ መግባቱ፤ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬ እና መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር እያበረሩ ጅቡቲ ማረፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬና አብዮት ማንጉዳይ በጅቡቲ መንግስት ለህወሓት ተላልፈው ተሰጥተው የእድሜ ልክ እስራት እና የ15 አመት እስር ተፈርዶባቸው መቶ አለቃ አብዮት የእስር ጊዜውን ጨርሶ በመፈታቱ በአሁኑ ጊዜ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ ኤርትራ በረሃ እንደሚገኝ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

የኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አዛዥ እና የበረራ አሰተማሪ የነበረው ሻለቃ አክሊሉ መዘነም ከአመታት በፊት ስርዓቱን በመቃወም ወደ ኤርትራ መጥቶ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ትግል ላይ ይገኛል፡
ሀሰቱም ያብቃ፤ ዳር-ድንበር መሸጡም ይቁም! (ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሜቴ የተሰጠ መግለጫ)
ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሜቴ የተሰጠ መግለጫ
የካቲት 8 ቀን 2008 ዓ/ም (February 16, 2016)
ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ በአገራችን የተከሰተው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሰሞኑን የተጀመረ ለማስመሰል እንደሚሞክረው ሳይሆን፤ ሕወሓት ካለፉት በርካታ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍና መከራ ድምር ውጤት ነው። ብሶቱም መጠነ ሰፊ፤ ጊዜውም ከ25 ዓመት በላይ ያስቆጠረ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው።

በተለያዩ ክፍለ አገራት ያሉ ወገኖቻችን ለዘመናት ይኖሩበት ከነበሩበት መንደሮች በልማት ስም በኃይል እየተፈናቀሉ የትም እንዲወድቁ ሲደረጉ፤ አንድም ቀን ይህን የሕወሓትን ግፍና መከራ በፀጋ የተቀበሉበት ጊዜ አልነበረም።
ከአፍንጫው ራቅ አድርጎ ማሰብ የማይችል አምባገነን አገዛዝ አንድ ሕዝብ በቁጣ በተነሳ ቁጥር ማስታገሻው ወይም እንደነሱ አባባል ማርከሻው ሕዝቡን በኃይል “ፀጥ” ማድረግ ነው። “ፀጥ” እናደርጋቸዋለን የሚሉ ወገኖች አንድ ቀን ራሳችው ፀጥ እንደሚሉ ስለማይገነዘቡ የማይቀረውን የቁልቁለት መንገድ ይያያዙታል። ያኔ ኃይል የነሱ ሳይሆን የሕዝብ መሆኑን ሳይወዱ በግድ ይረዱታል።
Tuesday, February 16, 2016
ከእስር እንዲፈቱ ከወሰነላቸው አምስት የፓርቲ አመራሮችና አባላት መካከል ሁለቱ ብቻ ማክሰኞ ተፈቱ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ጥያቄ ቀርቦባቸው ከእስር እንዲፈቱ ከወሰነላቸው አምስት የፓርቲ አመራሮችና አባላት መካከል ሁለቱ ብቻ ማክሰኞ ተፈቱ።
...

ፍርድ ቤቱ ከቀናት በፊት ሁሉንም ተከሳሾች ከእስር ቤት እንዲለቀቁ ወስኖ የነበረ ሲሆን፣ የአንድነት የህዝብ ግንኙነት አቶ ሃብታሙ አያሌውና በተመሳሳይ ክስ ስር የነበረው መምህር አብርሃም ሰለሞን ከእስር መለቀቃቸው ታውቋል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት አርብ ሁሉም ተከሳሾች ከእስር ቤት እንዲወጡ ቢወሰንም የቃሊቲ እስር ቤት ተከሳሾቹ ችሎት በመድፈር የተላለፈባቸውን ቅጣት ስላልጨረሱ ሊለቀቁ አለመቻላቸውን መግለጹ ይታወሳል።
ይሁንና፣ ተከሳሾቹ ቅጣታቸውን እንደጨረሱ ቢገልፅም የእስር ቤቱ ሃላፊዎች ቅጣቱ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር አይደለም በማለት ቅጣቱ አለማለቁን ለፍርድ ቤት ገልጿል።

በሚዛን ቴፒ በትንሹ 15 ሰዎች በመኪና አደጋ መሞታቸውን ፖሊስ ገለጸ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
በደቡብ ክልል ከሚዛን ወደ ቴፒ ከተማ ይጓዝ የነበረ የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ አውቶቡስ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበት በትንሹ 15 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ ማክሰኞ አስታወቀ። ...
በዚሁ አደጋ 32 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ተጎጂዎቹ ከሚዛን ወደቴፒ ከተማ ተጉዘው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ወስደው ሲመለሱ አደጋው መደረሱን ፖሊስ ገልጿል።
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞችን ይዞ ይጓዝ የነበረው አውቶቡስ በቁ በሚባል ወንዝ ውስጥ በመግባቱ አሰቃቂው አደጋ ሊደርስ መቻሉን እማኞች አስረድተዋል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ከ30 በላይ መንገደኞችም በቴፒ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፣ ከ15ቱ ሟቾች መካከልም አንድ ህጻን እንደሚገኝበት ፖሊስ አክሎ ገልጿል።
ባለፈው ሰምንት ደርሰው በነበሩ ሁለት የተሽከርካሪ አደጋዎች 36 ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በሃገሪቱ እያደረሰ ያለው የትራፊክ አደጋም ከምቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ መምጣቱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አመልክቷል።
የአሮጌ ተሽከርካሪዎች መብዛት፣ የትራፊክ ምልክት በአግባቡ አለመኖር፣ ጠጥቶና ጫት ቅሞ ማሽከርከር ለጉዳቱ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው ይነገራል።
የአለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ቁጥር አንጻር አነስተኛ ተሽከርካሪ ቢኖራትም እየደረሰ ያለው ጉዳት ግን በአለም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቋል።
ከ90 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባላት ኢትዮጵያም የተሽከርካሪዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን የማይሞላ ሲሆን፣ ባለፈው አመት ብቻ ከሶስት ሺ በላይ ሰዎች በዚሁ አደጋ መሞታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከ200 በሚበልጡ ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መፈጠሩን አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ገለጹ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የድርቅ አደጋ ተከትሎም ከ200 በሚበልጡ ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መፈጠሩን አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ገለጡ።

በነዚሁ ወረዳዎች ውስጥ ተከስቶ ያለውን የውሃ እጥረት መቅረፍ ካልተቻለ ችግሩ በነዋሪዎች ላይ ጉዳትን ሊያስከትል እንደሚችልም የብሪታኒያው ኦክስፋም እና ወርልድ ቪዥን የተባሉ ድርጅቶች አስታውቀዋል።
በወረዳዎቹ ውስጥ እየታየ ያለው የውሃ እጥረት የድርቁ አደጋ የሚያደርሰውን ጉዳት የከፋ ሊያደርገው እንደሚችል ያሳሰቡት የግብረ-ሰናይ ድርጅቶቹ፣ በአጠቃላይ 209 ወረዳዎች በዚሁ ችግር መጠቃታቸውን ገልጸዋል።
በሃገሪቱ ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት በተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከልም ወደስድስት ሚሊዮን የሚጠጉት አስቸኳይ የውሃ አቅርቦት የሚፈልጉ መሆናቸውም ታውቋል።

የኖርዌይ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደ ኦሮሚያ በሚያደርጉት ጉዞ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
መቀመጫውን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ ያደረገው የኖርዌይ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደ ኦሮሚያ ክልል በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ ማክሰኞ አሳሰበ።

በክልሉ በምዕራብ አርሲ ዞን አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎች ማሳሰቢያን ያሰራጨው ኤምባሲው የጸጥታ ስጋት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች መሆኑንም አመልክቷል።
በክልሉ ያሉም ሆነ ወደ ክልሉ ለመጓዝ እቅድ ያላቸው የኖርዌይ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄን በማደረግ በጉዞአቸው ላይ ማስተካከያን እንዲያደርጉ ኤምባሲው ጠይቋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት በልዩ ሁኔታ በመከታተል ላይ የምትገኘው ኖርዌይ፣ በአውሮፓ ህብረት በመመረጥ የሃገሪቱን አጠቃላይ የደህንነትና የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እየተከታተለች እንደሆነም ታውቋል።
ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ስታወጣ የቆየችው ሃገሪቱ በአውሮፓ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ በምታደርገው ጥረት ተደማጭነት ያላት ሃገር መሆኗንም ለመረዳት ተችሏል።

በምዕራብ አርሲ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ተዛምቶ ከፍተኛ ግጭት ተካሄደ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
በምዕራብ አርሲ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አጎራባች ቀበሌዎች መዛመቱንና በአካባቢው ከፍተኛ ግጭት በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞችን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ማክሰኞ ዘግቧል።
...
...
ይኸው ተቃውሞ በሻላ፣ ሲራሮ፣ አጄና፣ ሻሸመኔ ከተማ ተዛምቶ የሚገኝ ሲሆን፣ የፀጥታ ሃይሎችም ከነዋሪዎች ጋር ግብግብ ውስጥ መሆናቸውን መጽሄቱ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አቅርቧል።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃዎች በሻሸመኔ ከተማና በአቅራቢያዋ ባሉ አካባቢዎች በትንሹ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች አስረድተዋል።
በሻሸመኔ ከተማ ከሞቱ ሁለት ሰዎች መካከል አንደኛዋ እድሜዋ በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኝ ነፍሰጡር መሆኗን የከተማዋ ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎም በሻሸመኔ ከተማ የመንግስትና የግል ተቋማት ተዘግተው የሚገኙ ሲሆን፣ በከተማዋ ወደተለያዩ አካባቢዎች የሚወስዱ መንገደኞችም መዘጋታቸውን ለመረዳት ተችሏል።
የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ሃይሎችም በሻሸመኔ ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በመስፈር ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል።
አካባቢው የተረጋጋ ባለመሆኑ የሟቾች ቁጥር በአግባቡ ማወቅ እንዳልተቻለ የሚናገሩት ነዋሪዎች በርካታ ሰዎችም ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው በአካባቢው የተፈጠረውን ግጭት ምክንያት ለማወቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ማክሰኞ ምሽት አስታውቀዋል።

በምዕራብ አርሲ በትንሹ አምስት ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃ፣ በትንሹ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ድርጊቱ ሻሸመኔ ከተማን ጨምሮ በአካባቢው በሚገኙ አነስተኛ ከተሞች ተቃውሞ መቀስቀሱ ተሰማ።

የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው በፀጥታ ሃይሎችና በነዋሪዎች መካከል በተቀሰቀሰው በዚሁ ግጭት ሰባት የጸጥታ ሃይሎች መሞታቸውን ሜይል ኤንድ ጋርዲያን አፍሪካ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት በፀጥታ ሃይሎች ላይ በወሰዱት እርምጃ ግጭቱ ሊቀሰቀስ መቻሉን ተናግረዋል።
ይሁንና የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ሰርገኞችን አሳፍሮ ይጓዝ በነበረ አውቶቡስ ላይ የወሰዱትን የማዋከብና የተኩስ እርምጃ ተከትሎ በስፍራው ግጭት መነሳቱን አስረድተዋል።
በአካባቢው ነዋሪዎችና በፀጥታ ሃይሎች መካከል የተካሄደውን ግጭት ተከትሎም በርካታ ነዋሪዎች ግድያና ድብደባ እንደተፈጸመባቸውም ጋዜጣው አስነብቧል።

የአርቲስት አድማሱ ብርሃኑ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
የታዋቂው የኪነጥበብ ሰው አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ። ለ36 ዓመታት ያህል በኪነጥበቡ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጉ የሚነገርለት አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ በተለይ በኦሮምኛ የኪነጥበብ ስራዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነት አትርፏል።

“አባ ለታ” በሚል ብዙዎች የሚጠሩት አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ያለፈው ሰኞ የካቲት 7 ፥ 2008 ዓ ም ሲሆን፣ የቀብር ስነስርዓቱ ማክሰኞ የካቲት 8 ፥ 2008 በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ሐምሌ 26 ቀን 1948 አም ከአባቱ አቶ ብርሃኑ መገርሳና ከእናቱ ከ ወ/ሮ ዘነበች ጎሹ በወለጋ ክፍለሃገር በቢላ ወረዳ የተወለደው አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ፣ ለ36 አመታት በተለያዩ የመድረክ ስራዎች እንዲሁም በፊልሞች የኪነጥበብ ስራዎችን ለኢትዮጵያውያን ሲያበረክት ቆይቷል።
የሶስት ሴቶችና የሁለት ወንድ ልጆች አባት የነበረው አርቲስት አድማሱ ብርሃኑ ከዚህ አለም በሞት የተሰናበተው በተወለደ በ60 አመቱ ነው። ኢሳት ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆቹና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

ኢሳት በናይልሳት የ24 ሰዓት ሬዲዮ ስርጭት ጀመረ!
ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ወደ ኢትዮጵያ ሲያሰራጭ የቆየውንና የተቋረጠውን ፕሮግራሙን በሬዲዮ ጀመረ። የቴሌቪዥን ስርጭቱን ለማስቀጠልም ከሳተላይት አቅራቢ ኩባንያዎች ጋር ቴክኒካዊ ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም የኢሳት ማኔጅመንት አስታውቋል።

