Tuesday, July 31, 2018

በሶማሊ ክልል ተቃውሞ ቀጥሎ ዋለ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 24 ቀን 2010 ዓ/ም )ትናንት በራሶም ወረዳ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ በአፍዴራ ዞን ቀጥሎ ውሎአል። በአፍዴራ ዞን በሙሉ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን ለክልሉ ተወላጆች መብት መከበር የሚታገለው አቶ ጀማል ድሪሬ ገልጸዋል። የራሶም ወረዳ ተወላጆች የአብዲ አሌን ባለስልጣናት ማስወጣታቸውንና አስተዳደሩን መቆጣጠራቸውን አቶ ጀማል ገልጸዋል። በቅርቡ ዶ/ር አብይ ምሁራንን ሰብስበው ባናገሩበት ወቅት ፣ በክልሉ ያለውን ተቃውሞ በጎሳ መነጽር ለማየት መቻላቸው እንዳሳዘናቸው አቶ ጀማል አክለው ገልጸዋል። አቶ አብዲ ኢሌ የክልሉን ወረዳዎች ከ52 ወደ 99 ወረዳዎች ከፍ ማድረጉ ታውቋል። አብዲ ኢሌ በክልሉ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ ለተለያዩ ጎሳ አባላት ወረዳ እየሰነሸነ መስጠቱን የገለጹት አቶ ጀማል፣ አከላሉም ብዙ ችግሮች ያሉበት መሆኑን ገልጸዋል። ወረዳዎች ሲከለሉ ባህላዊ አሰራርን የጣሱና ግጭት ለመፍጠር ተብለው የተዘጋጁ መሆኑን አቶ ጀማል አክለው

ሰመጉ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከ700 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 24 ቀን 2010 ዓ/ም )የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ)፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመረጃ አስደግፎ በ144ኛ ልዩ መግለጫው በዝርዝር ሪፖርቱ ከ735 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። ከጥር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2010 ዓ.ም የተፈፀሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያጣሩ ባለሙያዎቹን ጥቃቱ ወደተፈፀመባቸው አካባቢዎች በመላክ የማጣራት ሥራውን ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ አከናውኖ፣ 258 የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል ሲገደሉ፣ በኦሮምያ ክልል የነበሩ 451 ሰላማዊ የሶማሊ ብሄር ተወላጆች መገደላቸውን ገልጿል። ኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ባቢሌ፣ ሐረር፣ አማሬሳ፣ ሀሮማያ፣ አወዳይ፣ ሜታ (ጨለንቆ)፣ ድሬደዋ፣ ፈዲስ፣ ኮምቦልቻ፣ ጉርሱም፣ ጃርሶ። በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ፣ ሚኤሶ፣ ቦርደዴ፣ መሰላ፣ ጡሎ። በምሥራቅ ጉጂ ሊበን እና ጉሚ ኤልደሎ። በምዕራብ ጉጂ ቡሌ ሆራ። በምስራቅ ሸዋ አዳማ አጣሪ ቡድኑ በመዘዋወር ምርመራዎችን አድርጓል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጂግጂጋ

ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ

Image may contain: 1 person, sitting and beard(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 24/2010) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ 27 ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ላደረገው ልኡል እግዚአብሔር ምስጋና አቅርበዋል።
እንዲሁም ይህ እርቅ ኣንዲወርድ አስተዋጻኦ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ምስጋናቸውን አቅረበዋል።
መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና በጎውን ሁሉ ተመኝተውላታል። ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ 27 ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተጓዙ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡ
Image may contain: one or more people, people standing and outdoorበአብዲ ዒሌ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሀምሌ 24/2010)በሶማሌ ክልል በክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ መቀጠሉ ተገለጸ።
ላለፉት 3 ወራት በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ አብዲ ዒሌ ስልጣን እንዲለቅ ተጠይቋል።
በአውበር ጂጂጋ ዞንና በአፍዴር ዞን ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች መደረጋቸው ታውቋል።
በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በሌላ በኩል በጋሞጎፋ ሳውላ ባላፈው ሳምንት የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ከ500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በጣና በለስ የስኳር ፕሮጀክት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሶስት ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል።

በቶሪኖ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን የመደመር ቀንን በጋራ አከበሩ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነዋሪነታቸውን በጣሊያኗ ቶሪኖ ከተማ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን በጋራ በመሆን የመደመር ቀንን በአዳራሽ ውስጥ በማክበር ለሰላም ጥሪው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ላለፍት ሃያ ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሰላም እንዲፈታ በተሾሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድንና አጋሮቻቸውን አመስግነዋል። ለሰላሙ ጥሪ እጃቸውን በመዘርጋት ለመደመሩ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂና ፓርቲያቸውንም አድናቆት ለግሰዋል። ለቀጣይ ካለፈው በመማር ልዩነቶችን በሰላም በመፍታት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ቃል በመግባት ዝግጅቱ በሰላም ተጠናቋል።

Monday, July 30, 2018

ላለፉት 12 አመታት በህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ።

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ካለፉት ስድስት ዓመታት እስር በኋላ በቅርቡ ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የሚዲያ ውጤቶች ከህዝቡ ጋር ለመገናኘት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል.። የእስክንድ ቢሮ ከ12 ዓመታት በኋላ ሲከፈት ጋዜጠኞች እና የዞን ዘጠን ጦማርያን ተሰባስበውም ኬክ በመቁረስ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል.። በስደት አሜሪካ የምትገኘው የሰርካለም አሳታሚ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ባለቤቱ ሠርካለም ፋሲል ጉዳዩን አስመልክታ በሰጠችው አስተያዬት፦“.ነፃው ፕሬስ ታፍኖ አይቀርም….የህዝብ አደራ አለብን!”ብላለች። ትናንት በሆላንድ -ደንሀግ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመቀበል በተሰናዳው ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባደረገው ንግግር ከእስክንድር ነጋና ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር አንድ ላይ በመሆን በቴሌቬዥንና በጋዜጣ ወደ ጋዜጠኝነት ሥራው ለመቀላቀል ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሲፈፀምባቸው የነበሩት አራት የፌደራል ማረሚያ ቤት አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደረገ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) በህግ ጥላ ስር ያሉ ፍርደኛ እስረኞችን በመቀበል የቅጣት ጊዜያቸውን እስኪፈፅሙ ድረስ በማቆያነት የተቋቋሙት ማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ የመብት ጥሰት ሲፈፀምባቸው ቆይቷል። ከማእከላዊ ምርመራ ሰቆቃ የተረፍትን ታራሚዎች በመቀበል ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች በመፈፀም የሚታወቁት የቂሊንጦ፣ የድሬዳዋ፣ የሸዋሮቢትና የቃልቲ ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ተነስተው በምትካቸው አዲስ አስተዳዳሪዎች ተሹመዋል። የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳዳር ዛሬ እንዳስታወቀው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አዛዥ የነበሩት ገ/ኢየሱስ ገ/እግዚአብሔር ተነስተው ኮማንደር ተክሉ ለታ ተተክተዋል። በተመሳሳይ በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት አስተዳዳር የነበሩት የማነ አስፋው በኮማንደር እንዳሸው ማሙዬ ተቀይረዋል። የድሬዳዋ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የነበሩት መኮንን ደለሳ በበኩላቸው በወንድሙ ደበሌ ሲተኩ፤ የቂሊንጦው አስተዳዳሪ አሰፋ ኪዳኔ በኮማንደር ጫላ ጸጋ እንዲተኩ ተደርጓል። የፌደራል ማረሚያ ቤት የኃላፊነት ቦታዎችን ጨምሮ፤ የህክምና ጥበቃና የንብረት አስተዳደር ሹመቶች በአብዛሃኛው በህወሃት የቀድሞ ታጋዮች መያዛቸው ይታወቃል። በቂ መረጃ እያለ እስረኞች ላይ የመብት ጥሰቶች የፈፀሙ የማእከላዊ መርማሪዎችም ሆነ የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ውስጥ እስካሁን በህግ ተጠያቂ የሆነ አለመኖሩ እንዳሳዘናቸው ጉዳተኞች ተናግረዋል።

በሃረር ወጣቶችን እርስ በርስ ለማጋጨት የተደረገው ሴራ ከሸፈ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወኪላችን እንደገለጸው ጠ/ሚ አብይ አህመድን ለመደገፍ፣ በኢንጂኒየር ስመኛው ሞት ሃዘናቸውን ለመግልጽ እንዲሁም የአሟሟታቸው ሁኔታ በፍጥነት ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ለመጠየቅና ጄ/ል አብርሃ የምስራቅ እዥ አዛዥ በነበሩበት ወቅት ታፍነው የተወሰዱትን የአቤል ፈቃዱ ወይም አቤል ኩባ እና የደረጀ ሙሉጌታ ሁኔታ ለህዝብ እንዲገለጽ ለመጠየቅ የወጡ ፋኖና ዘርማን የሚወክሉ ወጣቶችን ከቄሮዎች ጋር ለማጋጨት የተጠነሰሰው ሴራ ከሽፏል። ወጣቶቹ ጠዋት ላይ ኮከብ የሌለበትን ሰንደቃላማ ይዘው ሲወጡ፣ ለቄሮዎች “የእናንተን ትግል ለመቃወም ፋኖዎችና ዘርማዎች የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ነውና ተቃወሙዋቸው” የሚል መልዕክት እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን፣ የቄሮ አባላትም ወደ ወጣቶች ሄደው ከፋኖና የዘርማ አባላት ጋር ውይይት ሲያደርጉ፣ የተሰጣቸው መረጃ ሆን ተብሎ በህዝብ

በአማሮ ወረዳ እና በጉጂ መካከል እንደገና ግጭት በማገርሸቱ የሰዎች ሕይወት አለፈ

(ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) በድንበር በማካለል ስም የተነሳውና ለአንድ አመት ያክል የዘለቀው በአማሮ ወረዳ በሚኖሩ የኮሬ ብሄረሰብና በጉጂ ኦሮሞ መካከል የተከሰተው ግጭት ዛሬ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ ዛሬ ከዲላ ወደ አማሮ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት መኪና ሲያሽከረክር የነበረ፣ በጀሎ ቀበሌ ቅዱስ ዮሃንስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት የታጠቁ ሃይሎች ተኩስ በመክፈት ሹፈሩን ጨምሮ ሌላ አንድ ተሳፋሪ ወዲያዉ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል። ይህንን ተከትሎም ተኩስ በሁለቱ ወገን ተከፍቶ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የተኩስ ልዉወጥ እየተደረገ እንዳለና እስከ አሁን ሰዓት በኮሬ በኩል ብሻሮ ዘለቀ የሚባል አርሶአደር እንደተገደለ፣ ሌሎች ሶስት ደግሞ ቆስለዉ ኬሌ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአካባቢዉ የመከላከያ አባላት ቢኖሩም፣ ግጭቱን ማስቆም እንዳልቻሉ በተለይ መከላከል ያልቻሉት ደግሞ

