ኀዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት የሚጓዙ 22 ኢትዮጵያዊያን ስደተኛችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አንድ ተሽከርካሪ በደረሰበት አደጋ የመኪናውን አሽከርካሪ ጨምሮ 3 ኢትዮጵያዊያን ወዲያውኑ ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ 19 የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአገሪቱ የፖሊስ አዛዥ ፓውል ኒያቲ እንዳሉት የስደተኞቹን አገባብና የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑንና ጉዳተኞቹ ለሕክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን መግለጻቸውን ዘ ሲትዝን ዘግቧል።
ኢትዮጵያዊያን የትውልድ ቀያቸውን እየለቀቁ ሕይወታቸውን ለአደጋ በማጋለጥ በአራቱም የዓለም ማእዘናት መፍለሳቸውን ቀጥለዋል። ይህም አገሪቷ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታና ማለትም የስራ ዋስትና ማጣት፣ድርቅ፣ የዴሞክራሲ አፈና ውጤት መሆኑን ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።
ኢትዮጵያዊያን የትውልድ ቀያቸውን እየለቀቁ ሕይወታቸውን ለአደጋ በማጋለጥ በአራቱም የዓለም ማእዘናት መፍለሳቸውን ቀጥለዋል። ይህም አገሪቷ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታና ማለትም የስራ ዋስትና ማጣት፣ድርቅ፣ የዴሞክራሲ አፈና ውጤት መሆኑን ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።
No comments:
Post a Comment