አሁን በናይል ሳተላይት የሚተላለፈው የኢሳት ሬዲዮ ስርጭት ለ24 ሰዓታት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑም ታውቋል። ስርጭቱ በ Nilesat 12604 horizontal ላይ በመተላለፍ ላይ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። ከኢሳት ማኔጅመንት መረዳት እንደተቻለው የኢሳት የ24 ሰዓታት የቴሌቪዥን ስርጭት በቅርቡ ይጀምራል።
ኢሳት በተለያዩ ሳተላይቶች ወደኢትዮጵያ ሲያስተላልፋቸው የነበሩ ፕሮግራሞች ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የውጭ ባለሙያዎችንና የውጭ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አስተጓጉሎት ቆይቷል ያለው የኢሳት ማኔጅመት በዚህ ሳምንት ኢሳት በሬዲዮ ስርጭት ወደ አየር መመለሱን አስታውቋል።

ጥያቄህን ልመልስ-ልጄ | ከስርካለም ፋሲል
ለረጅም ግዜ ተራርቀን የማገኛቸው ጓደኞቼ ናፍቆትን ሲያዩት የሚጠይቁኝ “ያ ቃሊቲ የተወለደው ልጅ ነው በጣም አደገ” በማለት ነበር።
አንተም በተደጋጋሚ “ቃሊቲ” የምትለዋን ስም ስትሰማ፣ ቦታው ትምህርት ቤትም ሆነ መዝናኛ ስፍራ አለመሆኑን ጠንቅቀህ ስለምታውቅ፣ ጥያቄህ ፦
“ታስረሽ ነበር እንዴ ?…. እኔም ታስሬ ነበር?” የሚል ነው። ለብዙ ግዜ መልሱን በሽፍንፍን ነበር የማልፈው። ምክንያቴ ደግሞ፣ የመረዳት አቅምህን ግምት ውስጥ በማስገባት ነበር።
እስኪ ዛሬ ከ ዘጠኝ ዓመት በፊት ስለነበረው እውነተኛ ታሪክ ልተርክልህ። ምንም እንኳ አሁንም ትረዳኛለህ ባልልም።
ልጄ፣ “ታስሬ ነበር እንዴ እውነቱን ንገሪኝ?”…ለምትለኝ ፦
“አዎ። ለ9 ወራቶች ከማዕከላዊ -ቃሊቲ አብረን አሳልፈናል”
” ምን አድርጌ?… እጄ ላይ እንደእስክንድር ብረት ገብቶልኝ ነበር?” ….
ጥያቄህ ብዙ እንደሚሆን እገምታለሁ … እኔም ብዙ መልስ አለኝ። ለዛሬው ግን የታሰርኩበትን የመጀመሪያውን ቀንና የምጧን ሰዓት ብቻ ላውጋህማ።

በምዕራብ አርሲ ሰልፈኞች እስርቤት ሰብረው ከ100 በላይ የፖለቲካ እስረኞችን አስለቀቁ | 3 ቤተክርስቲያኖች ወድመዋል
(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ ማዕከል በሆነችው አጄ ከተማ ዛሬ ሙሉ ቀን ከተማዋ ሳትረጋጋ መዋሏን ዘ-ሐበሻ ስትዘግብ ውላለች:: የሟች ወታደሮች ቁጥር ከ8 እንደሚበልጥ በተነገረበት በዚህ ወቅት በፖሊስ የተገደሉ ሰላማዊ ሰልፈኞች ቁጥርም 4 እንደደረሰ የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች አስታውቀዋል::
የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ በሰበር ዜናው እንዳስታወቀው በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ የሚገኘውን እስር ቤት ሰልፈኞች ሰብረው በመግባት በእስር ቤቱ ውስጥ ታጉረው የነበሩ ከ100 በላይ እስረኞችን አስለቅቀዋል::
አካባቢውን የወረሩት የፌደራል ፖሊሶች ሕዝቡን መግደል ከጀመሩ በኋላ ሕዝቡም እርምጃ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዱን ዘ-ሐበሻ ቀደም ብላ መዘገቧ አይዘነጋም::
በምዕራብ አርሲ የፌደራል ፖሊሶች ሬሳ አደባባይ ላይ ተጎተተ 8 ወታደሮች ተገድለዋል ተብሏል
(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው አርብ በም ዕራብ አርሲ በአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት ላይ የፌደራል ፖሊሶች ንጹሃን ዜጎችን ከገደሉ በኋላ በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎ በዛሬው ዕለት 8 የፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ተሰማ:: ይህ የሟች ወታደሮች ቁጥር ሊጨምር ይችላል እየተባለም ነው::
ፖሊሶቹ ለተቃውሞ በወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጥይት ተኩሰው ከገደሉና ካቆሰሉ በኋላ ሕዝቡ በዚህ በመቆጣት በፌደራል ፖሊሶቹ ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱ ተሰምቷል:: በዚህም መሠረት በአደባባይ የወደቁት የፌደራል ፖሊሶች ሬሳ ሲጎተት እንደዋለና በየቦታው እንደወደቁም ተዘግቧል::
በም ዕራብ አርሲ አጄ ከተማ እንዲሁም በሻሸመኔ እና ሲራሮ ከተሞች ውጥረቱ እንዳለ ነው:: ሕዝብና የፌደራል ፖሊሶች ተፋጠዋል::

Monday, February 15, 2016
በሻሸመኔ ባለፈው ቅዳሜ የተጀመረው ተቃውሞ ደም አፋሳሽ ሆኖ ቀጥሎአል
የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በሻሰመኔ ስር በሚገኘው በአጄ ወረዳ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል። አንዳንድ ምንጮች የሟቾቹን ቁጥር እስከ 3 ያደረሱታል። ይሁን እንጅ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት 2 የፌደራል ፖሊስ አባላትና 7 ሰዎች ተመትተው ሆስፒታል ገብተዋል።
ግጭቱ ትናንት ከምሽቱ 2 እስከ 5 ሰአት ቀጥሎ ፣ በምሽት የብሄር ግጭት ይፈጠራል በሚል ያካባቢው ሰዎች ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸው ነበር። ይሁን እንጅ ዛሬ በነበረው ተቃውሞ ህዝቡ የመብት ጥያቄዎችን እያነሳ ከፖሊሶች ጋር ሲፋጠጥ ውሎአል።
በኦሮምያ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ነው። መንግስት ተቃውሞውን መቆጣጠጠሩን በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ይህን አያሳይም።

ጋምቤላ በፌደራል ፖሊስና መከላከያ ስር መሆኑዋን መንግስት አመነ
የኮምኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ በጋምቤላ የአኝዋክና የኑዌር የጸጥታ ሃይሎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ተደርጎ መከላከያ ካምፕ መግባታቸውን ገልጸዋል። "ይህን ያደረግንበት ምክንያትም ሁለቱ ወገኖች ወደ ለየለት የብሄር መጠፋፋት ሊያመሩ መሆናቸውን ስለደረስንበት ነው" ብለዋል።
ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተደረጉ ውይይቶች ግጭቱን ለማብረድ ችለናል ቢሉም፣ ከአካባቢው የሚደርሱን መረጃዎች ግን አሁንም በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው። ውጥረቱ በየአካባቢው ያለ ሲሆን፣ አንዱ ብሄረሰብ በሚገኝበት አካባቢ ሌላው መጓዝ አይችልም።
ክልሉ ለምን ያክል ጊዜ በወታደራዊ አዛዦች ቁጥጥር ስር እንደሚውል ሚኒስትሩ አልተናገሩም። ጸጥታ ያስከብራሉ ተብለው የሚገመቱት የጸጥታ ሃይሎች የብሄር ግጭት ያስነሳሉ በሚል ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ከተደረገ፣ ክልሉ ከእንግዲህ በመከላከያ ስር ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነውን፣ ይህን ክልሎች ራሳቸውን ያስተዳድራሉ ከሚለው መብት ጋር እንዴት ነው የሚታየው በማለት ነዋሪዎች በስብሰባዎች ላይ ጥያቄ ማንሳታቸው ታውቋል።
ክልሉ በቅርቡ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ማክበሩ ይታወቃል። በበአሉ ላይ የተገኙት ባለስልጣናት በክልሉ የሰፈነውን ሰላም እና የተረጋገጠውን መብት በተመለከተ ንግግር አድርገው ነበር። ይሁን እንጅ ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ክልሉ በወታደራዊ ጥበቃ ስር መውደቁ፣ የብሄር ብሄረሰቦችን በአል ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ አገሪቱ ከጸጥታና መረጋጋት ጋር የገባችበትን ችግር እንደሚያሳያስ በክልሉ ውስጥ በአንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ሰው አስተያየታቸውን ለኢሳት አካፍለዋል።

ሁለተኛ ዙር የመከላከያ አባላትን ለመቅጠር ቅስቀሳ ተጀመረ
በቅርቡ መንግስት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ለመቅጠር ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጎ የሚፈለገውን ያክል የሰው ሃይል ሊያገኝ ባለመቻሉ፣ ሁለተኛ ዙር ቅጥር ለማካሄድ ቅስቀሳ ጀምሯል።
ምንጮች እንደሚሉት በየጊዜው እየጠፉ የሚሄዱ የመከላከያ አባላት መበራከት እንዲሁም አንዳንዶች ለህገመንግስቱ ታማኞች አይደሉም በሚል መንግስት በጥርጣሬ የሚያያቸው በመሆኑ በተከታታይ በሚደረግ ቅስቀሳ በርካታ ሰልጣኞችን በማስመረቅ በሚጠፉትና በሚባረሩት ቦታ ለመተካት አቅዷል።

ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደና ሌሎች ሙስሊሞች ጥፋተኞች ተባሉ
በአማን አሰፋ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል ከተከሰሱት መካከል 24ቱ ጥፋተኞች ሲባሉ፣ 4ቱ ብቻ በነጻ ተለቀዋል።
ጥፋተኞች ከተባሉት መካከል የሙስሊም ጉዳዮች መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ይገኝበታል። ተከሳሾቹ እስላማዊ መንግስት የማቋቋም ፍላጎት እንዳላቸው፣ በውጭ ከሚገኙ አሸባሪ ድርጀቶች ጋር ግንኙነት ነበራቸው የሚሉና ሌሎችም ክሶች ቀርበውባቸዋል። ተከሳሾች እጅግ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎችን ቢያቀርቡም ፍርድ ቤት አልሰማቸውም።
ጋዜጠኛ ሰሎሞን በእስር ቤት ውስጥ በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ መንገድ የተከሰሰው ሌላው ጋዜጠኛ ዮሴፍ ጌታቸው 7 አመት ተፍርዶበት በእስር ላይ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ እስር ቤት ፍርድ ቤት ነፃ ያላቸውን እስረኞች አለቅም ብሎአል።
በሽብር ተከሰው በእስር ሲማቅቁ የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነጻ ብሎ ቢያሰናብታቸውም እስር ቤቱ ሊለቃቸው ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

በአንድ ክፍለከተማ ብቻ 81 መሃንዲሶች በከፍተኛ ሙስና መዘፈቃቸው ተሰማ
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ 81 መሃንዲሶች በከፍተኛ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ተገኝተዋል። የመሃንዲሶቹ ስም እስካሁን ይፋ ባይሆንም፣ መሃንዲሶቹ ከባለስልጣናት ጋር እጅግና ጓንት በመሆን በመሬት ሽያጭ ከፍተኛ ሃብት አፍርተዋል።
በመሃንዲሶቹ ላይ እስካሁን የተወሰደ እርምጃ የለም። ከእነሱ ጋር በመሆን የአዲስ አበባን መሬት በመቸብቸብ የጥቅም ሰንሰለት ፈጥረዋል በተባሉ ባለስልጣኖች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ይሁን አይሁን ለማወቅ አልተቻለም።

Sunday, February 14, 2016
Friday, February 12, 2016
Ethiopian regime forces arrest dozens in Guji, South Ethiopia, as protest continues unabated
ESAT News (February 12, 2016)
Security forces arrested at least thirty seven people in Guji, south Ethiopia in a bid to crackdown on protesters who demanded political and economic justice in the region where poverty runs deep despite the prevalence gold mines and other gems, which are siphoned by the corrupt regime and its close allies.

The regime sent its regular army to the region to silence the growing protest against MIDROC Gold, the company with close ties to the corrupt government and which has been mining 4.5 metric tons of gold every year for over 20 years. The locals were furious that they have gotten no benefits whatsoever when cronies of the government amassed so much wealth from their land. They are also demanding for the release of prisoners of conscience and for the formation of a fair administration in the region.
The army has rounded up people whom it deemed were leaders of the uprising. University students and members of opposition political parties were among those arrested in the latest round of crackdown by the security forces.
A protester told ESAT that they were taking the protest to the rural areas as the towns have become too dangerous as the federal government keeps sending forces to squash protesters.