Friday, July 27, 2018

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ግድያ በአስቸኳይ እንዲጣራ ተጠየቀ


Image may contain: 1 person, smiling, outdoor(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 20/2010) የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ግድያ በአስቸኳይ ተጣርቶ ፍትህ እንዲሰጥ በጎንደር ፣ ማክሰኝትና በባህርዳር ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ጠየቁ።
በጎንደር በነበረው ህዝባዊ ቁጣ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ግጭት ተፈጥሮ አንድ ወጣትና አንድ ታዳጊ በጥይት ተመተው ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ትላንት ጠዋት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተገድለው የተገኙት የአባይ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ጉዳይ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ብርቱ ሀዝን ፈጥሯል።

በአወዳይ አንድ ታጣቂ የነበረ ግለሰብ 3 ሰዎችን ገደሎ 5 ሰዎችን ደግሞ አቆሰለ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም )ሃሙስ እለት ከአስተዳደር ጥበቃ ስራ የተባረረው ከድር ኢብራሂም የተባለው ታጣቂ በህዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ 3 ሰዎችን ወዲያውኑ ሲገድል 5 ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ህዝቡ በወሰደው እርምጃም ሰውዬው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ታውቋል። ግለሰቡ ከስራ ከተሰናበተ በሁዋላ ታጥቆት የነበረውን የጦር መሳሪያ አለማስረከቡን ወኪላችን ገልጿል።

ኢትዮጵያውያን በኢንጂነር ስመኛው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን እየገለጹ ነው

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዜጎች በአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ በኢንጂነር ስመኛው ሞት የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ፣ የኢንጂኒሩ አሟሟት ሁኔታ በፍጥነት ተጣርቶ ለህዝብ እንዲገለጽ እየጠየቁ ነው። በጎንደር ከተማ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥተው ተቃውሞአቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ የከተማው የአገር ሽማግሌዎች ወጣቶችን በመምከር አረጋግተዋቸዋል። በባህርዳርና በደሴ እንዲሁ የከተማዋ ነዋሪዎች የሻማ ማብራት ስነስርዓት በማድረግ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የኢንጂነር ስመኜው በቀለን ሞት ተከትሎ በቁጣ ወደ አደባባይ ከወጡት የጎንደር ወጣቶች መካከል አንድ የ14 ዓመት ታዳጊና አንድ ሌላ ወጣት በጥይት ተመተዋል። ለኢሳት የድረሰው በምስል የተደገፈ መረጃ እንደሚያመለክተው በዛሬው ዕለት በጎንደር ለተጠራውን ሰልፍ ኃላፊነት የወሰደ የሚታወቅ አካል የለም። ይህም በመሆኑ በርካታ አክቲቪስቶች ከትናንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሰልፉ እንዳይደረግ እና ወጣቱ ከቁጣ ስሜት በመውጣት ነገሮችን በስክነትና በጥንቃቄ እንዲከታተል ሲጠይቁ ውለዋል። በጥይት የተመቱት ወጣቶች ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተከታተሉ መሆናቸውም ተመልክቷል።

ጠ/ሚ አብይ አህመድና ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ተነጋገሩ

 ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) አሜሪካ የሚገኙት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ለአንድ ሰዓት ያክል የነበራቸው ግንኙነት የትውውቅ እንደነበረና ተጨማሪ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ታውቋል። አርበኞች ግንቦት7 መሰረታዊ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲገነቡ ላለፉት 10 አመታት ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ከሆኑ በሁዋላም እርሳቸው የጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴ በመደገፍ የሃይል አማራጭ ትግን መግታቱን አስታውቋል። ሌላው የድርጅቱ አመራር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር በተፈቱ ማግስት ዶ/ር አብይ በቤተመንግስት ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል። አርበኞች ግንቦት7 ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ከሚያደርገው ውይይት በሁዋላ በአገር ውስጥ ትግል ስለሚጀምርበት ሁኔታ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Thursday, July 26, 2018

በሳውላ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደሙ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) በጎፋ ወረዳ ሳውላ ከተማ ላይ ዛሬ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፣ በደኢህዴን ባለስልጣናትና እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ለሳምንት የቆዬ ውዝግብ ነበር። ባለፈው ሳምንት ለዶ/ር አብይ የተደረገውን የድጋፍ ስልፍ ተከትሎ ህዝቡ የአካባቢውን ባለስልጣናት መቃወሙ ያስቆጣቸው የወረዳው ባለስልጣናት በወጣቶቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲዝቱ የሚያሳይ የድምጽ ማስረጃዎች ለኢሳት ደርሰው ነበር። ወጣቶቹ- “ከዶ/ር አብይ ጎን የማይቆም ደኢህአዴን የተባለን ድርጅት አንፈልግም” በማለት ዛሬው ቭተቃውሞአቸውን ሲገልጹ እንደነበር ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልጸዋል።

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ

Image may contain: 1 person, beard and outdoor( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) ግድቡን በዋና ሃላፊነት ሲመሩ የነበሩት ኢንጂነር ስመኛው በቀለ መስቀል አደባባይ ከዋናው መንገድ ገባ ብሎ በቪ 8 መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ መገኘቱን የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ ዘይኑ፣ ኢንጂነር ስመኛው ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው እንደነበረ፣ በቀኝ እጃቸው በኩል ኮልት ሽጉጥ መገኘቱን ገልጸዋል። ፖሊስ የአይን እማኞችንና ማስረጃ ይሰጣሉ የተባሉትን ሰዎች ይዞ ምርመራ እያደረገ መሆኑን፣ ቢሮአቸውንም ፈትሾ መረጃ ማሰባሰቡን ተናግረዋል። የኢንጂነሩ አሟሟት በርካታ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። በዜናው የተደናገጡ ወጣቶች በድንገት ተሰባስበው

Tuesday, July 24, 2018

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ።

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። የእርቅ ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ የሁለቱም አባቶች የተገናኙበት የጋራ የጸሎት ስነስርአት ተካሂዶ አንደነበር ታውቋል። ከሐገር ቤት የመጡት አባቶች በውጪ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት የጸሎት ስነስርአት ላይ ሲገኙ የውጪ ሲኖዶሱ አባላት ደግሞ በሐገር ቤቱ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ተሰምቷል። ስምምነታቸው በቀጣዮቹ ቀናት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። አባቶቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋርም ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

በወለጋ ደምቢዶሎ አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ

No automatic alt text available.(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በወለጋ ደምቢዶሎ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ።
ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልታወቁ ሰዎችም ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
በባሌ ጎባ የተከሰተው ግጭት ዛሬም መቀጠሉን የገልጹት ነዋሪዎች መንግስት በአስቸኳይ ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።
በባቢሌ በጭናክሰን ውጥረቱ መባባሱን ያገነኘው መረጃ ያመልክታል።
በተያያዘ ዜናም በደሴ ባልታወቁ ሃይሎች በተፈጸመ የስለት መሳሪያ ጥቃት በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

በወለጋ ደምቢዶሎ አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በወለጋ ደምቢዶሎ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ።
ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልታወቁ ሰዎችም ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
በባሌ ጎባ የተከሰተው ግጭት ዛሬም መቀጠሉን የገልጹት ነዋሪዎች መንግስት በአስቸኳይ ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።
በባቢሌ በጭናክሰን ውጥረቱ መባባሱን ያገነኘው መረጃ ያመልክታል።
በተያያዘ ዜናም በደሴ ባልታወቁ ሃይሎች በተፈጸመ የስለት መሳሪያ ጥቃት በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት አምጽ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከትላንት ሌሊት ጀምሮ አምጽ መቀስቀሱ ተሰማ።
በጥይትና በአስለቃሽ ጢስ በርካታ እስረኞች ተጎድተዋል።
በዞን አራት የሚገኙ እስረኞች እንፈታ የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ የተጀመረው አመጽ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ውጥረት ማንገሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በአከባቢው መንገዶች መዘጋታቸው ተገልጿል።
እስረኞች የድረሱልን ጩሀት እያሰሙ መሆኑም ታውቋል።በተመሳሳይ በደብረማርቆስ ማረሚያ ቤት በተቀሰቀሰ አመጽ ቤቶች መቃጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በአርባምንጭ እስር ቤት ውስጥም ተቃውሞ ተነስቷል። በርካታ እስረኞች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል።

በፍኖተሰላም ህዝቡ በህወሀት ላይ ከፍተኛ ቁጣ አሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በምዕራብ ጎጃም ፍኖተሰላም በተካሄደ ስብሰባ ህዝቡ በህወሀት ላይ ከፍተኛ ቁጣ ማሰማቱ ተገለጸ።
ላለፉት 27 ዓመታት በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸምው ግፍና መከራ በህዝቡ በዝርዝር ተነስቶ የህወሀት አገዛዝ ላይ ውግዘት መቅረቡን ያገኘነው መረጃ ያምለክታል።
በህዝብ ላይ ይሄ ሁሉ መከራ ሲደርስ ብአዴን የት ነበረ በሚል በአመራሮቹ ላይ ተቃውሞ መሰማቱን ለማወቅ ተችሏል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ድጋፍ ለማሳየትና ከለውጡ ለመጓዝ አስተዋጾአችን ምን መሆን አለበት በሚል ለመምከር የተጠራው ስብሰባ አጀንዳው ተቀይሮ የዓመታት ብሶት የተገለጸበት መድረክ ሊሆን መቻሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ እንደግፋለን አሉ

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ገለጹ።
የወንጌል አማኞቹ ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማሕበራዊ መስኮች በተወጠረችባቸው ጊዚያት ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ልመና ሲያደርጉ እንደነበረ ጠቅሰው አሁንም ለተጀመረው የሰላምና የእርቅ ጉዞ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ቃል በመግባት መግለጫ አውጥተዋል።
እሁድ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ጉባዔ ላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል የተደረሰው የሰላም ስምምነት አድናቆት ተችሮታል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ላበረከተው አስተዋጾ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኤርትራውያን ፌስቲቫል ላይ ተገኝተው የእውቅና ሽልማቱን የተረከቡት የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።
በፌስቲቫሉ ላይ የሁለቱ ሀገራትንና የአፍሪካውን ቀንድ ሰላም የተመለከተ ጉባዔ ተካሄዷል። በምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎችም ቀርበዋል።

በደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጂድ ውስጥ ጥቃት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ።

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በትናንትናው እለት በደሴ ከተማ ሸዋ በር በመባል በሚጠራው መስጂድ ውስጥ ድምጽ አልባ የስለት መሳሪዎችን ይዘው በመግባት መስኪዱ ውስጥ የነበሩ ምእመናን ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በመስጅዱ ሃይማኖታዊ ፀሎት በማድረግ ላይ እያሉ ቁርአን እናስቀራለን በሚሉና አናስቀራም በሚሉ መሃከል አለመግባባት መፈጠሩን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በወቅቱ በተከሠተው ግጭት በ11 ሰላማዊ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጉዳተኞቹ በደሴ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ከተጎዱት ውስጥ አንድ ሰው ከባድ ጉዳት

የማምረቻ እንዱስትሪዎች በዶላር እጥረት ለቅሶ ላይ ነን ሲሉ ባለሀብቶች ተናገሩ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኢትዮጵያ የማምረቻ እንዱስትሪ ባለሀብቶች ከአዲሱ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ከአቶ ይናገር ደሴ ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም ያለውን የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ ለውጭ ባለሀብቶች መሰጠቱ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣባቸው ነው። የሲዲኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤት 800 ሰራተኞችን ቢያስተዳድሩም፣ ወደ አምራች እንዱስትሪ የገቡበትን ቀን እየረገሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የብረታብረት አምራች ድርጅት ወኪል የሆኑት ግለሰብ ደግሞ 3800 ሰራተኞች እንዳላቸው ይናገራሉ። መንግስት ካወጣው ህግ አንጻር እራሱን ራሱን መፈተሽ አለበት የሚሉት ወኪሉ፣ ብሄራዊ ባንክ በሚከተለው የተዛባ አሰራር ችግር ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል። ሌላው ባለሀብት ደግሞ በአለም ላይ እንድንወዳደር የሚያስችሉን የመሰረተ ልማቶችና የገንዘብ አቅርቦት ሳይኖር፣ ምርት ወደ ውጭ

Monday, July 23, 2018

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ባደረጉት ዉይይት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባረው የነበሩ መምህራን ወደሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ አስታወቁ

(ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም )በጠቅላይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከመላው ኢትዮጵያ ከሃምሳ ዩኒቨርሲቲዎች ከተወጣጡ 3 ሽህ 175 የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር በአገሪቱ የከፍተኛ የትምህርት ጥራት፣ አገራዊ አንድነት፣ አገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለ ብልሹ አሰራር እና ሌብነት፣ አጠቃላይ የትምህርት ፖሊሲ፣ ብቃት እና ስነምግባር ያለው ዜጋ ስለማፍራት እንዲሁም ጥናት እና ምርምሮችን በተመለከተ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ውይይት አድርገዋል። በስብሰባው ላይ የተገኙት መምህራንም ስለ አገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ስለ መማር ማስተማሩ ተግዳሮቶች አስመልክተው ጥያቄዎቻቸውን አቅርበው ከጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በትምህርት ጉዳይ አስመልክቶ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መምህርነት የተከበረ ሙያ መሆኑንና በዘርፉ ለሚያጋጥሙ ችግሮች የጋራ ኃላፊነት መውሰድ ይገባናል። የትምህርት ጥራት ችግር መኖሩን አምነው ይህን ለመቀየር በሠፊው እየሠራን ነው ብለዋል። የመምህራን ደሞዝና ጥቅማጥቅም ዝቅተኛ መሆኑንና ይህንንም ለማሻሻል ከሚመለከተው

በባሌ ጎባ አንጻራዊ መረጋጋት ቢታይም አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ነዋሪዎች ገለጹ

(ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ ደም አፋሳሽ የነበረው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ አንጻራዊ መረጋጋት ታይቶበታል። ባለፈው ረቡዕ የዞኑ ባለስልጣናት የባሌ ገበሬዎች አመጽ መሪ የነበሩትን የሃጂ አደም ሳዶን ሃውልት ለማቆም በሚል ህዝቡን አወያይተው የነበረ ሲሆን፣ በእለቱ አብዛኛው ተሰብሳቢ ሃውልቱ ቢቆም ችግር እንደሌለው ይሁን እንጅ፣ ሃውልቱ በከተማው መሃል አደባባይ ላይ የሚገኘው የቀይ ቀበሮ ሃውልት በሚሰራበት ቦታ ላይ ይሁን መባሉን የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል መቃወሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ብዙ ገንዘብ የፈሰሰበትን ሃውልት ከማፍረስ ሌላ ቦታ ላይ መገንባቱ ይሻላል በሚል የተከራከሩ ቢሆንም፣ ባለፈው ቅዳሜ የከተማው ከንቲባን ጨምሮ የዞን አመራሮች ውሳኔውን ለማስፈጸም በመንቀሳቀሳቸው ግጭት ተከስቷል። ግጭቱ ሃይማኖታዊ ቅርጽ እየያዘ መምጣቱን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ በተለይም የኦሮምያ ፖሊስ ከሁሉም ጎን ሆኖ ችግሩ እንዳይባባስ ማድረግ ሲገባው፣ በአንድ ወገን ላይ ጥቃት መፈጸሙ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አካባቢው ባይገቡ ኖሮ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችል እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማዋ ከንቲባ ዘይነባ ጣሀ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል እንደተናገሩት በግጭቱ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ብዙዎችም ተጎድተው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። የዞኑ አመራሮች ከህብረተሰቡ ጋር ከህብረተሰቡ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት በስብሰባው ላይ የተሳተፉት አካላት አብዛኛዎቹ የሐውልቱን መተከል ይቃወሙት ነበር ሲሉ ከንቲባዋ ቢናገሩም፣ በስብሰባው የተሳተፉት

በጅግጅጋ ወጣቶች በአብዲ ኢሌ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ አደረጉ

(ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወጣቶቹ ተቃውሞዋቸውን ያሰሙት የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ አገዛዝ በመቃወም እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ተጠርጥረው የተሳሩ ዜጎች እንዲፈቱ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እስር ቤቶች እንዲዘጉ ለመጠየቅ ነው። ወጣቶቹ ተቃውሞአቸውን በሚያሰሙበት ወቅት አብዲ አሌ ወታደሮቹን ልኮ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ማድረጉን አቶ አሊ አብዲ ሃሰን ከጅግጅጋ ገልጸዋል። በጥቃቱ እስካሁን የደረሰውን ጉዳት ለማወወቅ ባይቻልም፣ ብዙ ወጣቶች እንደቆሰሉ የሚደርስን መረጃ ያመለክታል። አዲስ አበባ የሚገኙ የሶማሊ ክልል አገር ሽማግሌዎች ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ሙሃመድ አሊ ጣሂር ተናግረዋል።

በባሌ ጎባ በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ

Image may contain: sky and outdoor(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በባሌ ጎባ በማንነትና ከእምነት ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ጥቃት ለበርካታ ሰዎች መገደል ምክንያት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።
በአካባቢው የታጠቁ ሃይሎች በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የመከላከያና የፌደራል ወታደሮች ቢገቡም የባሌ ጎባ ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸው ታውቋል።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ጥቃቱን ለመከላከል የመጡት የፌደራል ወታደሮች ቁጥራቸው ጥቂት በመሆኑ ተጨማሪ ሃይል ካልመጣ ከፍተኛ እልቂት ሊከሰት ይችላል።

ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ተደረሰ

Image may contain: 9 people, people standing(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ።
በዚህም የቀድሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ የቤተክርስቲያኒቱን መንበር እንዲይዙ ይደረጋል ማለት ነው።
አሁን በሃገር ቤት ባለው ሲኖዶስ ያሉት አቡነ ማቲያስ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ስራ እንዲሰሩ ተወስኗል ተብሏል።

በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊጎትተው አይገባም ተባለ

Image may contain: 1 person(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊጎትተው አይገባም ሲሉ ጠቅላይ ኢታማጆር ሹሙ አሳሰቡ።
ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ሰአረ መኮንን በኢትዮጵያ የታየው ለውጥ ከዘራችን ይልቅ በኢትዮጵያዊነታችን እናስብ የሚል ነው በማለትም ተናግረዋል።
በፓርቲዎች ስኩቻ ውስጥ ግን አያገባንም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከሐገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ጋር የተወያዩትና በመከላከያ ሰራዊቱ ፕሮግራም ላይ በተላለፈው መልዕክታቸው ሰራዊቱ ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ ለሕገመንግስቱና ለሕገመንግስታዊ ስርአቱ እንደሚቆም አረጋግጠዋል።
በፖለቲካ ሁኔታዎች ልንጎተት አይገባም በማለት ያሳሰቡት ጄኔራል ሰአረ መኮንን የፓርቲዎ ሽኩቻና ልዩነት የራሳቸ ጉዳይ ነው እኛ ወደዚህ ከተሳብን የባለሙያ ተግባር አይሆንም ብለዋል።

ሕገ ወጥ የመሳሪያና የገንዘብ ዝውውር እየጨመረ ነው

No automatic alt text available.(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ ሕገ ወጥ የመሳሪያና የገንዘብ ዝውውር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ።
ይህ በሃገሪቱ ሰላምና ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
የጦር መሳሪያዎቹ ከቱርክ ተነስተው በሱዳንና በጅቡቲ በኩል እየገቡ መሆናቸውንም ከኮሚሽነሩ መግለጫ መረዳት ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በጥቁር ገበያና በመደበኛ የሚመነዘረው የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተቀራራቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታወቋል።
በዶላር እስከ 10 ብር የነበረው ልዩነት ወደ ሳንቲም ደረጃ መውረዱ ተመልክቷል። በሳምንቱ መጨረሻ 10 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የፌደራል ፖሊስ ያስታወቀው።
በተመሳሳይ ሕገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውሩ የቀጠለ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ አቅራቢያ ባካሄዱት ክትትል ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችንም ሆነ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሩን በመቆጣጠር ላይ መሆናቸው ተመልክቷል።

Saturday, July 21, 2018

ትላንት በማዳበርያ በህገወጥ መንገድ በማዳበርያ ሊወጣ ሲል የተያዘው 6 ኩንታል ገንዘብ ተቆጥሮ ሃያ አራት ሚልዮን ብር መሆኑ ተረጋግጦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአደራ እንዲቀመጥ ተደርጓል።

ትላንት በማዳበርያ በህገወጥ መንገድ በማዳበርያ ሊወጣ ሲል የተያዘው 6 ኩንታል ገንዘብ ተቆጥሮ ሃያ አራት ሚልዮን ብር መሆኑ ተረጋግጦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአደራ እንዲቀመጥ ተደርጓል።
ንግድ ባንክ በይፋ ያወጣውን ደብዳቤ ያንብቡት
No automatic alt text available.Image may contain: one or more people

