የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በሰጡት መግለጫ በዚህ ዓመት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መሰረታዊ መብት ጥበቃ መገለጫ የነበረው የበርካታ ጦማሪያን ከእስር መለቀቅን ጨምሮ ፤ በኢትዮጵያ የታዩ መሻሻሎችን የምንደገፍ ቢሆንም፤ በቅርቡ የታሰሩ ሌሎች ጋዜጠኞች ጉዳይ በጥልቅ አሳስቦናል ብለዋል፡፡ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን በመጠበቅና ዲሞክራሲን በማስፋት ረገድ ከዚህ ቀደም የታዩ መሻሻሎችን አጠናከሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያን መንግሥት እንጠይቃልን ያለው መግለጫው፣ ገለልተኛ ድምጾችን መገደብ ልማትንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ጨምሮ መሰል መሻሻሎችን እንደሚገታ እንገነዘባለን ብሎአል።
ኢትዮጵያ ሞዴልና የአፍሪካ የልማት ድምጽ መሆኗን አሜሪካ ስታደንቅ ቆይታለች የሚለው መግለጫው፣ እነዚህ ውጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው፤ በዲሞክራሲያዊ፣ መልካም አስተዳደርና በሰብዓዊ መብት መከበር ላይ ሊመሰረቱ ይገባል ብሎአል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችንና ሃሳብን በነፃ የመግለጽ መብትን ተግባራዊ በማድረጋቸው የታሰሩትን እንዲለቅ፣ የፀረ-ሽብር ሕጉን የተቃዋሚ ድምጾችን የማፈኛ መሳሪያ አድርጎ እንዳይጠቀም፤ የጋዜጠኞችን ፣የጦማሪያን እንዲሁም የተቃዋሚዎችን የመጻፍና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲጠብቅ እንጠይቃልን ሲል መግለጫው ይደመድማል።

No comments:
Post a Comment