አርበኛ ታጋይ ዘመነ ካሴ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ወደ ኤርትራ በረሃ የሚጎርፉ ወጣቶች ቁጥር እየናረ መምጣትን በሚመለከት ከአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ጋር ያደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ በፅሁፍ፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
አርበኛ ታጋይ ዘመነ ካሴ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ወደ ኤርትራ በረሃ የሚጎርፉ ወጣቶች ቁጥር እየናረ መምጣትን በሚመለከት ከአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ጋር ያደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ በፅሁፍ፡፡
ጥያቄ
"እንግዲህ እንደሚታወቀው አርበኛ ታጋይ ዘመነ ካሴ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ኦሮሚያ አካባቢ፣ በጎንደር ፣በጋቤላና በደቡብ ከፍትኛ የሆነ ውጥረት አለ፤ግጭትአለ፤ ህወሓት ደግሞ ከቁጥጥሩ ውጭ ሆኖበታል፤ ከፍተኛ የአፈና መዋቅሩን፣ የእስር መዋቅሩን እንዲሁም ጭፍጨፋ ከዚያም ባለፈ ደግሞ ወደ ዘር ግጭት የመቀየር ስራ እየሰራ ይገኛል፤ እና ይሄን አገሪቱ ላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ከእኛ ትግል አንፃር እንዴት ይመለከቱታል?"
አርበኛ ታጋይ ዘመነ ካሴ
"አመሰግናለሁ! እድሉን ስለሰጣችሁኝ እና እንግዳ አድርጋችሁ ስለጋበዛችሁኝ በዚህ ጉዳይ ላይ እንድናገር፡፡
"አገር ውስጥ ያለው ቅድም በጠቀስካቸውና በአንዳንድ አሁን በይፋ ያልወጡ አካባቢዎች ያለው የህዝብና የመንግስት ትንቅንቅ በየትኛውም መለኪያና መመዘኛ ብታየው እሚያሳይህ ወይም እሚነግርህ አንድ ነገር ነው፡፡ እሱም ምንድን ነው? ብሔራዊ ጭቆናው፤ ፀረ-ጭቆና ትግል ምንም አይነት መልክ ልንሰጠው ብንችል ምንም አይነት ቀለም ልንቀባው ብንችል በተመሳሳይ አይነት ስሜት እና በተመሳሳይ አይነት ግለት በተመሳሳይ አይነት እምቢተኝነት ደረጃ እየደረሰና እየመጣ እንደሆነ ነው የሚያሳየው፡፡
"በመሰረታዊ ጥያቄ ደረጃ ጋምቤላ ያለው ህዝባዊ አመፅ ኦሮምያ ካለው ህዝባዊ አመፅ አይለይም፤ ጎንደር ያለው ህዝባዊ አመፅ ኦሮሚያ ካለው ህዝባዊ አመፅ አይለይም፡፡መሰረታዊ ጥያቄው በዛ አገር ውስጥ እንደ ሰው ሰው ሆኖ የመኖር፣ ተከብሮ የመኖር፣ እንደ ዜጋ የመኖር ጥያቄ ነው፡፡ ስለዚህ በተለይ ላለፉት 25 ዓመታት ሰው ከሰው በታች ተዋርዶ ተቀጥቅጦ፣ ታፍኖ መፈናፈኛ አጥቶ ነው እየኖረ ያለው፤ እየተገዛ ያለው፤ የዚህ አፈና የዚህ ጭቆና ፀረ-ጭቆና እና ፀረ-አፈና ትግል በተጠናከረ ሁኔታ መልክ እየያዘ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል እየተነሳ እና ወደ አንድ አቅጣጫ እየሔድን መሆኑ ነው የሚታየው እሱን ነው ማረጋገጥ የሚቻለው፡፡

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ተከላከሉ ተባሉ
*ተከሳሾች 200 የሰው መከላከያ ምስክሮች አሉን ብለዋል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ከአዲስ አበባ ተነስተው ሲጓዙ ማይካድራ የሚባል የድንበር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሶ የፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ የመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቷል፡፡
ዛሬ የካቲት 4/2008 ዓ.ም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾቹ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ወ/ሪት እየሩሳሌም ተስፋው፣ አቶ ፍቅረማርያም አስማማው እና አቶ ደሴ ካህሳይ አቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ በሰነድና በአንድ የሰው ምስክር ማስረጃዎች አስረድቷል በሚል ተከሳሾች መከላከል ይገባቸዋል ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
ተከሳሾች 14ኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀየርላቸው አቤቱታ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ ይህ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ችሎቱ ብይኑን እንዳያሰማ ቢጠይቁም፣ ችሎቱ ‹‹አቤቱታው ቶሎ ብይን እንዲሰጣችሁ የሚጠይቅ ነው፣ በመሆኑም ብይኑ ተሰርቷል›› ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡ በዚህም ተከሳሾች ብይኑ አይሰማብን የሚለውን ጥያቄ ባለመቀበል ችሎቱ ብይኑን በንባብ አሰምቷል፡፡
እነ ብርሃኑ ተከላከሉ መባላቸውን ተከትሎ መከላከያ ማስረጃዎች ያቀርቡ ከሆነ በሚል ፍርድ ቤቱ ጠይቆ፣ ተከሳሾች 200 የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች በጋራ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም መከላከያ ማስረጃዎችን ለማድመጥ ለመጋቢት 21/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ተከሳሾች እያዘጋጁት የነበሩት የተከሳሽነት ቃል ጽሁፍ በማረሚያ ቤት ፖሊሶች እንደተወሰደባቸው ለፍርድ ቤቱ በመግለጽ ከዚህም በኋላ ተመሳሳይ ለችሎት የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ማዘጋጀት እንዲችሉ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ችሎት የቀረቡት እነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን እና እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ 14ኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀየርላቸው አቤቱታቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ብይን ለማሰማት ለየካቲት 10/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

" ዲሞክራሲ -101"…"መካሪ አያሳጣህ!" ኤርሚያስ ለገሰ
ይቺን አጭር ፅሁፍ ለመጫር የገፋፋኝ በዛሬው እለት አትሌት ሐይሌ ለአንድ የውጭ ሚዲያ የሰጠውን አስተያየት በማዳመጤ ምክንያት ነው። አላማዬ ሐይሌ የተናገረውን ሁሉ ለመቃወም አይደለም። ወይም አንዳንድ " ልወደድ ባይ ደካማ" ሰዎች እንደሚያስቡት አትሌቱ የተጐናፀፈውን ዝና ለማጉደፍ አስቤ አይደለም።
ለእኔም ሆነ ለመላው ኢትዬጲያውያን ሐይሌ በአለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያዊ አርማችን ነው። አርማን ማቆሸሽ ደግሞ ሐገርን ከመክዳት የሚተናነስ አይደለም። ሀይሌ የማይቻል የሚመስል ነገርን በአለም አቀፍ መድረክ እንደሚቻል ያሳየልን በአርአያነት የምናወድሰው ብሔራዊ ሃብታችን ነው። ሐይሌ ሃይላችን ነው። በስደት አለም እንኳን አንዳንድ ሰዎች ሀገራችንን ጠይቀውን ማወቅ ከተሳናቸው ለማስረዳት ከምናነሳቸው ብርቅዬ ስሞች አንዱ ሐይሌ ገ/ሥላሴ የሚለውን ነው።
Thursday, February 11, 2016
ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ አይደሉም የተባሉት ዳኛ ከኃላፊነታቸው ተነሱ
- ለመጀመርያ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች ተሾሙ
ፓርላማው ዳኛውን ከሹመታቸው ያነሳው፣ ጥር 28 ቀን 2008 ዓ.ም. የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ዳኛው ፈጽመውታል ያለውን የዲሲፕሊን ስህተት አዳምጦ ከተወያየ በኋላ ነው፡፡
በዳኛ ግዛቸው ላይ የቀረቡ የዲሲፕሊን ክሶች አራት ሲሆኑ፣ የቀረቡትን ክሶች የመመርመርና ምስክሮችን የመስማት፣ ተከሳሹም በቀረበባቸው ክስና የሰዎች ምስክርነት ላይ ምላሻቸውን እንዲሰጡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አድርጓል፡፡
ዳኛ ግዛቸው ከተከሰሱባቸው አራት ክሶች መካከል በዳኞች ሥነ ምግባር ረቂቅ ደንብ የፍትሕ አካላት ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ ‹‹ዳኛ ሕገ መንግሥቱ ላይ ልዩነት (Reservation) ቢኖረውም ዳኛ ሆኖ መሥራት ይቻላል የሚል አቋም ሲያንፀባርቁ መታየታቸው፣ እንዲሁም በሌሎች አጋጣሚዎችና በተግባር ሕገ መንግሥቱ ላይ የማይቀበሏቸው ሐሳቦች መኖራቸውን የሚገልጹ መሆኑ›› የሚለው ዋነኛው ነው፡፡
በጉጂ ዞን በርካታ ሰዎች ቢታሰሩም ተቃውሞው ግን ቀጥሎአል
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፍትሃዊ ስርዓት እንፈልጋለን፣ የታሰሩ የህሊና እስረኞች ይፈቱ፣ ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ ከአካባቢያችን ይውጣ፣ የተሻለ አስተዳደር ይምጣ የሚሉና በርካታ ጥያቄዎችን በመያዝ የተጠናከረ ተቃውሞ ሲያካሂዱ የሰነበቱት የጉጂ ማህበረሰብ፣ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊሶች እየተደበደቡ ወደ እስር ቤት ቢጓዙም፣ ትግላቸውን ከከተማ ወደ ገጠር በማዞር መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ አዳዳስ ወታደሮች ወደ አካባቢው የተሰማሩ ሲሆን፣ ህዝባዊ ንቅናቄውን ይመራሉ ያሉዋቸውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ጨምሮ በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ37 በላይ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል። ከተያዙት ...መካከል የአካባቢው የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ የሆነው ሙሃመድ ጥላሁን ግርጃ ይገኝበታል።
ትናንት በሃርቃሎ የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ዋገራ፣ ሱክራ ቀበሌ የተሸጋገረ ሲሆን፣ በሻኪሶ ቀበሌዎችም ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነው።
"በከተማው ውስጥ ያለው ሁኔታ አደገኛ በመሆኑ፣ ትግላችንን ወደ ገጠር ለማዞር ተገደናል" በማለት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የተቃውሞው ተሳታፊ ተናግረዋል።
በኦሮምያ የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ በመሳሪያ ሃይል ለማስቆም የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች ግምገማዎች እየተካሄዱ መሆኑም ታውቋል።

በጋምቤላ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ወደ ክልሉ በማምራት የኑዌርና የአኝዋክ የአገር ሽማግሌዎችን በማነጋጋር ላይ ቢሆኑም፣ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
ሁለቱም ብሄረሰቦች በሰፈሩባቸው ኣካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደማይቻልና፣ አንዱ ብሄረሰብ ወደ ሌላው አካባቢ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ እንደሚገደል ምንጮች ተናግረዋል።
የክልሉ አስተዳደር አሁንም ወደ ቦታው አልተመለሰም። ክልሉን የሚያስተዳድሩት የመከላከያ ሰራዊተት አዛዦች ሲሆኑ ፣ የሁለቱ ፕሬዚዳንቶች እጣ ፋንታ አልታወቀም። የክልሉ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች መሳሪያቸውን እንዲፈቱ ከተደረገ በሁዋላ፣ ተሃድሶ በሚል እየተገደመገሙ ነው። ከግምገማው በሁዋላ እርምጃ የሚወሰድባቸው የልዩ ሃይል አባላትማ የክልሉ ባለስልጣናት ...ይታወቃሉ።
ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በአበቦና በኢታንግ 5 የንዌር ተወላጆች መገደላቸው ታውቋል። አኝዋኮች በገዢው ፓርቲ የሚካሄደውን የሽምግልና ጥረት እንዳልወደዱት ምንጮች አክለው ገልጸዋል። መንግስት አንዱን ብሄረሰብ በመደገፍ በሌላው ላይ እንዲነሳ እያደረገነው በማለት ክስ ያቀርባሉ።
ደቡብ ሱዳናውያን ከክልሉ የማስወጣቱ ስራም እንደቀጠለ ነው።

