ጎንደር ህመምተኛ ጠያቂ ወገኖች ዓመጽ ታስነሳላችሁ በሚል ሰበብ ወደ ሆስፒታል እንዳይገቡ ተከልክለዋል፥ ህዝቡና ወታደሮቹ በር ላይ ተፋጠው ይገኛሉ፥
የወያኔ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል መትረየስ ጠምደው እስረኛውንና የከተማውን ሰው በጸሀይ በጉባይ እረሸኑት፥ በጥይት ተገድለው የገቡ ብዙ ዓስከሬኖች በሆሥፒታል ውስጥ ይገኛሉ፥
18 እሬሳ ቆጥሬ በዓይኔ ዓይቻለሁ ሲሉ አንድ በሆስፒታሉ የተገኙ የዓይን ምስክር ተናግረዋል፥
ከእስር ቤቱ ውስጥ እንዳሉ በእሳት የጋዩት ቁጥር ያለማጋነን ወደ 45 ሰዎች ይሆናሉም ብለዋል፥
በጎንደር ከተማ ከፍተኛ መረበሽና መጨናነቅ ይታያል፥ በሁሉም አቅጣጫ የሚወጡ መኪናዎች ይፈተሻሉ::
18 እሬሳ ቆጥሬ በዓይኔ ዓይቻለሁ ሲሉ አንድ በሆስፒታሉ የተገኙ የዓይን ምስክር ተናግረዋል፥
ከእስር ቤቱ ውስጥ እንዳሉ በእሳት የጋዩት ቁጥር ያለማጋነን ወደ 45 ሰዎች ይሆናሉም ብለዋል፥
በጎንደር ከተማ ከፍተኛ መረበሽና መጨናነቅ ይታያል፥ በሁሉም አቅጣጫ የሚወጡ መኪናዎች ይፈተሻሉ::
በደቡብ ጎንደር መውጫ፥ በሰቲት ሁመራ መውጫ፣ በመተማ መውጫ እና በዳባት ወደ ሰሜን በር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል ባልደረባዎች የሚወጣውን ሁሉ ይፈትሻሉ፥
ለእሳቱ መነሻ እሄ ነው ብለው ስም ባይጠሩም የእድሜ ልክ እስረኞች በውጭ ካሉ ኃይሎች ጋር በመተባበር እንደ ፈጸሙት የመንግሥት ምንጮችን ጠቅሰው የከተማው FM radio ሲዘግብ ተሰምቷል፥ የወያኔ መንግሥት ባሳየው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃና በሁኔታው ተቆጥተው ድንጋይ ከወረወሩ ወጣቶች ጋር ለማያያዝ ጥረት ሲያደርጉ ይታያል፥
No comments:
Post a Comment