ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት በመቃወምና እንዲሁም በኦሮምያ የደረሰውን ጭፈጨፋ በማውገዝ በኮርያ ሲዖል ከተማ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ፈት ለፊት የታቃዉሞ ሰልፍ አድርገዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሱዳን ኢምባሲ በማምራት የኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ ለመስጠት ያሰበዉ መሬት የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተቃወሙ በመሆኑ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ለወደፊቱ ለሚፈጠረው ዘላቂ ሰላም እና ጥሩ ጉርብትና ሲል ከመንግስት ጋር ምንም አይነት ድርድር እንዳያደርግ ጠይቀዋል። ከኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ የተዘጋጀዉን ደብዳቤም እንዲሁ ለኢምባሲዉ ልከዋል።
ወደ ኢትዮጵያ ኢምባሲ በመሄድ መንግስት መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱን እንዲሁም በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግድያ፣ ድብደባ እና እስራት በጽኑ አውግዘዋል። የህዉሐት አገዛዝ በአገሪቷ ላይ እያካሔደ ያለዉን እርስ በርስ የማጋጨት ሥራ እንዲያቆምም ጠይቀዋል።

No comments:
Post a Comment