አመራሮቻቸውን በገመገሙ ዜጎች ላይ የበቀል እርምጃ እየተወሰደ ነው
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ለውጥ አመጣለሁ በማለት በየአካባቢው ህዝባዊ ስብሰባዎችን እንዲያደርጉ የታዘዙት አመራሮች በርካታ ሚስጥሮች ስለወጣባቸው በጠቋሚዎች ላይ የብቀላ ድርጊት እየፈጸሙ መሆኑ ተነገረ።
በደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ በቅርቡ የአስፋልት መንገድ የሚያገኛትና ዘረፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሏት የተገነዘቡት የከተማዋ አመራሮች በከፍተኛ ደረጃ የመሬት ሽያጭ በማካሄድ የሰሩትን የሙስና ስራ ለማጋለጥ የሞከሩትን ባለሙያዎችና ነዋሪዎች ለመበቀል እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ሰሞኑን በተካሄዱ ህዝባዊ ስብሰባዎች መነገሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመላከተ።
በደቡብ ጎንደር ዞን ልዩልዩ ከተማዎች በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ በተደረ...ጉ ስብሰባዎች በባለስልጣናቱ ላይ ጥቆማ የሰጡ ወጣቶችንና ባለሙያዎችን በአደባባይ «በጥይት በሏቸው! »»እስከ ማለት የደረሱ የወረዳ አመራሮች እንዳሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) እድል የትዳር መፍረስ እንዲባባስ አንድ ምክንያት መሆኑን ከአ/ አ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ጠቆመ።
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንዶሚኒየም እጣ በሚወጣበት ወቅት በባለትዳሮች መካከል የጥቅም ግጭቶች እየተከሰተ የፍቺ ቁጥር እንዲያድግ አስተዋጾ አድርጓል።
በሌላ በኩል ባልና ሚስት ሁለቱም ኮንዶሚኒየም ለማግኘት ተመዝግበው እጣ ሲወጣ ሁለት ቤት ስለማይፈቀድ በስምምነት የውሸት ፍቺ የሚፈጽሙበት ክስተቶች እየተበራከቱ መጥተዋል።በተጨማሪም ለዲቪ ጉዞ ተብሎ የሚደረግ መጠናናት የሌለበት ጋብቻ እንዲሁም የውሸት ጋብቻ በተጨማሪ ምክንያትነት ተጠቅሰዋል ።
ተጋቢዎች የሚፋቱበትን ምክንያት ያለመናገር መብት ያላቸው በመሆኑ ፍ/ቤቶች ሆን ብለው አጥፊዎችን ለመቆጣጠር አላስቻላቸውም ተብሎአል። በ2006 ዓም 941 ሰዎች በአ/አ ከተማ ፍቺ የፈጸሙ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2007 ወደ 3747 አሻቅቦአል።

Wednesday, February 10, 2016
አርበኞች ግንቦት7 የውጭ ዘርፍ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ
የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ በውጭ አገር የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄ የውጭ ዘርፍ አባላት ከጥር 27 እስከ ጥር 29 ፣ 2008 ዓም የዘረፉን 1ኛ ጠቅላላ ጉበኤ አካሂደው፣ የውጭ ዘርፍ አመራሩ ባለፈው አንድ አመት ያከናወነውን የስራና የፋይናንስ እንዲሁም የተለያዩ ኮሚቴዎች ያቀረቡትን ሪፖርት ማዳመጡን ገልጿል።
በበጎ የተሰሩ ስራዎችን በማጠናከር፣ መሰራት ሲገባቸው ባልተሰሩት ስራዎች ላይ ሰፋ ያሉ አስተያየቶችን መካሄዱን ንቅናቄው በመግለጫው ጠቅሶ፣ በዘረፉ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት በመወያየት ህገደንቡን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የንቅናቄውን የውጭ ዘርፍ ሊመሩ የሚችሉ የአመራር አካላትንም መምረጡን ገልጿል። ...
ንቅናቄው የጀመረውን የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ እና አገር የማዳን ትግሉን በድል ለመወጣት ትግሉን አጠንክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

Tuesday, February 9, 2016
በጉጂ ዞን ተቃውሞው ቀጥሎአል
የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለወራት ሲንከባለል የቆየው የጉጂ ዞን ህዝብ የመብት እና የኢኮኖሚ ጥያቄ ከፌደራል እና ከክልሉ መንግስት ምላሽ መነፈጉን ተከትሎ ወደ አደባባይ የወጣው ህዝብ፣ ተቃውሞውን አጠናክሮ ቀጥሎአል።
ትግሉ በጎበዝ አለቃ እየተመራ በመካሄድ ላይ መሆኑን የተቃውሞው ተሳታፊዎች ይገልጻሉ።...
ተቃውሞውን ለመቆጣጠር የፖሊስ ሃይል በብዛት ቢሰማራም፣ ሊያስቆመው አልቻለም። የሼክ ሙሃመድ አላሙዲን የወርቅ ማምረቻ ኩባንያም ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገለት ነው። የድርጀቱ መኪኖች ከቦታ ቦታ መዘዋወር አቁመዋል።

ነዋሪዎቹ ሚድሮክ ወርቅ ከአካባቢያቸው ለቆ እንዲወጣ፣ የታሰሩት እንዲፈቱ እና ለወራት ያቀረቡዋቸው የመልካም አስተዳደር፣ የአስተዳደርና የአገልግሎት ጥያቄያቸው እንዲመለሱላቸው ይጠይቃሉ።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደሮችን ከመሬት ይዞታ ባለቤትነት የሚያፈናቅለውን ማስተር ፕላን በመቃወም ሰላማዊ ጥያቄያ ያነገቡ ከ140 በላይ ተማሪዎችና አርሶአደሮች መገደላቸው፣ ኢትዮጵያ ገና ያልተሻገረቻቸው የፖለቲካ ጥያቄዎች መኖራቸውን ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል።

በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲ አመራሮች በፍርድ ቤት ቀጠሮ እየተሰቃዩ ነው
የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ነጻ ያላቸውና አቃቤ ሕግ ይግባኝ በመጠየቁ ምክንያት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳያቸው በመታዬት ላይ ያሉት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሽ እና መምህር አብርሃም ሰሎሞን ዛሬ የካቲት 01 ቀን 2008 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል።
አቃቤ ሕግ በአቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሺ ላይ የሚቀርበው ከብሔራዊ ደኀንነትና መረጃ ማዕከል ተገኘ የተባለው ኦርጂናል ማስረጃ ያቀርባል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ማስረጃውን ለማቅረብ ተጨማሪ የአንድ ...ሳምንት ጊዜ እንዲሰጠው በጽሁፍ ጠይቋል።

ጸረ ሙስና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለመቆጣጠር አልቻልኩም አለ
የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የስነምግባርነሰ የጸረ ሙስና ኮሚሽን በመንግስት መ/ቤቶች ሙስናን ለመዋጋት ያዋቀራቸው የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች ውጤት እንዳላመጡ ከኮምሽኑ የተገኘ ሪፖርት ጠቁሟል።
ኮምሽኑ በመንግስት መ/ቤቶች የስነምግባር አውታሮችን በማደራጀትና በመደገፍ ሙስናን የመዋጋት ሚናቸውን እንዲወጡ ክፍሎቹን በሰው ሀይልና በቁሳቁስ እንዲደራጁ ቢያደርግም በተለያዩ ምክንያቶች ዉጤታማ መሆን አልቻሉም። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል የሙስና ወንጀልን ከማጋለጥ ይልቅ ተባባሪ መሆን፣ የሙስና ክሶችን መደበቅ፣ ከማኔጅመንት አባላት ጋር በመሞዳሞድ ሽፋን መስጠት፣ ችግሮችን በምን ቸገረኝነት አይቶ እንዳላየ ማለፍ፣ በሰራተኛው ዘንድ የስነምግባር መኮንኖቹን እንደ...ፖለቲካ ተሹዋሚ በማየት የመገለል ጫና መኖሩና የመሳሰሉት ችግሮች ተነስተዋል።
የአንድ መንግስታዊ መ/ቤት የስነምግባር መኮንን በሰጠው አስተያየት ተጠሪነቱ ለመ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መሆኑ፣ በአንጻሩ በማኔጅመንቱ የሚሰሩ የስነምግባር ጉድለቶችንና የሙስና ወንጀሎችን እንድንታገል መታሰቡ እርስበርሱ የሚጋጭ በመሆኑ መኮንኑ ስራውን ላለማጣት ሲል መጋጨትን አይፈልግም ብሎአል።
የመንግስታዊ ተቁዋማት የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች ውጤታማ አለመሆን ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲሰራፋ አንድ ምክንያት ነውም ተብሎአል። በፌዴራል መ/ቤቶች ብቻ 103 ፣በመንግስት የልማት ድርጅቶች 77፣ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 32፣ በአ/ አ ከተማ አስተዳደር 28፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 40 በድምሩ 280 የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች መኖራቸው ታውቆአል።
ኮምሽኑ በመንግስት መ/ቤቶች የስነምግባር አውታሮችን በማደራጀትና በመደገፍ ሙስናን የመዋጋት ሚናቸውን እንዲወጡ ክፍሎቹን በሰው ሀይልና በቁሳቁስ እንዲደራጁ ቢያደርግም በተለያዩ ምክንያቶች ዉጤታማ መሆን አልቻሉም። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል የሙስና ወንጀልን ከማጋለጥ ይልቅ ተባባሪ መሆን፣ የሙስና ክሶችን መደበቅ፣ ከማኔጅመንት አባላት ጋር በመሞዳሞድ ሽፋን መስጠት፣ ችግሮችን በምን ቸገረኝነት አይቶ እንዳላየ ማለፍ፣ በሰራተኛው ዘንድ የስነምግባር መኮንኖቹን እንደ...ፖለቲካ ተሹዋሚ በማየት የመገለል ጫና መኖሩና የመሳሰሉት ችግሮች ተነስተዋል።
የአንድ መንግስታዊ መ/ቤት የስነምግባር መኮንን በሰጠው አስተያየት ተጠሪነቱ ለመ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መሆኑ፣ በአንጻሩ በማኔጅመንቱ የሚሰሩ የስነምግባር ጉድለቶችንና የሙስና ወንጀሎችን እንድንታገል መታሰቡ እርስበርሱ የሚጋጭ በመሆኑ መኮንኑ ስራውን ላለማጣት ሲል መጋጨትን አይፈልግም ብሎአል።
የመንግስታዊ ተቁዋማት የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች ውጤታማ አለመሆን ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲሰራፋ አንድ ምክንያት ነውም ተብሎአል። በፌዴራል መ/ቤቶች ብቻ 103 ፣በመንግስት የልማት ድርጅቶች 77፣ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 32፣ በአ/ አ ከተማ አስተዳደር 28፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 40 በድምሩ 280 የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች መኖራቸው ታውቆአል።
አርበኞች ግንቦት7 የውጭ ዘርፍ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ
የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ በውጭ አገር የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄ የውጭ ዘርፍ አባላት ከጥር 27 እስከ ጥር 29 ፣ 2008 ዓም የዘረፉን 1ኛ ጠቅላላ ጉበኤ አካሂደው፣ የውጭ ዘርፍ አመራሩ ባለፈው አንድ አመት ያከናወነውን የስራና የፋይናንስ እንዲሁም የተለያዩ ኮሚቴዎች ያቀረቡትን ሪፖርት ማዳመጡን ገልጿል።
በበጎ የተሰሩ ስራዎችን በማጠናከር፣ መሰራት ሲገባቸው ባልተሰሩት ስራዎች ላይ ሰፋ ያሉ አስተያየቶችን መካሄዱን ንቅናቄው በመግለጫው ጠቅሶ፣ በዘረፉ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት በመወያየት ህገደንቡን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የንቅናቄውን የውጭ ዘርፍ ሊመሩ የሚችሉ የአመራር አካላትንም መምረጡን ገልጿል።
ንቅናቄው የጀመረውን የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ እና አገር የማዳን ትግሉን በድል ለመወጣት ትግሉን አጠንክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ግንቦት7 እና አርበኞች ግንባር ውህደት ከጀመሩ በሁዋላ ንቅናቄው ያካሄደው የመጀመሪያው የውጭ ዘርፍ ጉባኤ ነው። ትግሉን መሬት ላይ የሚያካሄደው ሌላው ወታደራዊ ዘርፍ ቀደም ብሎ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወቃል።

Monday, February 8, 2016
በጉጂ ዞን ህዝቡ "በቃኝ" በማለት ትግሉን እንደቀጠለ ነው
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ የፌደራል ፖሊስ አባላት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አካባቢውን ተቆጣጥረውታል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችና አዛውንቶች ታስረዋል። ይሁን እንጅ "ህዝቡ የጎበዝ አለቃ መርጦ ትግሉን በጥንቃቄ እና በወኔ እያካሄደ ነው። ትግሉ መቆሚያ የለውም" በማለት በተቃውሞው ላይ የሚሳተፉ አንድ ግለሰብ ለኢሳት ተናግረዋል።
የጉጂ ህዝብ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትና የኢኮኖሚ ነው የሚሉት ግለሰቡ፣ ባለፉት አመታት ችግሮቻቸው እንደሚፈቱ በርካታ ቃሎች ቢገቡላቸውም፣ አንዱም ተፈጻሚ አልሆነም።
የሼክ አላሙዲን ሚድሮክ ወርቅ የተቃውሞው ዋነኛ ኢላማ ሆኗል። የአካባቢው ህዝብ በድህነት እየተሰቃዬ፣ ባለሃብቱ የአካባቢውን ሃብት መዝረፋቸው ፍትሃዊ ባለመሆኑ፣ ከእን...ግዲህ የአላሙዲንን ኩባንያ በሻኪሶ ልናየው አንፈልግም ሲሉም ግለሰቡ ያክላሉ።
የኢህአዴግ መንግስት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን አሰማርቷል። አንዱ ወረዳ ከሌላው ጋር እንዳይገናኝ መንገዶችን ዘግቷል፤ የስልክ መስመሮችን በየጊዜው ያጠፋል፣ መብራት ያቋርጧል፤ ከዚህም አልፎ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስቦ ለጥያቄያቸው አፋጣኝ መልስ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ይሁን እንጅ ህዝቡ የኢህአዴግን ቃል አምኖ የሚቀበል አልሆነም ፣ እንደ ገልሰቡ ገለፃ።
በዛሬው ተቃውሞ የመንግስት ስራተኛው ሰይቀር መውጣቱንም ግልሰቡ ይናገራሉ።

