ተደጋግሞ እደተዘገበው ወያኔ በቅማንት ስም ጎንደርን ለመረከብ ሴራ ሲያሴር ከርሞ ብጥብጥ ፈጥሮ ነበር፡፡ ወዲያው በወያኔው ቅጥረኛ ሰራዊት ላይ አማራው “በሉ እንግዲህ ቋራ ላይ እንክተት” ብሎ ልክ አባቶቹና እናቶቹ በጥንት ዘመን ያደርጉ እንደነበረው ታጥቆ ተሰባስቦ ወደሽንፋ ሄደ፡፡ ወደቋራ ከዘመተው አማራም የደባርቅ፤ የበለሳ፤ የደብረታቦር፤ የጎጃም፤ የጎንደር አማራ ይገኝበታል፡፡ በመኪና እየተጫነ ሆ ብሎ ሽንፋ ገባ፡፡ በማሩ ቀመስ ደምቢያ በኩል ያለው አማራ ደግሞ ሆ ብሎ ወደዛው ወደሽንፋ ዘመቻ ሲያደርግ መንገድ ላይ ታቦት ከቤተ ክርስቲያን ወጥቶ በስንት ልመና ተመለሰ፡፡
. በዚህ ግርግር መድረሻ ያጡት 4500 ቅጥረኛ ወያኔዎች ወደጭልጋ (ሰራባ ወታደራዊ ካምፕ) ሸሽተው በመግባት ወደውጭ እንዳይወጡ በአማራው ሀይል ስለተከበቡ ታግተው ከርመው አሁን ተለቀዋል፡፡ የተለቀቁትም በሀገር ሽማግሌ በስንት ልመና እርቅ ተፈጽሞ ዳግም አማራውን እንዳያውኩ ቃል ገብተው ነው፡፡
እነደመቀ፤ አባይ ጸሀየና የመሳሰሉት የወያኔ ባለስልጣናት የጎንደርን ወጣቶች በጎሀ ሆቴል ሰብስበው ነበር፡፡ ስብሰባው ለ10 ሰአት ሆኖ ጥሪ የተደረገላቸው ግን በ9 ሰአት ነበር፡፡ ስብሰባውም ላይ ወጣቶች “እኛ እኮ የራሳችንን ስራ ሰርተን የምንኖር፤ መንግስት የማይደግፈን ነን፡፡ ለምንድነው አስር ሰአት ስብሰባ ለማድረግ ዘጠኝ ሰአት ምትጠሩን? ምን መስለን ታየናችሁ? ደግሞ እያንዳንዷን የምታደርጓትን ነገር እናውቃለን፤ ማናውቅ እንዳይመስላችሁ፡፡ በቅማንት ስም እና በሱዳን ስም መሬታችንን ለራሳችሁ ለትግራይ ሪፑብሊክ ልትወስዱ ነው፤ ተነቃቅተናል” ብለው አፋጠጧቻው፡፡ ባለስልጣናቱም “አወ ጥፋት ተሰርቷል፤ እናውቃለን” አሉ፡፡ ወዲያው ግን ወጣቶቹ በጥያቄ ቀጥለው ያጣድፏቸው ጀመር፡፡ ባለስልጣናቱም ተደናግጠው አንገታቸውን ደፉ፡፡ የስብሰባው ሁኔታ አዝማሚያው አላምር ሲላቸውም ራሳቸው በትነውት ወዲያውኑ ብን ብለው ጠፉ፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ እንደታየው እንደዛ አይነት ድፍረት የተመላበት ንግግርና ማፋጠጥ ገጥሟቸው አያውቅም ተብሏል፡፡
4. የወልቃይት የአማራ ብሄረተኝነት ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ በይፋ ጎንደር ላይ ጽ/ቤት ከፍቷል፡፡ በዚህም አባይ ጸሀየ ለምን ተፈቀደላቸው የሚል አቲካራ ቢጤ ከፍቶ ተገቢ መልስ ተሰጥቶታል ተብሏል፡፡
5. የጎንደር አማራ በቅማንት ስም የሚደረገውን ሴራ፤ ለሱዳን በሚስጥር ስለተሰጠው መሬት፤ ስለወልቃይት ጉዳይ፤ አማራው ላይ ስለሚደረገው አጠቃላይ መድሎና የዘር ማጥፋት ወንጀል ውግዘት የሚያደርግ ሰልፍ እያዘጋጀ እንደሆነ ታውቋል፡፡ መላው አማራም ከጎናቸው እንዲቆም አሳስበዋል፡፡
መቸም መብታችንንም ሆነ ህልውናችንን በልመና አናገኝም፡፡ በቻልነው መንገድ ሁሉ መታገል አለብን፡፡ ህልውናችን ስጋት ላይ ከመውደቅ የከፋ ነገር ምንም አይደርስብንም፡፡ የህልውና አደጋ የሚፈታው ደግሞ በእልህ አስጨራሽ ትግል ነው፡፡
No comments:
Post a Comment