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከብሄራዊ መረጃና ደህነት፣ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር ሆኖ ህብርተሰቡን ማዕከል ባደረገ መልኩ በተከሄደው የጥቂት ቀናት ዘመቻ ገንዘቡ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ጥቂት ቀናት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በተካሄደው ዘመቻ ከ1ሺህ በላይ የነፍስ ወከፍና የቡድን ጦር መሳሪያ እንዲሁም 80 ሺህ የሽጉጥና ክላሽ ጥይቶች ወደ አገር ሊገቡ ሲል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡
ከገንዘቡ በተጨማሪ በህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳፉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገባቸው መሆኑንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

Friday, July 20, 2018

የምህረት አዋጁ ጸደቀ።

Image may contain: one or more people and people sitting(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010) የምህረት አዋጁ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱና የሚፈለጉ እንዲሁም የተፈረደባቸውን ሰዎች ጭምር ነጻ የሚያደርግ መሆኑም ታውቋል። ፓርላማው በአስቸኳይ ስብሰባው ያጸደቀው የምህረት አዋጁ ከግንቦት 30/2010 በፊት በወንጀል የሚፈለጉና የተፈረደባቸው እንዲሁም የተከሰሱ ሰዎችን ሙሉ በሙሉ ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። የምህረት አዋጁ የኮበለሉ የመከላከያ ሰራዊት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያካሂዱት ውይይት ጥላቻና መከፋፈልን በማስወገድ ለአንድ ሃገር በጋራ ለመቆም እንደሚያግዝ የጉብኝቱ የአቀባበል ኮሜቴ ገለጸ።

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያካሂዱት ውይይት ጥላቻና መከፋፈልን በማስወገድ ለአንድ ሃገር በጋራ ለመቆም እንደሚያግዝ የጉብኝቱ የአቀባበል ኮሜቴ ገለጸ። በዋሽንግተን ዲሲ የአቀባበል ኮሜቴ ሰብሳቢዎች በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጡት መግለጫ ላይ ይሄ ለውጥ ከመምጣቱ በፊት የችግሩ ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት እድሉ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 28/2010 በዋሽንግተን ኮንቬንሽን ሴንተር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለምንም ምዝገባ ለ25 ሺ ሰዎች መድረኩ ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል። በኋላ ላይ በሌላ አዳራሽ በሚኖረው ውይይት ደግሞ 1 ሺ 5 መቶ ሰዎች የጥያቄና መልስ እድል እንደሚሰጣቸው ተግለጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያውያን ያለፈውን በመርሳት አዲስ ምዕራፍ ተሰፍቶ የበኩላቸውን ለማድረግ ይሻሉ። በተለያየ ምክንያት ከሃገር የተሰደዱና በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የለውጥ ጉዞ ይደግፋሊ። ይህ ሲባል ግን ያለፈው ግፍና በደል፣ግድያና ስቃይ እንዲረሳ

Thursday, July 19, 2018

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ 2 ሺህ ከሚበልጡ የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይም 2 ሺህ 400 የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች መካፈላቸው ተገልጿል።
በውይይት መድረኩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እና ገለፃ ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር
ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም በመቻቻል፣ በመከባበር እና በሌሎች የኢትዮጵያ እሴቶች ዙሪያም ለመድረኩ
ተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010) ለእረፍት ተበትኖ የነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተነገረ።
ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባውን በነገው እለት የሚያካሂደው በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ለነበሩ ሰዎች ምሕረት ለመስጠት በሚቀርብ ረቂቅቅ አዋጅ ላይ ለመምከር ነው ተብሏል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ረቂቅ አዋጅ እና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ፓርላማው በነገው ውሎው የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተለያዩ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉ ሰዎች ምህረት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያጸድቃል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተጓደሉ የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ለመሾም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010)በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀውን ችግር በንግግር ለመፍታት ከአዲስ አበባ የተወከሉት የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል።
ልዑካኑ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት በቤተመንግስት ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተወያይተዋል።
ከአዲስ አበባ የመጡት የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ማለዳ ዋሽንግተን ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ የሚገኙ አባቶችና ምዕመናን ከፍተኛ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኤርትራ መንግስት ድንበር ላይ ሰፍሮ የነበረውን ጦሩን እንዲነሳ አደረገ



(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ12/2010) የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ አጎራባች ድንበር ለይ ሰፍሮ የነበረውን ጦሩን ከአካባቢው እንዲነሱ ማድረጉን ሮይተርስ ዘገበ ።
በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሰፈረው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እንዲነሳ የተደረገው በሁለቱ ሀገራት መካከል የተወሰደውን የእርቅ እርምጃ መነሻ በማድረግ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ኢትዮጵያ ከግጭቱ ወዲህ የመጀመሪያ የተባሉትን አምባሳደር አቶ ሬድዋን ሁሴን በአስመራ መመደቧ ታውቋል ።

ባለስልጣናት ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 12/2010)ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና ለኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስኪያጅ መሾማቸው ተነገረ።
ከሁለቱ መስሪያቤቶች የተነሱት የቀድሞ የስራ ሃላፊዎች ደግሞ በሌላ ቦታ ተመድበዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የአዲስ አበባ መንገዶች ባልስልጣናት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ናቸው።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አርዓያ ግርማይ ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው ነው የተገለጸው።

Wednesday, July 18, 2018

ሕገወጥ የመሳሪያ ዝውውር ተጧጡፏል ተባለ

No automatic alt text available.ሕገወጥ የመሳሪያ ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ።
በአንድ ቀን ብቻ መትረየስን ጨምሮ 73 መሳሪያዎች ሰሜን ሸዋ ላይ መያዛቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል።
የኦሮሚያ ክልል የገጠር ዘርፍ አደረጃጀት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳስታወቁት 20 ሽጉጥና አንድ መትረየስ የጫነች የቤት ተሽከርካሪ ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረሊባኖስ ወረዳ ላይ በቁጥጥር ስር ውላለች።
ትላንት መሳሪያ ጭና የተያዘችው ተሽከርካሪ ከደብረማርቆስ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረች መሆኑንም ተመልክቷል።
በተመሳሳይ በዚሁ ቀን 53 ሽጉጦችን ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ ሰሜን ሸዋ ዞን ቅምብቢት ወረዳ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉንም አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ሰሜን ሸዋ ዞን ላይ በአንድ ቀን 73 ሽጉጦችና አንድ መትረየስ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሽጉጦቹን በምስል ማየት እንደተቻለውም ሩሲያ ስሪት ማካሮቭ መሆናቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ከስልጣኑ ማዕድ የተገፉ ወገኖች እንዳቀነባበሩት የተገመተ ግጭት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች መከሰቱ ይታወቃል።
ይህም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ይሁን የተራ ንግድ የታወቀ ነገር የለም።

ዐቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱት ክስ እንዳይቋረጥ ጠየቀ

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአርበኞች ግንቦት 7 ስም ከአሸባሪነት ዝርዝር ቢነሳም ፣ በስሙ የተከሰሰሱትና በእስር ላይ የሚገኙት አባሎች ክሳቸው መነሳት የለበትም ሲል መከራከሩን ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ዘግቧል። ሐምሌ 10/2010 ዓም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በአርበኞች ግንቦት 7 ስም በእነ ሚፍታህ ሸሕ ሱሩር ክስ መዝገብ ከተከሰሱት 77 ግለሰቦች መካከል ያልተፈቱት 46 ተከሳሾች የቀረቡ ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግ ክሳቸው መቋረጥ የለበትም ሲል ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱ የተወካዮች ምክር ቤት አርበኞች ግንቦት 7 ከፀረ ሽብር አዋጁ ስሙ እንዲነሳ ካደረገ በኋላ የሽብር ክሶች እንዲቋረጡ “የስራ መመርያ” ይተላለፋል ብሎ እየጠበቀ እንደነበር፣ ነገር ግን እንዳልደረሰው ገልፆአል። ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ድርጅት ስም ከፀረ ሽብር አዋጁ መነሳቱን በመግለፅ መፈታት እንዳለባቸው ቢገልፁም፣ ዐቃቤ ሕግ “ድርጊቱ የተፈፀመው የድርጅቱ ስም ከፀረ ሽብር አዋጁ ከመነሳቱ በፊት ነው። የድርጅቱ ስም ከአዋጁ በመነሳቱ ብቻ ክሳቸው ሊቋረጥ አይገባም። ክርክሩ መቀጠል አለበት።” ሲል ከፀረ ሽብር አዋጁ ስማቸው በተነሳለቸው ድርጅቶች ስም የተመሰረተው የሽብር ክስ መቋረጥ የለበትም ሲል ተከራክሯል። ከሶስት ቀን በፊት ከዐቃቤ ሕግ መስርያ ቤት የተወከለ ሰው ቂሊንጦ እስር ቤት እስረኞችን ባወያየበት ወቅት፣ በሽብር ተከስሰው ያልተፈቱት አቤቱታ ሲያቀርቡ “በዚህ ክስ ተከስሶ እስካሁን እስር ቤት ያለ ሰው ስለመኖሩ አናውቅም” የሚል መልስ እንደሰጣቸው ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ መግለጻቸውን ጋዜጠኛ ጌታቸው በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል። ፍርድ ቤቱም “የድርጅቱ ስም ከፀረ ሽብር አዋጁ መነሳቱን ብንሰማም፣ የስራ መመርያ አልደረሰኝም” በሚል ለሀምሌ 17/2010 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሃረሪ ፖሊስ ኮሚሽን መሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ የበርካታ ሰዎች አጽም ተገኘ

Image may contain: one or more people and outdoor( ኢሳት ዜና ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓ/ም ) ዛሬ ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓም በፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ውስጥ በጓሮ በኩል የወዳዳቁ የሰው አጽሞች የተገኙ ሲሆን፣ እንዲሁም አሰሳ ያደረጉት ቄሮዎች እዛው አካባቢ ሌላ በጆንያ የተጠቀለለ ሌላ አጽም አግኝቷል። አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦድሪን በድሪና ምክትሉ አቶ ነቢል መሃዲ እንዲሁም የኦህዴድ ተወካይ የሆኑት የሃረሪ ክልል ፍትህና ጸጥታ ሃለፊ አቶ አበበም በስፍራው ተገኝተዋል። አቶ አበበ ከፖሊሶች ባገኙት ጥቆማ መሰረት መሳሪያ ግምጃ ቤቱም እንዲከፈት ያስደረጉ ሲሆን፣ የመሳሪያ ግምጃ ቤቱ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች የተባሉ ግለሰብም “ ኮሚሽነር