እነ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በጋምቤላ የሚመሩት የሽምግልና ጥረት እስካሁን አልተሳካም
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮች እና የአርብቶአደር አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃንን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ የመከላከያ አዛዡ ጄ/ል ሳሞራ የኑስና ሌሎች ወታደራዊ አዛዦች እንዲሁም የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋምቤላ ገብተው ኑዌሮችና አኝዋኮችን ለማስታረቅ እንቅስቃሴ እያደረጉ ቢሆንም፣ ሽምግልናው ግን እስካሁን ውጤት አላመጣም። የአኝዋክ ሰርቫይቫል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኒካው ኦቻላ፣ መንግስት የሽምግልና ጥረት የጀመረ በመምሰል ፣ ችግሩ እንዲባባስ የሚያደርገው ድርጊት ከግጭቱ ጀርባ እጁ እንዳለበት የሚያመላክት ነው ይላሉ።
በክልሉ በየየቀኑ ሰዎች እየሞቱ ሲሆን፣ በኢታንግ ቅዳሜ እለት 2 አኝዋኮች ተገድ...ለዋል። ባለፈው አርብ ደግሞ ከፒዩንዶ የስደተኞች ካምፕ የወጡ ኑዌሮች 3 የአኝዋክ ሴቶችን ገድለዋል። ከሟቾች መካከል የ7 አመት ሴት ልጅ ትገኝበታለች። በጋምቤላ ከተማም እንዲሁ አንድ የ45 አመት ሴት ተገድላለች።
ከደቡብ ሱዳን መጥተው በጋምቤላ የሚኖሩ ስደተኞችን በአንድ ላይ ሰብስበው ወደ ድንበር እያጓጓዙዋቸው ነው።
አቶ ኒካው እንደሚሉት፣ አንዋኮች ምንም ችግር እንደሌለባቸውና ችግሩ በንዌሮች እንደተጀመረ በስብሰባ ላይ ቢነገርም እስካሁን ይህ ነው የሚባል ምላሽ አልተሰጠም። የታጠቁ ንዌሮች በማንኛውም ሰአት ጥቃት እየፈጸሙ ነው፡፡ በአኝዋኮች በኩል ደግሞ ይህን የሚያደርጉት ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሪክ ማቻር ወታደሮች ሆነው ሳለ ለምን እርምጃ አይወስድም በማለት እየጠቁ መሆኑን አክለዋል። እርቅ ይደረጋል ቢባልም የመንግስት እጅ እንዳለበት የሚያመላክቱ ጉዳዮች መኖራቸውን አቶ ኒካው ገልጸዋል።
ከ30 በላይ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን የጦር አዛዦች በ መንግስት ቁጥጥር ስር ሆነው የተወሰኑት ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።

በኮንሶ የልዩ ሃይል ፓሊስ አባላት ጉዳት እያደረሱብን ነው ሲሉ ወጣቶች ተናገሩ
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከኮንሶ የአስተዳደር ክልል ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር በአካባቢው የተሰማሩ የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት ፣ መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን ወጣቶች በመደብደብ አካላዊ ጉዳት እያደረሱባቸው መሆኑን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ወጣቶች ተናግረዋል።
ወጣቶቹ በፎቶ አስደግፈው በላኩት መረጃ፣ የፖሊስ አባላት በወጣቶች ላይ ድብደባ በመፈጸም፣ ማንኛውም የአካባቢው ወጣት ጥያቄ እንዳያነሳ ለማድረግ ይሞከራሉ ብለዋል።
በኮማንደር ፍስሃ ጋረደው የሚታዘዘው ልዩ ሃይል ጥር 26፣ 2008 ዓም ለሚ በርሻ የሚባል ወጣት ክፉኛ ተድብድቧል። ከእርሱ ጋር የነበሩ 14 ወጣቶም ተመሳሳይ ድርጊት ከተፈጸመባቸው በሁዋላ በአሁኑ ሰአት የት እንዳሉ... አይታወቅም።
የልዩ ሃይል አባላት ከሚፈጽሙት የሰብአዊ መብት ጥሰት በተጨማሪ፣ ሜዳ ላይ ያገኙዋቸውን ፍየሎችና በጎች እየዘረፉ እንደሚበሉ ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።

ከፍተኛ የፖሊስ እጥረት ተፈጠረ።
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚካሄደውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ተከትሎ የፖሊስ እጥረት በማጋጠሙ፣ መንግስት ስልጠናቸውን ያላጠናቀቁትን ከማሰልጠኛ በማውጣት ከማሰማራት በተጨምሪ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የፖሊስ ልብስ እያለበሰ በማሰማራት ላይ ነው።
አብዛኛው የፌደራል ፖሊስ አባላት በኦሮምያ የተሰማሩ ሲሆን፣ በጋምቤላ እና በአማራ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የፖሊስ አባላትም ተሰማርተዋል። በክልሎች የሚታየው ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ፣ መንግስት የመከላከያ አባላትን በፖሊስ ዩኒፎርም እያሰማራ ከመገኘቱም በላይ ስልጠናቸውን ያልጨረሱ ፖሊሶች ሳይቀር ወደ ክልሎች እየዘመቱ ነው። በዚህም የተነሳ የመንግስት ተቋማትን የሚጠብቁ ፖሊሶች ቁጥር በማነሱ፣ ብዙዎቹ ፖሊሶች 24 ሰአታት ያለ እረፍት እንዲሰሩ ተደርጓል። አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል፣ "አሁን ያለንበት ሁኔታ በ97 ከነበረው ጋር ሲተያይ የከፋ እንጅ የተሻለ አይደለም" ብሏል። ፖሊሶች እረፍት የሚባል ነገር ሊያገኙ ባለመቻላቸው እንዲሁም ከህዝቡ ጋር መጋጨታቸውና በየጊዜው የሚደርስባቸው ውግዘት እየከበዳቸው ጥለው የሚጠፉ ፖሊሶች መብዛታቸው ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ እንዳደረገውም ፖሊሱ ተናግሯል።

መምህራን አድማ መቱ
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ የሚገኘው የደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ''የትምህርት ጥራት ይጠበቅ '' በማለት የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።
ዛሬ ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም ተማሪዎች የአንደኛ ሴሚስተር እረፍታቸውን ጨርሰው ወደ ትምህት ቤቱ ቢያቀኑም መምህራን አድማ በማድረጋቸው በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም። ተማሪዎቹ በበኩላቸው ''የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!'' የሚለውን መፈክር በማሰማት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።
አድማውን ከመቱት መምህራን አንዱ ‹‹በክልሉ የሌለ አሰራር በመከተል በትምህርት ቤቱ 4 ምክትል ርዕሰ መምህራን ተሹመውብን ቆይተዋል፤ ይህ መመሪያ ይጥሳል ብለን ታግለን አስወረድናቸው፡፡ ነገር ግን ከወረዱት መካከል አንዱን ርዕሰ መምህር አድርገው እንደገና ሾሙት፡፡ በዚህም ችግሩ ተባብሶ ቀጠለ፤ እኛም ድርጊቱ ትምህርትን ይጎዳል ብለን ከዛሬ ጀምሮ አድማ ልናደርግ ችለናል›› ሲሉ ስለ ሁኔታው ለነገረ-ኢትዮጵያ አስረድተዋል። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ካሉ በመቶች ከሚቆጠሩ መምህራን መካከል አብዛሃኞቹ የአድማው ተካፋይ መሆናቸው ታውቋል። የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤትና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር በበኩላቸው የመምህራኑን ፍትሐዊ ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ፣ ሰማያዊ ፓርቲን እንጂ ኢህአዴግን አትቀበሉም በማለት ችግሩን ፓለቲካዊ መልክ ለማስያዝ እየሞከሩ መሆኑን ነገረ - ኢትዮጵያ አክሎ ዘግቧል።

Sunday, February 7, 2016
አንድ የመተማ ነዋሪ 6 የወያኔ ወታደሮችን ረሽኖ በመጨረሻ እራሱን በክብር ሰውቷል !!!
ባሳለፍነው ሳምንት በመተማ ወረዳ ውስጥ ከቅማንት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለአማራ መብት ሲቆረቆር የነበረን ወጣት ለማፈን በአካባቢው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባሎች ወደ ልጁ ቤት ይሄዳሉ። ልጁ እጁን አልሰጠም ተኩስ ገጠማቸው ። እናም 6 ወታደሮችን ገደለ ። በመጨረሻም በእራሱ መሳሪያ እራሱን አጠፋ።
አካባቢው ላይ ለአማራነት የሚቆረቆሩ የተወሰኑ ወገኖቻችን ታስረዋል። እስረኞች ከአካባቢው ወጥተው ወደ ሌላ ቦታ እንዳይወሰዱ የታጠቁ ወገኖቻቸው በር በሩን ይዘው ሌት ተቀን በመጠበቅ ላይ እንዳሉ የቤተ አማራ ምንጮች አሳውቀዋል። ብዙ ልጆች መሳሪያ ታጥቀው ሸፍተዋል። የቅማንቱ ጉዳይ እንደገና ሊያገረሽ እንደሚችል ተፈርቷል። በሕወሓት የሚታገዙት የቅማንት ጠበቃ ነን ባዬች አሁንም ትንኮሳቸውን አለተውም።
የቴዎድሮስ አንበሶች ድንበራቸውን እና አማራነታቸውም በደማቸው አስከብረው ሊያልፉ ተዘጋጅተዋል።
የሞተውን ጀግና ወንድማችንን ነብስ ይማር!

Saturday, February 6, 2016
SPLA IO high officials arrested in Ethiopia
SPLA-IO high Ranking Commanders has been arrested by Ethiopia Regional Police of Gambella (ERPG) yesterday their names are as follows
1- Lt Gen.Dor Manjur Gatluak
2- Lt Gen.Thomas Mabor Dhol
2- Lt Gen.Thomas Mabor Dhol
the names of others Comrades who were also arrested will be publishes sooner.
Reported by SSAF spokesperson Capt. Kim Lony Gatluak
በኦሮሚያ በጉጂ ዞን ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጋምቤላና በመላው ኢትዮጵያ የድንበር አከባቢዎች ውጥረቱ ተባብሷል::
ለስር ነቀል ለውጥ የትግል ስትራቴጂ የሚነድፍ የሚቀይር ወይም የሚቀይስ ምነው ጠፋ???#Ethiopia
በኦሮሚያ በጉጂ ዞን ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጋምቤላና በመላው ኢትዮጵያ የድንበር አከባቢዎች ውጥረቱ ተባብሷል:: #Oromoprotests#Gambella #MinilikSalsawi #EPRDF
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክፍለሃገር የተጀመረው ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን በጉጂ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ተቃውሞው ተፋፍሞ የቀጠለ መሆኑ ሲታወቅ በሚድሮክ የወርቅ ማእድን ማውጫ በስሩ የሚገኘው የጉጂ ዞን ነዋሪዎች በገዛ አከባቢያችን ጥቅማችን ተደፍሯል የመስራት ሕልውናችን ተገፏል ጉልበታችን እና የተፈጥሮ ሃብታችን በሕወሓት እና በቢስነስ አጋሩ በአላሙዲ እየተበዘበዘብን ስለሆነ ሚድሮክ ለቆ ይውጣልን ያስረክበት የሚል ድምጻቸውን ያሰሙ ሲሆን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የጅምላ ግድያው እንዲቆም ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ::
Friday, February 5, 2016
በጋምቤላ ውጥረቱ አይሏል * እናት እና ህፃን ልጇ ተገደሉ * ፒኙዶ ከተማ የጦር አውድማ መስላለች
(ዘ-ሐበሻ) የፌደራል መንግስት የኑዌር እና የአኝዋክ ብሄረሰቦችን ለማስታረቅ ከጋምቤላ በስተደቡብ 105 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ፒኙዶ ከተማ ላይ ስብሰባ ጠርቶ ስብሰባው እየተካሄደ ባለበት ወቅት የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ድንገት በወሰዱት እርምጃ እናት እና የ2 ዓመት ህፃን ልጇ ዛሬ መገደላቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው አስታወቁ::
ዘ-ሐበሻ በስልክ ያነጋገረቻቸው የዓይን እማኞች እንደሚገልጹት ፒኙዶ ከተማ የደቡብ ሱዳን አማጽያን የሪክ ማቻር ወታደሮች የሚኖሩባትና የስደተኞች ካምፕ የሚገኝበት ቦታ እንደሆነ ገልጸው ድንገት ስብሰባው እየተደረገ እርምጃውን የወሰዱት እነዚሁ የሪክ ማቻር ወታደሮች የሆኑ የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ናቸው ብለዋል::
የአይን እማኞቹ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ የከ እናት እና ልጅ በተጨማሪ ሌላም አንድ ሰው ሕይወቱ ማለፉን እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል:: የፌደራል መንግስት ሁለቱን ብሄረሰቦች ለማስማማት ስብሰባ ጠርቶ ኑዌሮች ድንገት እርምጃ ሲወስዱ የፌደራል ወታደሮች ግጭቱን ከማብረድ ይልቅ ዳር ቆመው ይመለከቱ ነበር ሲሉ እነዚሁ የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
በሌላም በኩል በጋምቤላ ኦሚንጋ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከ2 ቀናት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት በጠሩት ስብሰባ ላይ ሕዝቡን ወክሎ በስብሰባ ላይ ሲናገር የነበረውና በቅጽል ስሙ ሶኒ ተብሎ የሚታወቀው ወጣት ዛሬ ባልታወቁ ሰዎች ወገቡን ተምትቶ በጋምቤላ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኝ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል::
በጋምቤላ በተለይም ከፓንጋ ወደ ፒኙዶ የሪክ ማቻር ስደተኛ ወታደሮች በከ

