ታኀሳስ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ገንዘብ በማፍሰስና በዲፐሎማሲ ዘመቻ የኢሳትን የሳተላይት ስርጭት ለማፈን ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ ከቆየ በሁዋላ፣ በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ስርጭቱ እንደገና ለቀናት እንዲቋረጥ አድርጓል። ስርጭቱ መቋረጡን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን የደረሱን ሲሆን፣ ኢሳት ወደ አየር ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ስራ አመራር ክፍል ገልጿል።
ኢሳት በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አየር እንደሚመለስ የገለጸው ድርጅቱ፣ ህዝቡ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ አሁንም በትእግስት ከኢሳት የሚሰጠውን መረጃ እንዲጠባበቅና የተለመደውን የድጋፍ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል።
ኢሳት በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አየር እንደሚመለስ የገለጸው ድርጅቱ፣ ህዝቡ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ አሁንም በትእግስት ከኢሳት የሚሰጠውን መረጃ እንዲጠባበቅና የተለመደውን የድጋፍ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል።
No comments:
Post a Comment