በሀገር ቤት የሚገኘው ሲኖዶስ ኮሚቴ አባላት ተሸኙ

Image may contain: 3 people, people smiling(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 11/2010) በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኘውን ሲኖዶስ ወደ አንድነት ለማምጣት በሀገር ቤት የሚገኘውና ወደ አሜሪካ የሚያቀናው ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶሱና በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ አሸኛኘት ተደረገለት።
ፓትሪያሪክ አቡነ ማትያስ ወደ አሜሪካ ላቀኑት አባቶችም አባቶቻችንን ይዛችሁ ኑ መነጋገር ያለብንን ነገር በቤታችን እንነጋገራለን የሚል መልዕክት ማስተላለፈቻውም ተሰምቷል።
በዋሽንግተን ዲሲ የሚካሄደው የአባቶቹ ውይይትም ከሐምሌ 12 እስከ ሐምሌ 21/2010 እንደሚካሄድ ታውቋል።
ሁለቱን ሲኖዶሶች አንድ ለማድረግ በሀገር ውስጥና በውጪ በሚኖሩ የኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ጥረት ሲደረጉ መቆየታቸው ይነገራል።
ከዚህ በፊት ያልተሳኩ ነገር ግን ከፍተኛ መቀራረብ የታየባቸው ግኑኝነቶችም ተደርገዋል።
ጥረቱ አሁንም ቀጥሎ ባለፈው አንድ ዓመት ከስምንት ወር በሁለቱም በኩል የተዋቀረው ኮሚቴ አባቶቹን ለማገናኘት መንገድ ሲጠርግ መቆየቱንም ነው ከቤተክርስቲያኒቱ የወጣው መረጃ የሚያመለክተው።
የፊታችን ሐምሌ 12 የሚጀመረውና እስከ ሐምሌ 21/2010 የሚቆየው የአባቶቹ ግኑኝነትም ከተኬደው ርቀት አኳያ ውጤታም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በሀገር ቤት የሚገኘው ሲኖዶስ ኮሚቴ አባላት ተሸኙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 11/2010) በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኘውን ሲኖዶስ ወደ አንድነት ለማምጣት በሀገር ቤት የሚገኘውና ወደ አሜሪካ የሚያቀናው ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶሱና በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ አሸኛኘት ተደረገለት።
ፓትሪያሪክ አቡነ ማትያስ ወደ አሜሪካ ላቀኑት አባቶችም አባቶቻችንን ይዛችሁ ኑ መነጋገር ያለብንን ነገር በቤታችን እንነጋገራለን የሚል መልዕክት ማስተላለፈቻውም ተሰምቷል።
በዋሽንግተን ዲሲ የሚካሄደው የአባቶቹ ውይይትም ከሐምሌ 12 እስከ ሐምሌ 21/2010 እንደሚካሄድ ታውቋል።
ሁለቱን ሲኖዶሶች አንድ ለማድረግ በሀገር ውስጥና በውጪ በሚኖሩ የኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ጥረት ሲደረጉ መቆየታቸው ይነገራል።
ከዚህ በፊት ያልተሳኩ ነገር ግን ከፍተኛ መቀራረብ የታየባቸው ግኑኝነቶችም ተደርገዋል።
ጥረቱ አሁንም ቀጥሎ ባለፈው አንድ ዓመት ከስምንት ወር በሁለቱም በኩል የተዋቀረው ኮሚቴ አባቶቹን ለማገናኘት መንገድ ሲጠርግ መቆየቱንም ነው ከቤተክርስቲያኒቱ የወጣው መረጃ የሚያመለክተው።
የፊታችን ሐምሌ 12 የሚጀመረውና እስከ ሐምሌ 21/2010 የሚቆየው የአባቶቹ ግኑኝነትም ከተኬደው ርቀት አኳያ ውጤታም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 11/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ20 አመታት በኋላ የመጀመሪያውን መደበኛ በረራ ወደ አስመራ አደረገ።
ታዋቂ ሰዎችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሁለት ቡድን በሁለት አውሮፕላን ዛሬ አስመራ መግባቱም ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለም ላይ ከሚገኙ 50 ምርጥ አየር መንገዶች አንዱ መሆኑን ስካይትራክስ ትላንት ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ከፈነዳበት ግንቦት ወር 1990 ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ ቀጥሏል።
ሐምሌ 1/2010 በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተመራውን ልኡክ የያዘ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አስመራ የገባ መሆኑ ይታወሳል።
ነገር ግን ይህ ጉዞ በቀጥታ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የተደረገ ሳይሆን በጅቡቲ በኩል የተደረገ በረራ እንደነበርም ተመልክቷል።
የኤርትራ የአየር ክልል በይፋ መከፈቱን ተከትሎ ዛሬ አስመራ የገቡት 456

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ስራ ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 11/2010) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ትረስት ፈንዱ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በቀን 1 ዶላርና እንደ አቅሙ ለሃገሩ አስተዋጽኦ የሚያደርግበት አሰራር ነው።
ለዚሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ተከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለዲያስፖራው ያቀረቡትን የድጋፍ ጥሪ መነሻ በማድረግ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ትረስት ፈንድ ተቋቁሟል።
በዚሁም መሰረት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ነው የተገለጸው።
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመስራት ላይ የሚገኙ የውጭ ሃገር ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችም ይፋ ተደርገዋል።
ለዚሁ ስራም የትረስት ፈንዱ ድረገጽ እንደሚዘጋጅና በመላው አለም የሚገኙ የዲያስፖራው አባላት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ሁኔታዎች መመቻቸታቸው ተገለጿል።

አንዳርጋቸው ጽጌ አስመራ ገቡ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 11/2010) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ አስመራ ገቡ።
አቶ አንዳርጋቸው የመን ሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ታግተው ለአራት አመታት ያህል በወህኒ ቤት ማሳለፋቸው ይታወሳል።
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ የታገቱት ወደ አስመራ በመጓዝ ላይ በነበሩበት ወቅት እንደነበርም ይታወሳል።
የምርጫ 1997 ሰላማዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በሃይል ከተጨፈለቀ በኋላ ብዙዎች ከትግሉ ሜዳ ሲወጡና ከእንስቃሴ ሲገደቡ ትግሉን በሃይል ጭምር ማስቀጠል ይገባል በሚል ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ግንቦት ሰባትን የመሰረቱት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ነበሩ።

Monday, July 16, 2018

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረገው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 9 ቀን 2010 ዓ/ም )እሁድ እለት በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ላይ ህዝቡ 1500 ሜትር እርዝመት ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር እየወሰደ ላለው አወንታዊ እርምጃ ድጋፉን ገልጿል። በዚህ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የወረዳ አስተዳዳሪው አቶ በጋሻው ተክሉ “አጥፍቻለሁና ይቅር በሉኝ” ብለው ህዝቡን ይቅርታ ጠይቀው፣ መስራት ለሚችል ሃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ተናግረዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ላይም ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ህዝቡ መንገድና መብራትን ጨምሮ ሌሎች የመሠረተ ልማት አግልገሎት እንዲሟላለት ጠይቋል።

በዚገም ወረዳ በተነሳ ግጭት ወጣቶች ጉዳት ደረሰባቸው

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 9 ቀን 2010 ዓ/ም )በአዊ ዞን በዚገም ወረዳ በጉምዝና በአገው ብሄረሰብ ተወላጆች መካከል ተነስቶ በነበረው ግጭት ከሁለቱም በኩል 9 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ህዝቡን ለማወያየት የመጡ 4 የዞን አመራሮች፣ ህዝቡ ከክልል አመራር ካልመጣና አጠቃላይ የወረዳውን ችግር ካላወያየን በሚል አመራሮቹን ለ3 ቀናት ያክል አስሮ ለፖሊስ በአደራ መልክ ያስረከበ ሲሆን፣ የታሰሩት አመራሮች ሌሊት ላይ በመለቀቃቸው ወጣቶች ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ለማፈራረስ ሲሞክሩ በተተኮሰ ጥይት 4 ወጣቶች ተመተው አንዱ በቻግኒ ሆስፒታል፣ 3 ወጣቶች ደግሞ ባህርዳር ሪፈራል ሆስፒታል ተልከዋል። ህዝቡ ከ31 በላይ ፖሊሶችን ያሰረ ሲሆን፣ የልዩ ሃይል ወደ ከተማው መግባቱም ታውቋል። ከጤና ጣቢያ፣ ወፍጮ ቤትና ማህበራት በስተቀር ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ የለም። ሁሉም የወረዳዉ አመራሮች ከተማውን ለቀው ቻግኒ ገብተዋል። ወረዳውን ህዝቡ የመረጣቸው ኮሚቴዎች እየመሩት መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ጣሊያን 450 ስደተኞች በሲሲሊ አሳረፈች

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010) ጣሊያን 450 ስደተኞች በሲሲሊ እንዲያርፉ ፈቀደች።
ጣሊያን ውሳኔውን ያሳለፈችው ፈረንሳይ፣ፖርቹጋል፣ማልታ፣ጀርመንና ስፔን እያንዳንዳቸው 50 ስደተኞችን እንወስዳለን ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
በሲሲሊ ደሴት በፖዛሎ የወደብ ዳርቻ እንዲያርፉ የተደረጉት 57 ሕጻናትና ሴቶች ብቻ መሆናቸው ታውቋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሶስት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ አስመራ ተመለሱ።

Image may contain: one or more people, people standing and outdoor(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010)ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሶስት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ አስመራ ተመለሱ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የአዲስ አበባውን የኤርትራ ኤምባሲ በይፋ እንደገና መክፈታቸውም ታውቋል። በአዲስ አበባና በሃዋሳ ጎዳናዎች ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸውና በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ስነስርአት ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ አስመራ ሲመለሱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል። ቅዳሜ ማለዳ ከ20 አመታት በኋላ አዲስ አበባ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት እንዲሁም በሃዋሳና በሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እንደተናገሩት ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የተደረገው አቀባበል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያልታየና ደማቅ ነበር። ላለፉት 27 አመታት በየትኛውም መንግስታዊ መድረኮች ላይ ታይተው የማይታወቁ ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ጭምር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ተቀብለዋል። ፕሬዝዳትን ኢሳያስ አፈወርቄ በሚሊኒየም አዳራሽ በአማርኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር ፍቅራችንንና ስምምነታችንን ለማወክ የሚፈልጉትን ጨርሶ አንፈቅድላቸውም ብለዋል። “ክብር ለኢትዮጵያ ሕዝብ “በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ “የኤርትራን ሕዝብ የሰላምና የፍቅር መልካም ምኞት የማቀርበው በደስታ ነው”ሲሉ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። በአማርኛ ንግግራቸውን የቀጠሉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ “እውን ስላደረጋችሁት ድል የተመላበት ታሪካዊ ለውጥ እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ በአዳራሹ ለተሰበሰበው ሕዝብ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል። በባህላችንና በታሪካዊ ጥልቅ ጥቅሞቻችን ላይ ለመንዛት የተሞከረውን ጥላቻና ትንኮሳ

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የፌደራል የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ገብተው ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጥሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ትዕዛዝ ሰጡ።



(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010) በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የፌደራል የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ገብተው ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጥሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ትዕዛዝ ሰጡ። ሁለቱም ክልሎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ መሰረት የጸጥታ አካላት እንዲገቡም ስምምነታቸውን መግለጻቸው ተመልክቷል። ለመቶሺዎች መፈናቀል፣ ለብዙዎች ሞትና አካል መጉዳል ምክንያት የሆነው ግጭት ከአመት በላይ ዘላቂ መፍትሔ ሳያገኝ ቆይቷል። ይህንን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት

በኤርትራ ትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸውን አስታወቁ።

No automatic alt text available.(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010) በኤርትራ ትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸውን አስታወቁ። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዲሃን/ እና የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ባወጡት መግለጫ በኤርትራ ሲያካሂዱ የነበረውን የትጥቅ ትግል በማቆም በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ወስነዋል። ለሁለቱም ድርጅቶች እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ምክንያት የሆናቸው በኢትዮጵያ እየተካሄ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ተስፋ የሚሰጥ በመሆኑ ነው ብለዋል።

Sunday, July 15, 2018

ኢትዮጵያና ኤርትራን ማንም ሊለያይ አይችልም- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ

Image may contain: 3 people, outdoorኢትዮጵያ እና ኤርትራን ማንም ሀይል ሊለያይ የችልም አሉ ጠቅላይ መሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ይህን ያሉት በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ የኢትዮጵያ 
እና የኤርትራ መንግስት የሰላም ማብሰሪያ መድረክ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሲለያዩ ግንጥል ጌጥ ናቸው፤ አንድ ሲሆኑ ግን ከራሳቸው አልፈው ለአፍሪካም ፈርጥ ይሆናሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመልክ፣ በአንድነታችን ተመሳሳይ ነን፤ ይህን አንድ የሆነ ህዝብ ማንም ሀይል ሊለያይ አይችልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ።

እስካሁን የባከነውን ጊዜ ለማካካስ እንሰራለን- ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተለያይተው በነበሩበት ወቅት የተቃጠለውን ጊዜ ለማካካስ እንሰራለን አሉ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይህን ያሉት በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስት የሰላም ማብሰሪያ መድረክ ላይ ነው።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዚሁ ወቅት፥ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ አንድ ህዝቦች ናቸው ማንም ሀይል ሊነጣጥለን አይችልም ብለዋል።
ከዚህ በኋላ ባለው ጊዜም አብረን ወደ ፊት ለመራመድ ቆርጠን ተነስተናል ሲሉም ተናግረዋል።

Saturday, July 14, 2018

Eritrean President Arrives in Addis Ababa

Eruptious welcome to Eritrean President Isaias Afwerki as he arrived in Addis Ababa early Saturday. He was welcomed by Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed, who was in Asmara last week in his first visit to Eritrea. Tens of thousands of residents of the capital Addis Ababa and its environs lined up the streets from Bole International Airport to the National Palace singing and dancing, calling out the names of the two leaders and waving the flags of the two nations. 

ከብዙዎቹ በጥቂቱ የዛሬ የሸገርና የሀዋሳ ፎቶዎች

Image may contain: 1 person, standing and suit
Image may contain: 1 person, standing and suit
Image may contain: 2 people

Friday, July 13, 2018

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ (Ermias Legesse Wakjira)

Image may contain: Ermias Legesse Wakjira, sitting and indoorለአዲስ አበባ አስተዳደር አዲስ "ከንቲባ" ለመሾም እንደተዘጋጁ በተለያዩ ሚዲያዎች እየተነገረ ነው። የሚሾሙት "ከንቲባም" የከተማው ምክር ቤት አባል አለመሆናቸው እየተገለጠ ነው። በእኔ እምነት ይህ አካሄድ ህገ ወጥ ከመሆኑም በላይ ተመራጭ አካሄድ አይደለም። እንደ አንድ ሞጋች ደጋፊዎ ምክንያቶቼንና መፍትሔውን ለመጠቆም እፈልጋለሁ።
#ምክንያት አንድ -: የአዲስ አበባ ምክርቤት በህዝብ የተመረጠ ነው/ የተመረጠ አይደለም የሚል ክርክር ውስጥ ሳልገባ ምክርቤቱ የተሰጠውን አምስት አመት ጨርሷል። ከዚህ በኃላ ይሄ ምክር ቤት ቀጠለ ማለት ከተሰጠው የስራ ዘመን በላይ በህገ ወጥነት ቀጠለ ማለት ነው። በራሳችሁ ህገ መንግስትም ሆነ በአስተዳደሩ ቻርተር ያለ ህዝብ ምርጫ የመንግስት ስልጣን መያዝ እንደማይቻል በግልፁ ተቀምጧል።

የለውጥ ጸር የሆኑ ሃይሎች በኦሮምያ ላይ ጦርነት መክፈታቸውን አቶ አዲሱ አረጋ ተናገሩ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኦሮምያ ክልል የገጠር የፖለቲካና ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባወጡት ጽሁፍ፣ የለውት ጸር የሆኑ ሃይሎች ኦሮሞ ከባድ መስዋትነት ከፍሎ ያስመዘገበውን ድል ለማኮላሸትና ለመቀልበስ ከምንጊዜውም በላይ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። እነዚህ ሃይሎች ድላችንን ዋጋ ቢስ ለማድረግና ኦሮምያን የብጥብጥ አውድማ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው ያሉት አቶ አዲሱ፣ ኦሮሞን ለማንበርከክ ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱ ከሶማሊ ክልል አዋሳኝ ድንበር አካባቢ ጦርነት በመክፈት ሰላማዊ ዜጎችን መግደል፣ ንብረቱን በመቀማት ማፈናቀል ይገኝበታል ብለዋል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ፣ በምስራቅ ሃረርጌ ጉርሱም፣ ጭናክሰንና ባቢሌ ጦርነት ተከፍቶብናል የሚሉት አቶ አዲሱ፣ በዛሬው እለት ብቻ 3 የኦሮሞ ፖሊሶች፣ አንድ የመከላከያ አባልና 1 ሲቪል

የውጭው ሲኖዶስ ለሰላሙ ድርድር ዝግጁ ነኝ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራው በውጭ ሃገር የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰላሙ ድርድር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ።
በእርቅ መድረኩ ላይ የሚገኙ ሶስት ሊቃነጳጳሳት መሰየማቸውንም ይፋ አድርጓል። የጥላቻና የመከራው ዘመን ያብቃ ሲልም ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪውን አቅርቧል።
በሚቀጥለው ሳምንት ሐሙስ በሚጀመረውና ከሐምሌ 12 እስከ 21 እንዲቀጥል መርሃ ግብር በተያዘለት የእርቅ ፕሮግራም እንዲሳካ ቅዱስ ሲኖዶሱ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ይፋ አድርጓል።
በፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራውና በውጭ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ እስከዛሬም በሩን ከፍቶ ሲሰራ መቆየቱንም አስታውቋል።
በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶሱ በዋና ጸሃፊው አቡነ ሚካኤል ስም ያወጣው መግለጫ የጥላቻና የመከራው ዘመን አብቅቶ በኢትዮጵያ ሰላም ፍቅርና አንድነት ይሰፍን ዘንድም ምኞቱን ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ነገ ወደ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መንግስት ይፋ አደረገ።
የአዲስ አበባና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ለኤርትራው መሪ አቀባበል እንዲያደርጉላቸውም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ከቅዳሜ ሐምሌ 7/2008 ጀምሮ እስከ ሰኞ ሐምሌ 9/2010 ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ቆይታ እንደሚያደርጉም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል።

በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ መድረሱ ተነገረ።
በእስር ቤቱ የእንፈታ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ሲተኮስ እንደነበርና የቦምብ ፍንዳታም መሰማቱ ተነግሯል።
እስረኞቹን ለመጠየቅ የመጡ ሰዎች በፖሊስ እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል።
በቂሊንጦ እስር ቤት እስረኞች የእንፈታ ጥያቄ አቅርበው ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል።
እስረኞቹ የኦነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት በሚል ታስረው ከነበሩት መካከል መሆናቸውም ታውቋል።
ድሃ በመሆናችንና ታዋቂ ባለመሆናችን ከእስር አለመፈታታችን አግባብ አይደለም ሲሉ ታራሚዎቹ ተቃውሞ አሰምተዋል።
የእስረኞቹን ተቃውሞ ተከትሎ በግቢው ውስጥ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱንና የእሳት ቃጠሎ መከሰቱ ተነግሯል።

አምባሳደሮች ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማና አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ 8 ባለስልጣናት በአምባሳደርነት ተሾሙ።
የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ስምንቱ ተሿሚዎች በየትኛው ሃገር እንደሚወከሉ ዝርዝሩ ባይገለጽም ሹመቱን ግን ዛሬ ማግኘታቸው ታውቋል።
የደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸውን በቅርቡ የለቀቁትና የግብርና ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፣አቶ አለማየሁ ተገኑ፣አቶ እሸቱ ደሴ፣አቶ አዛናው ታደሰ ከተሿሚዎቹ ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ።
አቶ ዮናስ ዮሴፍ፣አቶ ያለው አባተና አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ በተመሳሳይ ተሹመዋል። ሹመቱን ተከትሎ አሁን በተለያዩ ሃገራት በስራ ላይ ያሉ አምባሳደሮች እንደሚጠሩ ይጠበቃል።

የጎዛምን ሆቴል ባለቤት ለሕዝብና ለሃገር እጨነቃለሁ አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በደብረማርቆስ አቶ በረከት ስምኦን ታይተዋል በሚል ጉዳት የደረሰበት የጎዛምን ሆቴል ባለቤት ከንብረታቸው ይልቅ ለሕዝብና ለሃገር እንደሚጨነቁ ገለጹ።
Image may contain: 1 personየሆቴሉ ባለቤት ዶክተር ምንውየለት ሞሴ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ሆቴሉን በትውልድ አካባቢውያቸው የገነቡት ሕዝቡ እንዲጠቀምና ሀገርን ለማሳደግ ነው።
ከ40 አመታት በላይ በውጭ ሀገር የኖሩትና በተለያዩ የስራ ሃላፊነት ላይ የቆዩት ዶክተር ምንውየለት ሞሴ ሕዝቡ በኢትዮጵያ ፍትህ እስኪሰፍንና እኩልነት እስኪረጋገጥ ድረስ ትግሉን መቀጠል አለበት ብለዋል

Wednesday, July 11, 2018

ሲኖዶስን ወክለው ሶስት ጳጳሳት ወደ አሜሪካ ሊጓዙ ነው

Image may contain: sky, tree, house, cloud, plant and outdoor(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በሽምግልና ለመፍታት ሶስት ጳጳሳት የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ ወክለው ወደ አሜሪካ እንደሚጓዙ ተገለጸ።
ፓትሪያሪክ ብጹዕ አቡነ ማትያስ አባቶቹ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ከሐገር በመውጣታቸው ላለፉት 26 ዓመታት የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ማዘናቸውንና ቤተክርስተያኒቱ በሰላም እጦት ውስጥ ማለፏን ገልጸዋል።
ከሐምሌ 11/2010 ጀምሮ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል በሚካሄደው የእርቅ ሒደት ላይ የሚሳተፉ ሶስት ሊቃና ጳጳሳት መወከላቸው

የአቶ በረከት ስምኦን ተሽከርካሪ በእሳት ጋየ

Image may contain: 1 person, outdoor(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) አቶ በረከት ስምኦን በደብረማርቆስ ታዩ በመባሉ በተካሄደ ተቃውሞ ቪ ኤይት ተሽከርካሪያቸው መቃጠሉ ተነገረ።
በጎዛምን ሆቴል ታይተዋል የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን ሹፌር መታወቂያም ተገኝቷል።
በደብረማርቆስ ሕዝቡ አቶ በረከትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያደረገው ተቃውሞን ተከትሎ በአካባቢው የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉም ታውቋል።
አቶ በረከት ስምኦን ከአምባገነኑ መሪ መለስ ዜናዊ ጋር የኢትዮጵያን መንግስት በተንኮልና በአሻጥር በመምራት የሕወሃት ተላላኪ ሆነው ላለፉት 27 አመታት ሲዘወሩ እንደነበር ይነገራል።
አሁን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ከሚቃወሙት የኢሕአዴግ ባላስልጣናት መካከል አንዱ መሆናቸውም ነው የሚታወቀው።

በሶማሌ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተፈጸሙት በህወሃት መሪዎች አስገዳጅነት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) በሶማሌ ክልል ሲፈጸሙ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎች በህወሃት መሪዎች ተገደን የፈጸምነው ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
ፕሬዝዳንቱ አብዲ ዒሌ ይህን የተናገሩት ዛሬ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው።
አብዲ ኢሌ የቀድሞ የደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋን በስም በመጥቀስ እያስገደዱን ወንጀል እንድንፈጽም ያደረጉን ናቸው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድንና አቶ ለማ መገርሳን በማወደስ ለኢትዮጵያ መልካም ነገር የሚያደርጉ ናቸው በማለት የገለጹት አብዲ ዒሌ የይቅርታ ጊዜ በመሆኑ ያለፈውን እንርሳ ሲሉ ተማጽነዋል።
በሶማሌ ክልል በተፈጸሙ ወንጀሎች ከእሳቸው ጋር የሚነሱትን የህወሃት ጄነራሎችን አለመጥቀሳቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
አብዲ ዒሌ በዛሬው የምክር ቤት ስብሰባው አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ጠንከር ያሉ ውንጀላዎችን አሰምተዋል።

ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደረገው በረራ በቀጣዩ ሳምንት ይጀመራል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደርገውን በረራ በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ እንዲሁም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞች ያለ ቪዛ በፓስፖርት ብቻ መጓዝ እንደሚችሉም ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻንም ወደ 114 ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።
ወደ አስመራ የሚደረገው በረራም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማክሰኞ ሐምሌ 10/2010 በቦይንግ 787 አውሮፕላን እንደሚጀምርም ተመልክቷል።
አንድ ሰአት ከ10 ደቂቃ በሚፈጀው በረራ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መንገደኞች ፓስፖርት እንጂ ቪዛ እንደማይጠየቁም ተገልጿል።
ቪዛው መዳረሻቸው ወደ ሆነው አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ እንደሚመታላቸውም ተመልክቷል።

የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት በሌሉበት መሻራቸውን ተቃወሙ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱላሂድ እርሳቸው ባልተገኙበት ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓም የተደረገው የማእከላዊ ስብሰባ እና የፕሬዚዳንት ምርጫ እንደማይቀበሉትና አሁንም ክልሉን እሳቸው እንደሚመሩት አስታውቀዋል። ምክር ቤቱ አቶ ኦድሪን በድሪን ሊቀመንበር ፣ አቶ ነቢል ማሃዲን ደግሞ ምክትል ሊ/መንበር አድርጎ መርጦ ነበር። አቶ ሙራድ ከአዲስ አበባ ከተመለሱ በሁዋላ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶችና ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች ሰብስበው ክልሉን አሁንም እርሳቸው እያስተዳደሩት መሆኑንና ስልጣን አለመልቀቃቸውን ተናግረዋል። የአቶ ሙራድን ድርጊት የሰሙት አዲሱ ፕሬዚዳንትና ምክትሉ፣ አቶ ሙራድ ቅስቀሳቸውን እንዲያቆሙ ያስጠነቀቁዋቸው ሲሆን፣ ዛቸውን የፈሩት አቶ ሙራድ ዛሬ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል። በክልሉ ባለስልጣናት መካከል ያለው መከፋፈል መጨመሩን ተከትሎ አካባቢውን የብጥብጥ ቀጠና ያደርገዋል የሚል ስጋት መኖሩን ወኪላችን ዘግቧል።

511 የሚሆኑ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች እስካሁን መፍትሄ አላገኙም ፡፡

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) ተፈናቃዮቹ የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ስብሰባን ምክንያት በማድረግ ወደ ስብሰባ ቦታው በመሄድ ችግራቸው እንዲታይላቸው የጠየቁ ሲሆን፣ የክልሉ አመራሮች ለአጭር ጊዜ አግኝተው አነጋግረዋቸዋል። ባለስልጣናቱ እስከ መጪው ቅዳሜ ስብሰባ ላይ መሆናቸውንና እሁድ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተፈናቃዮችን እንደሚያናግሩዋቸው ገልጸውላቸው ተፈናቃዮቹን አሰናብተዋቸዋል።

በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ በሚል ስም የጦርነት አዋጅ እያወጀ ያለው አካል ፣ እያደረገ ያለው ነገር እንዲያስብበት እና ወደትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ ኦቦ ለማ መገርሳ አስጠነቀቁ።

Image may contain: 1 person, sunglasses, eyeglasses and suit( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦቦ ለማ መገርሳ የጦርነት አዋጅ ያወጀውን ቡድን ያስጠነቀቁት፣ ትናንት በኦሮሚያ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ነው። “ከዚህ በፊት ቀጥታ ሲዋጉን የነበሩ አካላት ዛሬ ስፓንሰር በመሆንና ገንዘባቸውን በመርጨት የክልሉት ፀጥታ ለማደፍረስ እንቅልፍ አጥተው እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት አቅቶ ለማ፣ ከስፓንሰሮቹ የሚለገሳቸውን ገንዘብ በመቀበል የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈፀም ዝግጁ የሆኑ በርካታ የእኛው ወንድሞችም በመከላችን ይገኛሉ” ብለዋል፡፡ “ለዚህ ህዝብ ሁላችንም እንሥራለት በሚል ውሳኔ ሁሉም ወደ ሀገር ተመልሶ በሀሳብ በመፋለም አንድ ላይ መስራት አለብን ብለን ጥሪ ከማድረግም በላይ ፣ ህዝባችንን አምነን ብዙዎቹን ከሰሩት ወንጀልም ነፃ እንዲሆኑ አደረግን “ ያሉት ር ዕሰ መስተዳድሩ፣ የፓለቲካ ታርጋ ተለጥፎባቸው በሰው ሀገር የተበተኑ ወገኖቻችን ተመልሰው ለሀገር እንዲሰሩ በራፉን በከፈትንበት ፣ ብዙዎች ጥሪዎን ተቀብለው እየገቡ ባለበት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን እየፈታን ባለንበት እና አጠቃላይ የፓለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ ባለበት ጊዜ ፣”አይ! የኦሮሞ ነፃነትን ለማስከበር ትክክለኛ የጦርነት መክፈቻው ጊዜ አሁን ነው” ተብሎ በኦሮሞ ህዝብ ስም የሚደረግ እንቅስቃሴ ትርጉሙ ምን እንደሆነ በግሌ አልገባኝ”ብለዋል። አቶ ለማ አክለውም፦”ለኦሮሞ ነፃነት ለማስከበር የሚያስቡ ከሆነ ፣እስከዛሬ ይሄን ሁሉ ዘመን የት ነበሩ?…ሲሉ ጠይቀዋል። . “ እነዚህ ወገኖች ከልጅ ፊት አባት ገድለው ሬሳውን አቃጥለዋል።ሬሳ በማቃጠል የህዝብ ነፃነት እንዴት መከበር እንደሚችል አላውቅም። ኦሮሞ-ኦሮሞን ነው እየገደለው ያለው።…በምዕራብ ኦሮሚያ እየሆነ ያለው ነገር ይሄ ነው፡፡” ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አክለዋል። “ቄሮ ለዓመታት በመሪነት ባደረገው ትግልና በከፈለው መስዋዕትነት አሁን እያየነው ያለነው ለውጥ እንዲመጣ እና ዛሬ የመጣውን ውጤት እንድንጎናፀፍ አድርጎል.” ያሉት ኦቦ ለማ መገርሳ፣ “ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በቄሮ ስም ለመነገድ የሚሞክሩ ወጣቶች እዚህም እዛም የመዝረፍና አንዳንድ አካባቢዎችን የማወክ አዝማሚያ እያሳዩ እንደሆነ አልሸሸጉም። “ቄሮዎች ግን ይሄ በታሪክ ማህደር ላይ የተከተበ የጀግንነትና ለህዝብ መስዋዕትነት የከፈሉት ደማቸው ባክኖ እንዲቀርባቸው ስለማይፈልጉ፣ አሁንም እነዚህን ቅጥረኞች አደብ በማስገዛት እና ወደመስመር

የአቶ አብዲ አሌ ወኪሎች የለውጥ አራማጆችን ስብሰባ አደናቀፉ

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢትዮ-ሶማሊ ክልል መሪ የሆኑትን የአቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመርን አገዛዝ የሚቃወሙ፣ በክልላቸው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚታገሉ ከ300 ያላነሱ የአካባቢው ተወላጆች የአገር ሽማግሌዎሎች፣ ከውጭ አገር የመጡ ኢትዮጵያውያንና ምሁራን በሂደት ስለሚወስዷቸው እርምጃዎች የሚመክሩበት ስብሰባ አቶ አብዲ አሌ በላካቸው ሰዎች እንዲጨናገፍ ተደርጓል። ጠዋት ላይ በአዲስ አበባ ፍሬንድ ሺፕ ኢንተር ናሽናል ሆቴል አዳራሽ በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ ሆቴሉን አስቀድመው የተከራዩ ሰዎች ጩከት በማሰማት ስብሰባው እንዲበጠበጥ ያደረጉ ሲሆን፣ በስፍራው የደረሱ ፖሊሶችም ስብሰባው እንዲቋረጥ አድርገዋል። የመሰብሰብና ሃሳባቸውን በነጻ የመግለጽ መብታቸው መደፈሩን የሚደርስባቸውን ጥቃት በመፍራት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የስብሰባው አዘጋጆች ተናግረዋል፡፡ የኢትዮ-ሶማሊን ክልል ህዝብ እናድን የሚል አላማ ያነገበው ይህ ስብሰባ ፣ የፌደራል መንግስቱ በክልሉ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ይጠይቃል። የለውጥ ሃይሎቹ በቀጥታ ወደ ድሬዳዋና ጅግጅጋ ከተሞች በማምራት ህዝቡን አስተባብረው በክልሉ የለውጥ እንቅስቃሴ ለመጀመር እቅድ አላቸው። የሶማሊን ህዝብ እናድን መድረክ ምስረታ ሰነድ ላይ “የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርና ፓርቲው አመራሮች ከስልጣን እንዲወርዱና ስልጣን ለህዝብ ተመልሶ ህዝባዊ መንግስት እንዲቋቋም” የሚጠይቅ ጥሪ ቀርቧል። ሰሞኑን አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ወች በኦጋዴን እስር ቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ሰቆቃዎችን ማጋለጡን ተከትሎ የክልሉ ፕሬዚዳንት እስር ቤቱን ዘግተው መስጂድ እንደሚያደርጉት ተናግረዋል። በእስር ቤቱ ለአመታት የቆዩ ሰዎች እየተፈቱ ሌሎችም ወዳልታወቀ ቦታ እየተወሰዱ ነው።

Tuesday, July 10, 2018

የዋሽንግተን ዲሲው ኮሚቴ አወቃቀር ላይ ማስተካከያ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 3/2010) ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አሕመድን በዋሽንግተን ዲሲ ለመቀበል በተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት አወቃቀር ላይ ማስተካከያ መደረጉ ተገለጸ።
በኮሚቴው አወቃቀር ላይ ማስተካካያ የተደረገው በአሰራሩ ላይ ከአባላቱ እና ከልዩ ልዩ ወገኖች የተነሳውን ቅሬታ መሰረት በማድረግ መሆኑን አስተባባሪዎች ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ስራውን ከጀመረ አንድ ወር በሆነው የዋሽንግተን ዲሲ አስተባባሪ ኮሚቴ ውስጥ በፊት ያልነበሩና የጠቅላይ ሚንስትሩን የለውጥ እንቅስቃሴ የሚቃወሙ ሰዎች እንዲገቡ መደረጉ ቅሬታን ፈጥሮ ነበር።
የኮሚቴው ውክልናም ከዚህ ቀደም በአገዛዙ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ያደረጉ የነበሩ ታዋቂ አክቲቪስቶችን ባለማካካተቱ ተቃውሞ አስነስቷል።
ይሕ በመሆኑም በኮሚቴው አወቃቀር ላይ ማስተካካያ እንደተደረገና በዚህ ሂደት መሳተፍ ለሚፈልጉ ታዋቂ አክቲቪስቶችም መድረኩ ክፍት መሆኑንን በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ማስተወቁ ይታወሳል።

የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ኤርትራ ለመሄድ ጠየቀ

Image may contain: text(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 3/2010) የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ከአስመራ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ጠየቀ።
ለኤርትራ እግር ኳስ ፌደሬሽን በተላከ ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው የተጀመረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር በሁለቱ ከተሞች የእግር ኳስ ክለቦች መሀል በአስመራ የወዳጅነት ግጥሚያ ለማደረግ ተፈልጓል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ በከተማው ከንቲባ በአቶ ተቀባ ተባባል ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ጥያቄው መቅረቡ ታውቋል።

የህወሃት አባላት ያልሆኑ የጦር ጀነራሎች በአስከፊ ኑሮ ውስጥ ናቸው ተባለ

Image may contain: 2 people, people sitting and outdoor(ኢሳት ዲሲ--ሐምሌ 3/2010) በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ማንነትን መሰረት ባደረገ የማግለል ርምጃ የህዉሐት አባላት ያልሆኑ የጦር ጀነራሎች ከሰራዊቱ ያለጡረታ እየተገፉ በአስከፊ ኑሮ ውስጥ ማለፋቸውን አንድ የጦር ጄኔራል ለኢሳት ገለጹ።
በተለያዩ የሰራዊቱ የግምገማ መድረኮች የሕወሃት የበላይነትን በተመለከተ የሚነሱ አስተያየቶች ዋጋ ሲያስከፍሉ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል።
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በመረጃ ዋና መምሪያ የትንተና እና ፕሮዳክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ብርጋዴር ጀኔራል መላኩ ሽፈራው ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በመከላከያ ሰራዊቱ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፣ በሥርዓቱ ውስጥ ያለውን ችግርና የብሔር አድልዎ በዝርዝር ተመልክተዋል።
የህዉሐት ታጋዮች በነበሩ የጦር ጀነራሎች መካከል ባለው የርስ በርስ ግጭትም እነ ጀነራል ሰዓረ መኮንን፣ በጀነራል ሳሞራ አማካኝነት ከደረጃ ዝቅ እንዲሉ የተደረገበትንም ሁኔታ አስታውሰዋል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር አሜሪካ ለስብሰባ መጥተው ሥርዓቱን ከድተው አሜሪካ ከቀሩ በርካታ ወራትን ያስቆጠሩት ብ/ጀነራል መላኩ ሽፈራው፣ ከሶስት ዓመት በፊት MI-35 ሒሊኮፕተር ይዘው ኤርትራ የገቡትን ፓይለቶች በተመለከተ ምርመራ እንዲያደርግ የተመደበው ቡድን ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ አብራሪዎቹን ወደዚያ ውሳኔ ያደረሳቸውን የምርመራ ውጤትም በዚሁ ቃለምልልስ አንስተዋል።
ከቅማንት እና ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሱ ግጭቶች ውስጥ የሕዉሐትም የብአዴን ነባር አመራርን ተሳትፎ እንዲሁም የመከላከያ የጦር አዛዦችን ሚና በቃለ ምልልሱ አንስተዋል።

በአማራ ክልል ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬታ እየተሰማ ነው፡፡

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአማራ ክልል ከመሬት ልማት እና አስተዳደር ጋር በተያየዘ ከፍተኛ ቅሬታ እየታየ መሆኑን የክልሉ ቅሬታ ሰሚ አቶ ሰይድ ሁሴን አስታወቀዋል፡፡ አቶ ሰይድ በስድስት ወር ሪፖርታቸው አመቱን ሁሉ የቅሬታ ምንጭ ሁኖ ያለው መሬት ነው ብለዋል፡፡ አመቱን ሁሉ ከይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ፣ ካሳ አለመሰጠት እና ፍትሀዊ ያልሆነ አሰራር በዋናነት ህዝቡን ቅር ያሰኙ ጉዳዮች ሆነው ቀጥለዋል ብለዋል፡፡ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዚገም ወረዳ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በማህበር ተደራጅተን መሪ ማዘጋጃ ቤቱ መሥሪያ ቦታ ከፈቀደልን በኋላ ቤት ለመስራት ስንጀምር የወረዳው አካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር መሬት አይሰጥም ብሎ ያላግባብ አግዶናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡ በዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ከሰቆጣ ፃግብጅ በሚሰራው መንገድ ምክንያት የእርሻ ማሳቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ተመጣጣኝ ካሳ አልተከፈለንም የሚል ቅሬታ ያላቸው ሲሆን አሁንም ድረስ መፍትሄ እንዳላገኙ አመላክተዋል፡፡ በደሴ ከተማ አስተዳደር ፒያሳ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ቦታው ለመልሶ ማልማት ስለተፈለገ የምንኖርበት ቤትና ለንግድ የምንሰራበት ድርጅት በመፍረሱ ምክንያት ምትክ ቦታ ሳይሰጠን ከአካባቢው ልቀቁ ተባልን የሚሉ ቅሬታዎች እየቀረቡ ነው። በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እብናት ወረዳ የውስጥ ለውስጥ መንገድን

የሶማሌው ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣባቸውን መግለጫ እንዲያስተባብል ያስገደዱትን በቅርበ የተፈታ እስረኛ “በበቂ ሁኔታ አላስተባበለም”በማለት ዳግም እንዲታሰር አዘዙ።

( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) የእስርት ዕዛዝ የወጣበት ሙሀመድ አብዱላሂ ጉዴ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአካባቢው ተሰውሯል። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በአቶ አብዲ ኢሌና በሶማሌ ክልል የደህንነት ባለሥልጣናት ላይ በአስቸኳይ ምርመራ እንዲያደርጉ ማሣሰቡ ይታወቃል። ሂዩማን ራይትስ ዎች “የሞቱትን እንመስላለን” በሚል ርዕስ ባወጣወ በዚሁ ባለ 88 ገጽ መግለጫ፣ በአቶ አብዲ ኢሌ ትዕዛዝ አማካይነት በኦጋዴ እስር ቤቶች ሲፈጸሙ የቆዩትን ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የዓይን ምስክሮችን ዋቢ በማድረግ በዝርዝር አትቷል። በሰው ልጆች ላይ ለተፈጸሙት አሰቃቂ ወንጀሎችም አቶ አብዲ ኢሌን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የደህንነት ሠራተኞች ተጠያቂ መሆናቸውን ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታዉቋል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚፈጽሙ ባለሥልጣናትን በዝምታ የማለፍን ባህል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በመስበር ወንጀለኞቹን ለህግ እንዲያቀርቡም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ በአጽንዖት አሣስቧል። ይህን የሰብዓዊ መብት ተቋሙን ሪፖርት ተከትሎ ከፍ ያለ መረበሽ ውስጥ መግባታቸው የሚነገረው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አብዲ ኢሌ ፣ባለፉት ቀናት የቀረበባቸውን ክስ ለማስተባበል ሲሞክሩ ቆይተዋል። አብዲ ኢሌ በዚህ ሳያቆሙ ባለፉት ዓመታት በኦጋዴን እስር ቤቶች ከፍ ያለ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሢፈጸምባቸው የቆዩትንና በቅርቡ ከእስር የተፈቱትን እስረኞች መግለጫውን እንዲያስተባብሉ ማስገደድ ጀምረዋል። በዚህ ዙሪያ በርዕሰ መስተዳድሩ አደጋ ከተጋረጠባቸው መካከል በብዙዎች ዘንድ