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር እንዲለቀቁ ተጠየቀ።
ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ መንግስት እንደማያስራቸው የሰጣቸውን ዋስትና አምነው ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የአክሰስ ሪል ስቴት መስራች አቶ ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ጥር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ ይገኛሉ።
አቶ ኤርሚያስ ሰሞኑን ጥር 23 ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የህግ አማካሪያቸውና ጠበቃቸው አቶ ሞላ ዘገዬ የደንበኛቸው መታሰር አግባብ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
እንደ አቶ ሞላ ገለፃ አቶ ኤርሚያስ የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ሳይለይ መታሰራቸው ከሕግ አግባብ ውጪ ነው።
አቶ ኤርሚያስ የተጠረጠሩበት ድርጊት ወንጀል ወይም ፍትሐ ብሔር መሆኑ እንዳልተለየ የገለጹት ጠበቃው፤ <<ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ...በት ድርጊት ሳይለይ፣ እሳቸውን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገቢና ሕግን የተከተለ አይደለም>> ብለዋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ በተጠረጠሩበት ድርጊት ማስረጃ ቀርቦባቸዋል ቢባል እንኳን ዋስትና የሚያስከለክላቸው ሊሆን እንደማይችል የተናገሩት አቶ ሞላ፤ ያላቸው ማንኛውም ዓይነት ሀብት ዕግድ ስለተጣለበት የሚያሸሹትም ሆነ የሚሸሽጉት ነገር ስለሌለ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የምስክርነት ቃሉን ሰጠ
ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተብሎና 18 አመት እስር ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመከላከያ ምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡
ጋዜጠኛ እስክንድር -በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ አንደኛ ተከሳሽ ለሆነው አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ መከላከያ ምስክር ሆኖ ዛሬ ጥር 27/2008 ዓ.ም ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በመቅረብ ምስክርነቱን አሰምቷል።

ያለጠበቃ በግሉ የሚከራከረው ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ጋዜጠኛ እስክንድር እንዲያስረዳለት የሚፈልገው ጭብጥ፤ "ጡመራ ምንድነው?፣ ከወንጀል ጋርስ ግንኙነት አለው ወይ? እና ሰብዓዊ መብት እና ዴሞክራሲ ላይ ስልጠና ስለሚሰጡ ድርጅቶችና የስልጠናው ይዘት ምን ይመስላል?" የሚሉትን ነጥቦች እንደሆነ ቢያስታውቅም፤ በጭብጡ ላይ እንዳይመሰክር አቃቤ ህግ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡
አቃቤ ህግ ተቃውሞ ያሰማው-"ጡመራ ምንድነው? ወንጀልስ ነው ወይ?" የሚለው፤ በምስክር ሳይሆን በህግ ድንጋጌዎች የሚረጋገጥ ነው በማለት ነው፡፡
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ጡመራ ወንጀል ስለመሆን አለመሆኑ የተያዘውን ጭብጥ ውድቅ በማድረግ -ስለ ስልጠናውና አሰልጣኝ ተቋማት የተመዘገበው ጭብጥ ላይ ምስክሩ እንዲመሰክሩ ብይን ሰጥቷል፡፡

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ በኢትዮጵያ ግድብ ጉዳይ የግብጽን አቋም እንደምትደግፍ አስታወቀች
ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንጐ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦገስቲን ማታታ ፖኖዮ ካይሮን ሲጎበኙ ከግብጹ አቻቸው ከሸሪፍ ኢስማኢል ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፤ ከአባይ ወንዝ የምታገኘው ድርሻ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያመጣብኛል ብላ መስጋቷ አግባብ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ለዚህ የካይሮ አቋም ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡
የኮንጎው ጠቅላይ ሚኒስትር አክለውም፦" የኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ ያለንን አቋም በግልጽ አሳውቀናል፤ ሁለልጊዜም ድጋፋችን ለግብጽ ነው" ብለዋል፡፡
የግብጹ አቻቸው ሸሪፍ ኢስማኤል በበኩላቸው ኮንጎ- በኮንጎ ወንዝ ላይ እየገነ...ባች ላለው ታላቅ ግድብ ግብጽ ድጋፏን እንደምትሰጥ አማረጋገጣቸውን የ አህራም ኦንላይን ዘገባ ያመለክታል።

በጉጂ ዞን ሚድሮክን በማውገዝ ተቃውሞው ተባብሶ ሲቀጥል፤ በአዲስ አበባ ሚድሮክ ፕሮጀክቱን ተነጠቀ።
ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጉጅ የተለያዩ ወረዳዎች አደባባይ የወጡ የተቃውሞ ሰልፈኞች በዋኘኝነት ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኩባንያ ከአካባቢው እየፈጸመ ነው ያሉትን የወርቅ ማእድን ዝርፊያ ተቃውመዋል።
"በሰልፉ ላይ የነበሩ ገበሬዎች፦" ኦኮቴ የኛ መሬት ነው፤ አል አሙዲ የኛ ጠላት ነው" የሚል መፈክር ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
"ኦኮቴ" የሸህ መሀመድ አል አሙዲ ንብረት የሆነው ሚድሮክ ኩባንያ ማእድን ከሚያወጣባቸው ቦታዎች አንዱ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚድሮክ ኩባንያ በአዲስ አበባ የሚያካሂደውን የመንገድ ስራ ተነጠቋል።...
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከጥራትና አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሁለት ስራ ተቋራጮችን ኮንትራት ማቋረጡን የጠቀሰ ሲሆን፤ እርምጃ የተወሰደባቸው ኩባንያዎች ሚድሮክ ኮንስትራክሽን እና ትድሃር ኮንስትራክሽን መሆናቸውን ገልጿል።
የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ሃይሌ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በቦርዱ ውሳኔ መሰረት ስራው እንዲነጠቅ መደረጉን ተናግረዋል።
ኩባንያው ከመገናኛ ካፒታል ሆቴል ጀምሮ እስከ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ ያለውን መንገድ ለመስራት ውል ገብቶ ሥራውን ቢረከብም፥ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ግንባታውን ባለማከናወኑ ግንባታው እንዲነጠቅ መደረጉን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
ትድሃር ኮንስትራክሽን በተመሳሳይ የተረከባቸውን የመንገድ ፕሮጀክቶች በተቀመጠለት ጊዜ አጠናቆ ባለማስረከብና በታክስ ማጭበርበር ወንጀል መከሰሱን ተከትሎ ስራውን እንደተነጠቀ ተገልጿል።
ከዚህም ባሻገር የመንገድ ፕሮጀክት ስራ ያጓትታሉ በሚል ምክንያት ሳትኮን ኮንስትራክሽን፣ አፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽንና ኢትዮ ጄንራል ኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ በሚያወጣቸው ማንኛውም ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ መከልከላቸው ተወስቷል።

አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን በጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዐቃቤ ሕግ ጋር የቃል ክርክር አደረጉ
ዐ/ሕግ በጥቅምት ወር 2008 በፌ/ከ/ፍ/ቤት የሽብር ክሳቸው ተነስቶላቸው የተሰናበቱት አምስቱ ጦማሪያን ላይ «ማስረጃችን አልተመዘነም፣ በተከሰሱበት ወንጀል ሊከላከሉ ይገባል» በማለት ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ማለቱ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ጥር 27፣ 2008 አራቱ መልስ ሰጪዎች በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ እና አቤል ዋበላ ከጠበቆቻቸው አምሀ መኮንን እና ሽብሩ በለጠ ጋር ቀርበው ለይግባኙ መልስ ሰጥተዋል።
ይግባኝ ባይ በስር ፍ/ቤት «ከመጀመሪያ ጀምሮ የቡድኑን ሥም ካልገለጻችሁ እያተባልን፣ የቡድን አደረጃጀት ገልጸን አልገለጻችሁም እየተባልን ማስረጃዎቻችን አልታዩልንም። 1ኛ መልስ ሰጪ ቤት የግንቦት 7 እና የኦነግ ፕሮግራም ተገኝቷል። ቡድኑ የግብፅን አብዮት ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የሠለጠኑበት የተለያዩ ሰነዶች ተያይዘዋል። 2ኛ መልስ ሰጪ አመፅ ሊያነሳሳ ማሰቡን አምኗል፣ የቀረቡበት ማስረጃዎችም ይህንኑ ያስረዳሉ በሚል በወንጀል ሕጉ 257/ሀ መሠረት ይከላከል ከማለቱ በቀር በጥቅሉ መልስ ሰጪዎች በቡድን ‘እንዴት የግብፅን ዓይነት አብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ መቀስቀስ ይቻላል?’ በሚለው ላይ የተጻጻፏቸውን፣ እና የወሰዱትን ሥልጠና የሚያስረዱ በርካታ ሰነዶች ተይዘዋል። ከያንዳንዳቸው ኮምፒዩተሮች የወጡት ሰነዶች የሚያስረዱት፣ እንዴት አመፅ ማነሳሳት እንደሚቻል ነው። አንዱ መልስ ሰጪ ላይ በእጅ ጽሑፉ እንዴት ፈንጂ ማላቆጥ እንደሚቻል የሚገልጽ
ጽሑፍ ተገኝቷል። ስለሆነም ማስረጃዎቼ በስር ፍ/ቤት አልታየልኝም፣ በመጀመሪያው ክስ ይከላከሉ።» ብሏል።

Thursday, February 4, 2016
በጉጂ ዞን ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ቀንና ሌሊት እየተካሄደ ነው
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነጋዴው፣ የመንግስት ሰረተኞች፣ አርሰዶአሮችና የአካባቢው ህዝብ ቀንና ሌሎት ህዝባዊ እንቢተኝነቱን እየገፉበት መሆኑን ያነጋገርናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። ለ25 ዓመታት ዝርፊያ ሲያካሂድ የቆዬው የሼክ አላሙዲን የወርቅ ኩባንያ ከአካባቢው እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በቡሌ ሆራ የጉምሩክ ጽ/ቤት ተቃጠለ
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦረና ዞን በቡሌ ሆራ ወረዳ አንድ መኪና ኮንትሮባንድ ጭኖ አልፏል በሚል ምክንያት የጉምሩክ ጠባቂዎች መኪናውን እናስቆማለን በሚል የተኮሱት ጥይት አቶ ንጉሴ ጉዬ የተባሉትን ሰው ጭንና ትከሻቸው ላይ ማቁሰሉን ተከትሎ ለወትሮውም ቋፍ ላይ የነበረው ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ጉሙሩኩን ሙሉ በሙሉ አቃጥሎታል።
በአዋሳ አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህል አዳራሽ ክፍለከተማ አዳሪ ቀበሌ ልዩ ስሙ አድማስ መንደር በተባለ ቦታ ላይ በ30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወጣት ጨንቅላቱ አካባቢ በፖሊስ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ የአካባቢው ህዝብም ቁጣውን ሲገልጽ አርፍዷል።
ከወልቃይት ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ታሰሩ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች ባደረሱን መረጃ መሰረት አዛዡ ኮማንደር ውለታው ትናንት ምሽት ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የፖሊስ አዛዡ ድንገት ለ እስር የተዳረጉት የጎንደር ተወላጅ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ "የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ደጋፊናቸው" ተብለው ነው።

የጋምቤላ ኒሎትአንድነት ሰራዊት ንቅናቄ የህወሃት ኢሕአዴግ መንግስት በክልሉ የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልበአስቸኳይ እንዲያቆም ጠየቀ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መግለጫ ሕወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ የአኝዋክ ብሔር አባላት ላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን አስታጥቆ የሚፈጽመውን ግድያ
በአጽንዎት በመኮነን ፤ አገዛዙ ድርጊቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም ሲል ጠይቋል።

በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ላይ ፍርድቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ ተከሳሾቹ ችሎቱ እንዲቀየርላቸው ጠየቁ
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ እየተጉላሉ መሆናቸውን በመግለጽ ችሎት እንዲቀየርላቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አሰሙ።
ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ እስር ቤት ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ተገለፀ
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር ተሻግረው ወደ ማላዊ ገብተዋል ተብለው በአገሪቱ ፍርድ ቤት ቀርበው እስር የተፈረደባቸው ኢዮጵያዊያን ስደተኞች በእስር ቤቱ ውስጥ ሰብዓዊ መብታቸው ተጥሶ አስከፊ በሆነ አያያዝ በደል እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ሴቭ አወር ሳውል SOS የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታወቀ።
ዛሬ በአዋሳ ከተማ በወያኔ ፖሊስ የተፈፀመ አሰቃቂ ግድያ!፡፡
ግድያ ተጧጥፏል በያከባቢው ዛሬም 4 ሰአት አከባቢ በአዋሳ ታቦር ትምህት ቤት አከባቢ ይህ ወገን በፖሊስ ጥይት እንዲህ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሏል ‹‹ስለት ይዘህ ሰው አስፈራርተሀል›› በሚል በጥይት እበንደህ ሁኔታ ደፍተውታ፡፡
ፖሊሶቹ በግፍ የገደሉትን ሰው አስክሬን አድበስብሰ በመወስድ ለመቅበር ሲሞክሩ ከአከባቢህ ህዝብ ጋር ግጭት ተፈጥሮም ነበር የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ ጣቃ በመግባት በአስለቃሽ ጪስ በመወርውር ለተቃውሞ የተወጣውን ሰው በመበተ አስክሬኑን መውሰድ ችለዋል፡፡
Government detains a committee representing the people of Wolkait
ESAT News (February 04, 2016)
A 14 member committee representing the people of Wolkait was detained by authorities while they were in Addis Ababa to file formal complaints by the Wolkait people who demanded that they be incorporated to the Amhara region, as they were Amharas, opposing their current status under the Tigray region. The Wolkait people have been challenging the government saying their region was forcefully incorporated under the Tigray region 25 years ago when the ruling Tigrayan party, TPLF, took control of the central government.
Members of the committee were taken into custody while they were on their way out from the House of the Federation, Ethiopia’s upper house, after presenting their official complaints representing the people of Wolkait.
A vocal representative of the Wolkait in North America, Chalachew Abay told ESAT that the whereabouts of the 14 people is not yet known.
The Wolkait-Tegede region was historically with in the Gondar region of Amhara, but the ruling TPLF incorporated the region to Tigray 25 years ago, in what was seen as an attempt to integrate huge tract of fertile land to the otherwise barren region of Tigray. The people have since been demanding their identities to be respected as Amharas and their region to be incorporated back to Gondar.
Wednesday, February 3, 2016
22 የሚሆኑ የወልቃይት አማራ ብሔር ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በማእከላዊ ታስረው በሽብር ተከሰው ተፈቱ::
ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የታገዱት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአካባቢ ሽማግሌዎች ሰኞ ጥር 23 ቀን 2008 ወደ መዲናችን መግባት ችለው ነበር፡፡
የትግራይ ክልል ኮሚቴዎቹና ኅበረተሰቡ በወጡትበት ይቅርታ ጠይቀው በቶሎ ካልተመለሱ እርምጃ እንደሚወስድ በትግርኛ ቴሌቪዥን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠቱም ይታወሳል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ቁጥራቸው 22 የሚሆኑ ተወካዮች ለፌደሬሽን ምክር ቤትና ለፌደራል ጉዳዮች ቢሮ አቤቱታቸውን ለማሰማት ከቀኑ 7፡00 ላይ ሃያ ሁለት አካባቢ ከጓደኞቻቸው ተለይተው ሒደው ነበር፡፡ ነገር ግን እስከ ምሽት 2፡00 መመለስ አልቻሉም፡፡
ምሽት 2፡30 ሲሆን 22ቱም የኮሚቴ አባላት መሉ በሙሉ መታሠራቸውን ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ የታሠሩበትን ፖሊስ ጣቢያ እያጣራን ሲሆን እስካሁን እንደታሰሩ ስማቸው የደረሰን የወልቃይት ኮሚቴ አባለት

ESAT News (February 02, 2016)
Reliable sources in Gambella, Ethiopia told ESAT that the number of people being killed in the conflict between the Nuers and Anuak in Gambella is on the rise. The sources said over 10 people were killed on average on both sides every day since the recent crises began two weeks ago. The killings were reported in Gambella town, Abol, Belere, Etang, Betrifam, Pignang, Abobo, Alero and other localities including refugee shelters.
The Gambella region has been under the control of federal armed and security forces since Saturday. Sources say the head of security for the regime in Addis, Getachew Asefa and senior military commanders are in Gambella.

Reports of torture in Kaliti and Konso prisons
ESAT News (February 03, 2016)
The Human Rights League of the Horn of Africa reports torture of inmates in the notorious Kality Prison, on the outskirts of the capital Addis Ababa. The prisoners, who hail from the Oromia region of Ethiopia and detained after taking part in the recent protest in the region were reportedly made to strip and brutally beaten by the prison guards.

ሰውየው ---ብርሃኑ ነጋ - - አጭር ፍቅር ( ሄኖክ የሺጥላ )
ሰውየው ሕልም አለው ። የአንደበቱ ርትዖነት ካለው የቃላት አጠቃቀም እና ልቀት ሳይሆን የሚመነጨው ከሃሳቡ ጠጣርነት እና ከቆመለት ትልቅ እውነት እንጂ !
ሰውየው ሕልም አለው ፣ ለዚያውም በሞቀ ቤት እና በቀዘቀዘ ቢራ ውስጥ በሚደረግ የሳይበር ጦርነት የሚጸና ሳይሆን ፣ የማሽላ እንጀራ እየበላ አፈር ላይ እየተኛ ፣ ከእባብ እና ገጊንጥ ጋ እየተታገለ ፣ በሞርታር እና በፈንጂ ወረዳ ውስጥ ውድ ነብሱን አቁሞ የሚሞትለት እጹብ ሕልም ።

ሰወየው ትሁት ነው ፣ የትልቅነት ሚስጥሩ ምን እንደሆነ የገባው ትሁት ። ሕልሙ ባለ ወፍራም ቆዳ ያደረገው እንደራሴ ፣ አላማው ለትንንሽ ነገሮች እና በትንንሽ ነገሮች ከማኩረፍ እና ከመኮፈስ ነጻ ያወጣው የኔ ዘመን በትረ አሮን ። በግልምጫ እና በእርግጫ ፖለቲካ ውስጥ ሊባክን የሚችል ታል-ኢት ( የሰኮንድ ግማሽ ) የሌለው ሰው ። ሰውየው አፋር ነው ሃገሩ ፣ ጎጃሜም ነው ፣ በኦሮሞነቱ አይታማም ፣ ጥርት ያለ ጉራጌ ነው ፣ ዘሩን የቆጠሩ ሱማሌ ስለመሆኑ ይናገራሉ ፣ አብረውት ያደጉት እና በቅርብ የሚያውቁት ስለመንዜነቱ የሚያውቁትን ሁሉ ሳይደብቁ ያወራሉ ፣ እርግጥ ሰውየው ኢትዮጵያዊ ነው ። ማነስ አይችልም ፣ በጎጥ እና በጎሳ ፣ በአውራጃ እና ወረዳ ፣ ተቆርሶ እና ተሰባብሮ የሚነገር ማንነትም ሆነ ፣ የሚቆጠር ደም የለውም ። ሕሉሙ ከደሙ ጋ አንድ አይነት ነው ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና ዘረ ኢትዮጵያዊ ፣ ሰወየው !
ስለ ሰውየው ሳስብ ኩራት ይሰማኛል ፣ ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት እንደማይሞት ምሳሌ ሆኗልና ፣ ቃሉን አላጠፈምና ፣ የሚኖርለት ሰው ባይኖር እንኳ የሚሞትለት ክብር እና ነጻነት ያለው ስለሆነ ። በቅርቡ ዋሽንግተን ዲስ ባደረገው ንግግር " እዚህ ውስጥ ብዙ የማውቃችሁ ጓደኞቼን ወዳጆቼን አይቻለሁ ፣ ሁሌ አስባችሗለሁ ፣ ላናንተ ብዬ ግን ከምሄድበት አልቀርም " የምትለዋን ሐረግ ድግሜ ደጋግሜ አደመጥኩ ፣ በእድሜ የሱ እኩዮች የሆኑ ፣ እንደሱ ወይም ከሱ በላይ የተማሩ ፣ ሀገር ሀገር የሚሉ ግን አንዳች ቁም ነገር ያለው ሥራ መስራት ያልቻሉት ወዳጆቹ ምን ይሰማቸው ይሆን ? እነዚህ በጥላቻ እና በማጥላላት የፖለቲካ ቁማር የሰከሩ << የፖለቲካ ቁሞ ቀሮች >> ወይም ዊዶዎች ይህንን ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን ?
እርግጥ ይህንን ጽሑፍ ከምታነቡት ሰዎች ውስጥ ኣንዳንዶቻችሁ እያሽቃበጥኩ ሊመስላችሁ ይችላል ። አልተሳሳታችሁም ፥ ኣዎ እያሽቃበጥኩ ነው!! ሰው እንኳን ለብርሃኑ ነጋ ለወያኔ ያሽቃብጥ የለ ?! ታዲያ ምን ሽግር ኣለው ?
ሺዎች ከጎንህ ነን ። ከጎንህ ያቆመን ደሞ የቆምክለት አላማ ነው !
ሄኖክ የሺጥላ

Tuesday, February 2, 2016
Ethiopia’s Zone 9 collective - freed, but still under pressure
By: IPI Contributor Michael Kudlak
VIENNA, Feb 2, 2016 – Ethiopian authorities should cease an ongoing campaign of persecution targeting journalists and bloggers from the Zone 9 collective and allow them to travel and report freely, the International Press Institute (IPI) said today.
Despite a federal high court’s decision to drop widely criticised charges of terrorism against them last year, members of the group continue to face arbitrary travel bans and other actions against them that hinder their professional activity.
“Members of the Zone 9 collective face a pending appeal of the decision to drop charges against them, ongoing administrative harassment, threatening messages and constant surveillance, all of which appear designed to keep them in a state of fear where re-arrest is imminent,” IPI Director of Advocacy and Communications Steven M. Ellis said. “In addition to silencing the collective, these actions seem intended to muzzle the critical voice of Ethiopia’s independent journalists in general.
“We call, again, on authorities to respect constitutional guarantees of press freedom and freedom of information and to reform the country’s repressive anti-terrorism law, and we urge them to stop the harassment of members of the Zone 9 collective and allow them to do their job as journalists.”

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛትና ስርጭት ከደቡብ ሱዳን እንደምታንስ አንድ ጥናት ጠቆመ
ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዓለም ላይ ካሉ አገራት በቴክኖሎጂ ስርጭትና በሃብት ድርሻ ኋላቀር የሚባሉት አገራት የሚገኙበት የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ነው። በቀጠናው በኢንተርኔት ስርጭት ላይ በተደረገ ጥናት ኢትዮጵያ ከአዲሲቷ አገር ደቡብ ሱዳን ባነሰ የኢንተርኔት ስርጭትና ተጠቃሚ ብዛት ያላት አገር መሆኗ ታውቋል።
በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደር አንድ የኢንተርኔትና የስልክ ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮም ያላት ኢትዮጵያ ከዘጠና ሚሊዮን በላይ ከሚሆነው ሕዝቧ ውስጥ 3.7 በመቶ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ነው። ጎረቤት አገር ኬንያ 69.6 በመቶ የሚሆነው ሕዝቧ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋዳሽ ከመሆኑም በተጨማሪ የተለያዩ አማራጮች እንዳ...ሉት ተገልጿል። ደቡብ ሱዳን 15.9 በመቶ የኢንተርኔት አገልግሎት ለሕዝቦቿ በማሰራጨት ከኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በርካታ አርብቶአደሮች መታሰራቸው ታወቀ
ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፋር የታየውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ 70 አርብቶአደሮች ከብቶቻቸውን ወደ ስኳር እርሻ ልማት ውስጥ አስገብተዋል በሚል ተይዘው ። ከታሰሩት መካከል አንደኛው ሰው በድብደባ መሞቱን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ሟቹ ሰዲቅ ዳውድ ለመብቱ የሚታገል ሰው እንደነበር የሚናገሩት ምንጮች፣ ይህንን ተከትሎ ውጥረት መንገሱንና መንግስት ኤሌክትሪክ ነው የገደለው በማለት ህዝቡን ለማረጋጋት እየሞከረ ነው።
"አርሶደሮቹ መሬታቸውን ተቀምተዋል፤ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሄደው ከብቶቻቸውን እንዳይመግቡ እንኳን አካባቢው ድርቅ ነው፣ በዚህ ተስፋ በመቁረጥ ከብቶቻቸውን ወደ ስኳር እርሻ ልማቱ ማስገባታቸውን" የአፋር ሰብአዊ መብቶች ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ ተናግረዋል።

ቃልቲ የሚገኙ የኦሮሞ እስረኞች ራቁታቸውን ሆነው መገረፋቸውን አንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ገለጸ
ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ በቃሊቲ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ እስረኞች ራቁታቸውን ሆነው በመደብደባቸው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።ብዙዎች ደማቸውን እያዘሩ ታንከር ወደሚባለው ጨለማ ክፍል መወሰዳቸውንም ገልጿል።
የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገብረእግዚአብሄር በተባለ የእስር ቤቱ ሃላፊ ትእዛዝ የተፈጸመው ድብደባ ከምሽቱ 3 ሰአት እስከ 9 ሰአት የዘለቀ መሆኑንም ገልጿል። ከድር ዝናቡ፣ አብዲሳ ኢፋ፣ አብዲ ብሩ፣ ባንቲ ደገፋ፣ ደጃዝማች በያና፣ እና ሁሴን አብዱረህማን የተባሉት እስረኞች በከፍተኛ ሁኔታ ከተደበደቡትና ጨለማ ቤት ውስጥ ከተላኩት መካከል ይገኙበታል። ሁሴን አብዱራህማን ከሌሎች ተለይቶ መወሰዱንና ድብደባው ከተፈጸመበት ማግስት ጀምሮ የት እንዳለ አለመታወቁን ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

