“እናንተም ሆናችሁ ህወሓት የአገሪቱን ዳር ድንበር ማስከበር ስላልቻላችሁ፣ ህዝቡንም መምራት ስለተሳናችሁ ስልጣናችሁን ልቀቁ አርበኞች ግንቦት 7 ይምራን…” በማለት ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በአንድነት ጠይቋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ለሱዳን ተቆርሳ የምትሰጥ አንድ ጋት መሬት እንኳን ብትኖር ህዝቡ ከውስጥም ከውጭም በአንድነት ለመዋጋት ቆርጦ እንደተነሳና ህወሓት ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ ማስጠንቀቂያ ጭምር አስተላልፏል፡፡
የህወሓቱ አሽከር ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ጠዋት በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ከባህር ዳር አርማጭሆ ሙሴ ባምብ ገብቶ የአካባቢውን ህዝብ በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለማነጋገር ሞክሯል፡፡
በስብሰባው ላይ የተነሱት ሦስቱ የመወያያ አጀንዳዎች፦
1. በጎንደር የተከሰተው የእርስበርስ ግጭት
2. የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና
3. የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በሚመለከት ናቸው፡፡
በስብሰባው ላይ የተነሱት ሦስቱ የመወያያ አጀንዳዎች፦
1. በጎንደር የተከሰተው የእርስበርስ ግጭት
2. የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና
3. የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በሚመለከት ናቸው፡፡
ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ካድሬዎች በመሩት ስብሰባ ላይ የተገኘው የአርማጭሆ ህዝብ በጎንደር የተከሰተውን የእርስበርስ ግጭት ህወሓት እንደጠነሰሰው እና የእሱ ዲቃላ የሆነው ብአዴን እጁ እንዳለበት ገልጿል፡፡ ብአዴን የአህያ ባል ሆኖ ህወሓት ለተባለ የቀን ጅብ አሳልፎ ሰጥቶ የወልቃይትን ህዝብ እያስበላው እንደሚገኝም ህዝቡ ጨምሮ ተናገሯል፡፡
ድንበሩን በሚመለከትም፥ “እናንተም ሆናችሁ ህወሓት የአገሪቱን ዳር ድንበር ማስከበር ስላልቻላችሁ፣ ህዝቡንም መምራት ስለተሳናችሁ ስልጣናችሁን ልቀቁ አርበኞች ግንቦት 7 ይምራን…” በማለት ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በአንድነት ጠይቋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ለሱዳን ተቆርሳ የምትሰጥ አንድ ጋት መሬት እንኳን ብትኖር ህዝቡ ከውስጥም ከውጭም በአንድነት ለመዋጋት ቆርጦ እንደተነሳና ህወሓት ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ማስጠንቀቂያ ጭምር አስተላልፏል፤ ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ፡፡
በአጠቃላይ በአርማጭሆ ሙሴ ባምብ በህወሓት አሽከር ገዱ አንዳርካቸው እና በህዝቡ መካከል በዛሬው ዕለት የተካሄደው ውይይት ከፍተኛ ንትርክና እሰጥ አገባ እንዲሁም የከረረ ቁጣና ተቃውሞ የተሞላበት ሲሆን ከቀኑ 9፡30 ላይ ያለምንም ውጤት በአገዛዙ ውርደት የተላበሰ ሽንፈት ብቻ ተቋጭቷል፡፡
No comments:
Post a Comment