የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በስፋት ተቃዉሟቸውን እያሰሙ ነው። በወያኔ ግፈኛ ታጣቂዎች በጎንደር እና በኦሮሚያ በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ሃዘናቸውን በመግለጽ፣ እህቶቻችንም ጥቁር በመልበስ፣ በካፌቴሪያ ምሳ አንበላም ብለው ቦይኮት አደርገዋል።
እንቅስቃሴው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ወደ አዲስ አበባ እየገባ ነው። እንቅስቃሴው በኦሮሞ ተማሪዎች በማስተር ፕላኑ ዙሪያ ቢጀመርም፣ መልኩን በስፋት ቀይሮ፣ አሁን የሁሉም ዜጎች እንቅቃሴ ሆኗል። የመሰረታዊ የመብት፣ የነጻነት የእኩልነትና የዲሞክራስ ጥያቄ ሆኗል።
በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች እየተደረጉ ያሉ እጅግ በጣም ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በሃረር ከተማ (ሃረሬ ክልል)፣ በዲላ ( ደቡብ ክልል፣ ጌዲዮ ዞን ዋና ከተማ) እንዲሁም በአዋሳ (የደቡብ ክልል ዋና ከተማ) ተቃዉሞዎች ተደረገዋል።
በተለይም በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴውን በቅርብ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
No comments:
Post a Comment