Tuesday, December 1, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ዛሬ ዋልድባ ላይ መዋጋቱንና ጉዳት ማድረሱን ገለጸ * 29 ወታደሮችን ገደልኩ አለ

መነሻውን ኤርትራ ያደረገው አርበኞች ግንቦት 7 ከቀናት በፊት በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር አካባቢ በሚገኙ ከተሞች በምሽት ቀስቃሽ ወረቀቶችን ሲበትን መክረሙን ከገለጸ በኋላ ዛሬ በለቀቀው መረጃ ዋልድባ ላይ ከመንግስት ኃይሎች ጋር መዋጋቱን ገለጸ:: ዘ-ሐበሻ ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ያገኘችው መረጃ እንደሚጠቁመው ሰራዊቱ ዛሬ ዲሴምበር 1, 2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ከመንግስት መከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ጦር ጋር ተዋግቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ነው:: ከመንግስት በኩል ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ስለመዋጋቱ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተሰጠ መግለጫ የለም:: የአርበኞች ግንቦት 7 በራድዮው በኩል እንዳሰራጨው መረጃ በድንገት በከፈትኩት ጥቃት ዋልድባ ላይ ለሰዓታት ያህል ሰራዊቴ ሲዋጋ ውሎ በትሹ 29 ወታደሮችን ገድያለው እንዲሁም ከ40 በላይ ደግሞ አቁስያለሁ ብሏል::

No comments:

Post a Comment