በኮንሶ እስሩና ማንገላታቱ ቀጥሎአል
ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኮንሶ ህዝብ የተመረጡ 12 ሽማግሌዎችና የደቡብ ክልል ባለስልጣናት ትናንት በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ስቃይ እንዲቆም ስምምነት ላይ ቢደርሱም፣ ስምምነቱ አንድ ቀን ሳይደፍን የፌደራል ፖሊሶች በድጋሜ አካባቢውን ተቆጣጥረው ሰዎችን እየያዙ በማሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ስምምነቱ ህዝቡ ባቀረበው ጥያቄ ምክንያት ሰዎች እንዳይታሰሩ፣ ከስራ እንዳይፈናቀሉ፣ የታሰሩት እንዲፈቱ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ በዛረው እለት በወረዳው የሚታየው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። በካራት መውጫና መግቢያ ከፍተኛ ፍተሻ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ ወደ ፋሻ መንገድ መሄጃ መጨቀ መገንጠያ ላይ ተጓዞች ከመኪና እየወረዱ መታዋቂያ እየተጠየቁ ፣ ስም ዝርዝራቸው ፖሊሶች ከያዙት የሚታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ጋር እየተመሳከረ እንዲሄዱ ወይም እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ከ250 በላይ ሰዎች እየተፈለጉ ሲሆን፣ 8ቱ በኦነግነት 7 ቱ ደግሞ በግንቦት7 አባልነት ተፈርጀዋል። በካራት ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ 6 ሰዎች ደግሞ ወደ ግዶሌ እስር ቤት እንዲተላለፉ ተደርጓል።በእስር ላይ በሚገኙት ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።
የኮንሶ ህዝብ አሁን ከሚገኝበት ሰገል ዞን ወጥቶ የራሱ ዞን እንዲሰጠው በመጠየቅ ላይ ነው።

በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ
ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአካባቢው የተገኘው አስተማማኝ መረጃ እንደሚያመለክተው በጋምቤላ ከተማ፣ በአቦል፣ በለሬ፣ በኢታንግ፣ በተሪፋም፣ በስደተኞች ካምፖች፣ በኚንኛንግ፣ አቦቦ፣ አሌሮና በሌሎችም አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በእየቀኑ በአማካኝ ከ10 በላይ ሰዎች እየተገደሉ መሆኑንም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። በዛሬው ቀን ብቻ 2 ኑዌሮች በአጋዚ ወታደሮች ሲገደሉ፣ 5 የንዌር የልዩ ሃይል አባላት በአኝዋኮች ተገድለዋል። በአኝዋኮች በኩልም የሞቱ ሰዎች መኖራቸውንና የአስከሬን ፍለጋ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ጋምቤላ ከሁለት የተከፈለች ሲሆን፣ ከባሮ ወንዝ ድልድይ በላይ ኒውላንድ ተብሎ በሚጠራው አካ...ባቢ ኑዌሮች ሰፍረው ሲገኙ፣ በተቀራኒው ደግሞ አኝዋኮች ይገኛሉ። የአንደኛው ብሄረሰብ አባል ድልድዩን ከተሻገረ በሌላው ብሄረሰብ አባል የሚገደል መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ በሌሎች ወረዳዎችም በተመሳሳይ መንገድ ክፍፍል ተፈጥሮ ዜጎች እያለቁ ነው።

ሕወሃቶች ፎቅ ይሰራሉ ብአዴኖች ሎተሪ ይሸጣሉ – ግርማ ካሳ
ከኢትዮጵያ በቅርብ ከመጣ ከአንድ ወዳጄ ጋር አወራን። ከጥቂት ወራት በፊት ብአዴን በባህር ዳር ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ፣ የተገኘ ። በስብሰባው ከፍተኛ ጭቅጭቅ እንደነበረ ነገረኝ። ከዚህ ወዳጄ ባገኙሁት መረጃ፣ በተለይም በፓርቲው መካከለኛና ታች ባሉ የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ በሕወሃት ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ ተሰምቷል። “በኢሕአዴግ ዉስጥ የተጠቀሙት ህወሃቶች ናቸው እንጂ ሌላው አይደለም” የሚል ከፍተኛ ምሬትና ብሶት ቀርቧል። “በሁሉም ነገር፣ ሃላፊዎቹ ፣ ወሳኞች ቀዳሚዎቹ እነርሱ ናቸው ። ለምድንን ነው ይሄ የሚሆነው ?” የሚል ጥያቄ ቀርቧል። “እነርሱ ባለፎቅ እኛ ሎተሪ ሻጭ ነው የሆንነው “ ሲሉ ነበር። እንደሚታወቀው ኦህዴድ አምጿል። የኦህዴድ አባላትና ካድሬዎች ናቸው፣ የመንግስትን መዋቅርን በመጠቀም ፣ ህዝቡን በማደራጀት ከነጃዋር ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ላለፉት ሁለት ወራት ተቃዎሞ እንዲታይ ምክንያት የሆኑት። ወደ ድሃዴን(የደቡብ ሕዝቦችች ደርጅት) ከመጣን አንደኛ እርስ በርስ ፣ ሕወሃት ለርሱ እንዲመቻቸው ብሎ፣ ከፋፍሏቸዋል። ለምስሌ በወላይታና በሲዳማ የደሕዴን አባላት መካከል ችግር አለ። ሁለተኛ በድሃዴን ተራው አባላት አካባቢም ፣ ባለው ሁኔታ ደስተኛ ባይሆኑም፣ ብዙም በኦህዴድና በብአዴን እንዳለው አይነት ማጉረምረም አይሰማባቸውም። ምናልባት የኛ ሰው ነው ጠቅላይ ሚኒስተር የሆነው ከሚልም ሊሆን ይችላል። ለጊዜው ድሃዴንን ወደ ጎን በማድረግ፣ ብአዴን እና ኦህደድ ግንባር ቢፈጥሩ የሕወሃትን የበላይነት በማስቆም የስርዓት ለዉጥ ማምጣት የሚቻልበትን ትንሽ ድፍረት ከተገኘ ቀላል መንገድ ለማሳየት ልሞክር። ፓርላማው በ ቮት ኦፍ ኮንፊደንስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማንሳት ይችላል።
Monday, February 1, 2016
ከሶማሊያ ባሕር የተረፉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ሊመለሱ ነው
ባለፈው ወር መነሻቸውን ከሶማሊያ የባሕር ዳርቻዎች አድርገው በጀልባ በባሕር ወደ የመን ሊያቀኑ ሲሞክሩ አብዛሃኞቹ ስደተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።
የተወሰኑት ከአደጋ ተራፊዎች ውስጥ በሶማሊ ላንድ ራስገዝ ሃርጌሳ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ድጋፍ አማካኝነት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ሊደረግ ነው።
ባለፈው ዓመት ውስጥ ብቻ እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ከ90 ሽህ በላይ ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በባሕር በጦርነት ወደምትታመሰው የመን ማቅናታቸውን አይኦኤም ገልጾ ከስደተኞቹ ውስጥ ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን አስታውቋል።

ባለፈው ወር በጀልባ መገልበጥ አደጋ 34 ኢትዩጵያዊያን መሞታቸውንና በአጠቃላይ ከ96 በላይ ስደተኞች በባሕር አደጋ መሞታቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።
አይኦኤም በጎ ፈቃደኛ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያንን ማጓጓዣ እርዳታ ከአሜሪካ የስደተኞች ቢሮ ማግኘቱን አስታውቋል።
ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አገራቸውን በመተው ሕይወታቸውን ለ አደጋ አጋልጠው መፍለሳቸውን ቀጥለዋል። በስደት አገራት ለሚደርስባቸው ሰቆቃዎች የኢትዮጵያ ኤንባሲና ዲፕሎማት መስሪያቤቶች ለዜጎቻቸው ከለላ በመስጠት ወደ አገራቸው መብታቸው ተጠብቆ ይመለሱ ዘንድ ሲሰሩ አይታይም።

የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት በኢትዮጵያ ተጨማሪ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች መኖራቸውን አስታወቀ
ከሰላሳ ዓመት በኋላ የተከሰተውን ዘግናኝ የርሃብ አደጋ ተቋቁሞ የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ይቻል ዘንድ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት USAID የ100 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ልገሳ አደረገ። ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 10.5 ሚልዮን ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውን አመልክቶ ይህ አሃዝ በቅርቡ እንደሚያሻቅብ ስጋቱን ጠቁሟል።
የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት USAID ሃላፊ የሆኑት ጋይሌ ስሚዝ የሁኔታውን አሳሳቢነት ሲገልጹ ''አስከፊው እርሃብ ያስከተለው ቀውስ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል የኢትዮጵያ ሕዝብ የእኛ እርዳታ በአፋጣኝ ያስፈልገዋል''
በተጭማሪም አሉ ጋይሌ ስሚዝ ''በአፋጣኝ ተጨማሪ ግብአቶ...ችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ገበሬዎቹን ወደ አምራችነት እንዲመለሱ በማድረግ ከዚህ ቀውስ እንዲወጡ ማስቻል አለብን!'' በማለት ለረድኤት ድርጅቶችና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፕሬዝዳንት ባንኪ ሙን በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ በተከሰተውን ድርቅ ሳቢያ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት አስከፊ የምግብ ጥረት ስለሚከሰት ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት የእርዳታ እጃቸውን በአፋጣኝ እንዲዘረጉ ተማጽኖዋቸውን አቅርበዋል።
ባንኪሙን አክለውም ''አፋጣኝ ልገሳ በማድረግ የብዙዎችን ሕይወት በማዳን ቀውሱን መከላከል አለብን!'' ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለበትን አስጊና አስፈሪ የርሃብ አደጋ ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎችን በጎበኙበት ወቅት የተባበሩት መንግስታትና ዓለም አቀፍ ለጋሾች በጋራ 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማለትም ከሃያ ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ህዝቡ ትግሉን እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረቡ
የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በዲሲ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ንግግር፣ ወያኔን መጣል የሚቻለው በምኞት ሳይሆን ጠንክሮ በመታገል ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ከመንግስት ሽፍትነት ጋር የተያያዘ መሆኑንና የገለጹት ፕ/ር ብርሃኑ፣ የመሬት ቅርምቱ የዚህ ሽፍትነት ዋና ማሳያ ነው ይላሉ። ዝርፊያው በአንድ በኩል፣ የልማት መንግስት በሌላ በኩል የፈጠሩዋቸው በርካታ ችግሮች መሆናቸውን ገልጸው፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ የዚህ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳለፈው 50 አመት እንደዚህ ቅጣ ያጣ መንግስት ያዬ አይመስለኝም ነበር ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ፣ 20 ሚሊዮን ህዝብ ተርቦ በሚገኝበት ወቅት የመንግስት ባለስልጣናቱ ድርቁን ተቆጣጥረነዋል ማለታቸው ግብዝነታቸውን... ያሳያል ብለዋል።
ለከፋፍለህ ግዛው በሚል በሰፊውና በተወሰነም ደረጃ በስኬት እየተጠቀሙበት የማንነት ፖለቲካ መልሶ ራሳቸውን የሚነክስበት ደረጃ ደርሷል ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ የብሄር ጥያቄያቸውን በምሳሌነት አንስተዋል። ከማንነት ፖለቲካ ጋር ተያይዞ የተነገረው ተስፋ እና ስርዓቱ ሊያመጣ የቻለው ሊጣጣም አለመቻሉን የገለጹት ፕ/ር ብርሃኑ፣ አሁን እየተነሳ ያለው ጥያቄ ያላሰቡትና ያልጠበቁት ነው ብለዋል። የማንነት ጥያቄ ራስን የማስተዳደር ጥያቄ በመሆኑ በመሰረተ ሃሳቡ የዲሞክራሲ ጥያቄ ነው ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ፣ ወያኔ ይህን ጥያቄ ለመመለስ በፍጸም አይችልም ይላሉ።

በቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች ቤታችንን አናስፈርስም በማለት ተቃውሞ አሰሙ
በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ ቡታጅራ የወረዳው ባለስልጣናትና ፖሊሶች ቤት ለማፍረስ በመሄዱበት ወቅት ህዝቡ አታፈርሱም በማለት ተቃውሞውን በማሰማት፣ ባለስልጣኖቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ አድርገዋል። ህዝቡ "ኢህአዴግ ሌባ፣ መሬታችን አይሸጥም፣ መሬት አይገኝም፣ መሬት የህዝብ ነው" የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።
ታህሳስ ወር መጨረሻ ላይም እንዲሁ ህዝቡ ቤታችንን አታፈረሱም በማለት የፖሊሶችን መሰሪያ በመቀማት ወደ መጡበት መልሷቸዋል።
የወረዳው ፖሊሶች ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዳቸውም ታውቋል።

Subscribe to:
Posts (Atom)