ታኀሳስ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህንነት ምንጮቻችን እንደገለጹት መንግስት እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ቀጠሎአል። 99 በመቶ የሚሆነው ቦታ በአንድ ብሄር ተወላጆች የተያዘው የብሄራዊ ደህንነት መስሪያ ቤት ኢንሳ፣ ተላልፎ የሚሰጠውን መሬት የአየር ላይ ፎቶግራፍ እያነሳ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
የደህንነት ኤጀንሲው ፎቶ የማስነሳቱን ስራ የሚሰራው ትልቅ ለሆነ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚል ሰበብ ሲሆን፣ ዋናው አላማው ግን መሬቱን ለማካለል የሚሰጠውን ቦታ ለመወሰን መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ተቃውሞ እንዳይነሳ ለማድረግ የህዝቡን አጀንዳ በተለያዩ መንገዶች ለማስቀየር ተደጋጋሚ ሙከራዎች ማድረጉንም አክለው ገልጸዋል። የአየር ላይ ቅኝቱና ፎቶ የማንሳቱ ስራ እንደተጠናቀቀ ድንበር የመከለሉ ስራ ይከናወናል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ተቃውሞ እንዳይነሳ ለማድረግ የህዝቡን አጀንዳ በተለያዩ መንገዶች ለማስቀየር ተደጋጋሚ ሙከራዎች ማድረጉንም አክለው ገልጸዋል። የአየር ላይ ቅኝቱና ፎቶ የማንሳቱ ስራ እንደተጠናቀቀ ድንበር የመከለሉ ስራ ይከናወናል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment