Friday, June 29, 2018

ለውጥን ወደኋላ የሚቀለብስ ማንኛውንም ነገር ለመሸከም ዝግጁ አይደለንም ተባለ

Image may contain: 1 person, sitting(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጀመርነውን ለውጥ ወደኋላ የሚቀለብስ ማንኛውንም ነገር ለመሸከም ዝግጁ አይደለንም ሲሉ ገለጹ።
90 በመቶ የሚሆኑት የኢሕአዴግ አባላት የለውጥ ጉዞውን ደግፈው መቆማቸውንም አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ወደነበረው የጭንቀት ጊዜ እንዳትመለስ መከፈል የሚገባው ዋጋ ሁሉ እንደሚከፈልም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ይህንን የተናገሩት አፋር ክልል ሰመራ ላይ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
90 በመቶ የኢሕአዴግ አባላት በለውጡ ውስጥ ተሳታፊ ሆነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መጥራት የሚገባውን እያጠራን እንሄዳለን።
የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ለመቀልበስ የሚደረገውን ማንኛውንም ነገር ለመሸከም ግን ዝግጁ አይደለንም ብለዋል።

በኦሮሚያ 4 የፖሊስ አባላት ቆሰሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ያልታወቁ ሃይሎች 4 የፖሊስ አባላትን አቁስለው መሰወራቸው ተሰማ።
የገዳዮቹን ማንነት ለማወቅና ለፍርድ ለማቅረብ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን የኦሮሚያ መንግስት አስታውቋል።
የኦሮሚያ የገጠርና የፖለቲካ አደረጃጀት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በአካባቢው ያለው ሕዝብ እራሱን ከአጥቂዎች እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
በኦሮሚያ ክልል የነበረው ግጭት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋብ ቢልም በአንዳንድ አካባቢዎች ግን መጠነኛ ግጭት ይታያል።
ግጭቱ ተባብሶ ይታይባቸው የነበሩት የምዕራብ ጉጂና ጌዶ አካባቢ የሶማሌና አዋሳኝ አካባቢዎች ባሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንዲሁም በሞያሌ የነበረው ግጭት ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተሸጋግሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በኦሮሚያ ያለው ግጭት ጋብ ቢልም በደቡብ ክልል በቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳና ሌሎች አካባቢዎች ግን ብሔር ተኮር ግጭቶች ነበሩ።
ሰሞኑን በተሰማው ዜናም በአሶሳ 10 ሰዎች ተገድለው ከ38 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

ኦብነግ የጦር አዛዥ ከወህኒ ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/የጦር ኮማንደር ትላንት ከወህኒ ተለቀቁ።
የኦብነግ የጦር አዛዥ የነበሩት አብዱከሪም ሼክ ሙሳ አምና በነሐሴ ወር በሶማሊያ ጋልካዩ ታፍነው ወደ ሞቃዲሾ ከተወሰዱ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው መሰጠታቸው ይታወሳል።
አምና በነሐሴ 2009 ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር የጦር አዛዥ ኮማንደር አብዱከሪም ሙሳ ላለፉት 11 ወራት በኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ቆይተዋል።

Thursday, June 28, 2018

Leaders of Ethiopia, Eritrea to meet “soon”

by Engidu Woldie
ESAT News (June 28, 2018)
Leaders of Ethiopia and Eritrea would meet soon to further talks between the two sides to resolve borders issues and begin normalization. The announcement by the Ethiopian Minister of Foreign Affairs came at the end of a first leg visits by an Eritrean delegation to Ethiopia.Workneh Gebeyehu, Ethiopia’s Foreign Minister told reporters in Addis Ababa today that discussions with visiting Eritrean delegation has opened more doors of opportunities for further talks between the two sides.

በኢትዮጵያ የተጀመሩ ለውጦችን ለማደናቀፍ የሴራ ፖለቲካ እየተካሄደ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ የቴሌኮም ኔትዎርክን ከመጥፋት ጀምሮ የተደራጁ ሥራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ። 
ይህንን የማደናቀፍ ሴራ የሚመረምሩ ኮሚቴዎች መዋቀራቸውም ተመልክቷል።
አጥፊዎቹን ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ሂደት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ጠይቋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ሰኔ 16/2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ ቦምብ ከመወርወር ጀምሮ ሂደቱ እንዲስተጓጎል በወቅቱ የመብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ የማጥፋት ሥራ ተከናውኗል።
ከዚህም በተጨማሪ የኢኮኖሚ አሻጥርም በተደራጀ አኳኋን በመስራት የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እና የተለያዩ ህዝባዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስፈላጊውን አገልግሎት እንዳይሰጡ እየተደረገ መሆኑንም መንግስት ይፋ አድርጓል ።

የአሶሳው ግጭት በገንዘብ በተገዙ ግለሰቦች የተፈጸመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010)በአሶሳ ከተማ ከማክሰኞ ጀምሮ የተፈጠረው ግጭት በገንዘብ በተገዙ ግለሰቦች የተፈጸመ መሆኑን የክልሉ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
ገንዘቡን የከፈሏቸውና ለዚህ ድርጊት ያሰማሯቸው እነማን ናቸው የሚለው በምርመራ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።
በግጭቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 9 የደረሰ ሲሆን በግጭቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥርም 49 መድረሱ ይፋ ሆኗል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በአማራ ክልል በባቲና በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
በባቲም ግጭቱን የቀሰቁት ሰዎች በአካባቢው የማይታወቁ መሆናቸውን ሰለባዎቹ ተናግረዋል።
ከክልሉ መንግስት አቅም በላይ የሆነውና በአሶሳ ከተማ የተፈጠረው ግጭት በመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብነት ከትላንት ጀምሮ ጋብ ማለቱ ታውቋል።

በአማራ ክልል በግጭት ለሞቱና ለቆሰሉ ወገኖች ካሳ ሊከፈል ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010) በአማራ ክልል ላለፉት አመታት በተካሄደው ግጭት ለሞቱና ለቆሰሉ ወገኖች የክልሉ መንግስት ካሳ ለመክፈል መወሰኑን አስታወቀ።
የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስት ለሰለባዎቹ አጋርነቱን ለመግለጽ ያህል የካሳ ክፍያ እንደሚፈጽም አረጋግጠዋል።
በዚህም መሰረት ሰለባ ለሆኑ ወገኖች ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 75 ሺ ብር እንደሚከፈል ተገልጿል።
አካላቸው ጎሎ መስራት ለማይችሉ ወገኖች ደግሞ 50 ሺ ብር ካሳ እንደሚከፈል ተገልጿል። ለሌሎች ቁስለኞች 25 ሺ ብር እንደሚከፈልም ተመልክቷል።
በአማራ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ ጥያቄ ተከትሎ የመንግስት ሃይሎች በወሰዱት ርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ከስልጣናቸው ሊነሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010)የደቡብ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ከስልጣናቸው እንደሚነሱ ተገለጸ።
ሰሞኑን የድርጅቱ አመራር ሆነው የተመረጡት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምትካቸው እንደሚመረጡም ተመልክቷል።
የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱና በሌላ የደኢሕዴን አባል እንደሚተኩ የዘገበው በሀገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ተክተው ከሐምሌ 6/2005 ጀምሮ ላለፉት 5 አመታት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ደሴ ዳልኬ በአቶ ማቲዎስ እንደሚተኩ ተመልክተዋል።

የቦምብ ፍንዳታው የሚመረመረው በስድስት ቡድን በተከፈሉ ባለሙያዎች ነው

(ኢሳት ዲሲ--ሰኔ 21/2010) በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 16/2010 በመስቀል አደባባይ የተከሰተውን የቦምብ ፍንዳታ ለመመርመር ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ባለሙያዎች በስድስት ቡድን የተከፈሉ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ከቦምብ ጥቃቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ከታሰሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር በተጨማሪ ስድስት ኮማንደሮችም በተመሳሳይ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የዋስትና መብት የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዶ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ አዟል።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የለውጥ ጉዞ በመደገፍና ለቅልበሳ የሚንቀሳቀሱትን በማውገዝ በተካሄደው ትዕይንተ ሕዝብ ላይ ሰኔ 16 በፈነዳው ቦምብ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ከ150 በላይ ደግሞ ቆስለዋል።
የጥቃት ሙከራውን ተከትሎ ቁጥራቸው 30 ያህል ሰዎች ወዲያውኑ መታሰራቸው የተገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳም መታሰራቸው የተገለጸው እለቱኑ ነበር።

በተደራጀ ሁኔታ ሽብር የሚፈጽሙ፣ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ የሚያጠፉ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ኃይሎች መኖራቸውን መንግስት አስታወቀ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጀመሩትን አገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል በተደራጀ ሁኔታ የሚሰሩ ኃይሎች መኖራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። እነዚህ ቡድኖች በአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ ከተፈጸመው የቦንብ ጥቃት በተጨማሪ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ ማጥፋት፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በተደራጀ አኳኋን በመስራት የኑሮ ውድነት በአገሪቱ እንዲባባስ እና የተለያዩ ህዝባዊ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ የተቋቋሙ ተቋማት አስፈላጊውን አገልግሎት እንዳይሰጡ እያደረጉ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ መቻሉንም ጽ/ቤቱ አመልክቷል፡፡ ይህን ሕገወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን አጣርተው ለሕግ የሚያቀርቡ ኮሚቴዎች መቋቋማቸውንና ውጤቱንም ለሕዝቡ በወቅቱ እንደሚገለጽ መግለጫው አትቷል። ሕዝቡ ከኮሚቴዎቹ ጎን በመቆም አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ሂደት ላይ ተባባሪ በመሆን የአገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ ዘብ እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል።

በኢትዮ-ሶማሊ ክልል ነዳጅ የማውጣት ስራ ቢጀመርም፣ የሶማሊ ክልል ተወላጆች ቅሬታ እንዳላቸው እየገለጹ ነው።

(ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጹት የአገራችንን ሃብት መጠቀም መጀመሩ ጥሩ ቢሆንም፣ በአካባቢው ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ትኩረት አለማግኘቱን፣ በበቂ ሁኔታ የአካባቢ ጥበቃ አለመደረጉ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ህዝቡ ውይይት እንዲያደርግበት አለመጋበዙ ቅር አሰኝቶናል ብለዋል። ከድፍድፍ ማውጫ ግንባታው ጋር በሽላቦ አካባቢ ከፍተኛ የግጦሽ መሬት ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ፣1 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ አደጋ ውስጥ እንደሚገባ በአካባቢው ጉዳይ ላይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት አቶ ጀማል ድሬ ካሊፍ ገልጸዋል። ከነዳጁ በፊት በሶማሊ ክልል የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ሊቆም ይገባ ነበር ያሉት አቶ ጀማል፣ ኢትዮጵያውያን የዚህን ህዝብ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሰሙለት ይገባል ብለዋል። ጸሃፊና አክቲቪስት ሙስጠፋ ኡመር በበኩሉ ነዳጅ መውጣቱና አገሪቱ ተጠቃሚ መሆኗ ችግር ባይኖረውም፣ አሁንም አብዲ ኢሌ በስልጣን ላይ እያለና ህዝቡ ስለጉዳዩ በደምብ ሳያውቅ ነዳጅ እንዴት ሊወጣ ይችላል? የሚለው ነገር፣ ብዙዎችን እያነጋገረ መሆኑን ገልጸዋል። ጠ/ሚኒስትር አብይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ብዙ ለውጦችን እያመጡ ባለበት ሁኔታ የሶማሌ ክልል በተበላሸ አስተዳደር ባለበት ሲረግጥ ለምን ዝም አሉት? የሚል ከፍተኛ ጥያቄ አለ ሲሉም አቶ ሙስጠፋ አክለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአፋር ክልል ከህዝቡ ጋር ተወያዩ። የተወሰኑ የአፋር ምሁራንና ወጣቶች ተነጥለው በውይይቱ እንዳይገኙ ከመደረጋቸውም ባሻገር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ታወቋል።

(ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ሕዝባዊ ውይይት አደርገዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን መምጣት ተከትሎ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የሆነው የአፋር ሕዝብ ዴሞክራሲያ ፓርቲ (አ.ብ.ዴ.ፓ.) የፓርቲውን አባላትና ደጋፊዎችን ከተለያዩ ከተሞች በማምጣት አስተዳደራዊ ቅሬታዎች እንዳይሰሙ አድርጓል። በክልሉ የተንሰራፋውን ሌብነት፣ የዘመድ አዝማድ አሰራር፣ ኋላቀርነትና የህወሃትን ጣልቃ ገብነት ያጋልጣሉ የተባሉ ግለሰቦች ላይም አካላዊ ጉዳቶች ተፈጽሞባቸዋል። ቁጥራቸው ከሰማኒያ በላይ የሚሆኑ ወጣቶችና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም ካለ ፍትሕ ታስረዋል። ወጣቶችን በመደገፍ የምትታወቀውና የከተማው ፖሊስ ሰራዊት አባል የሆነችው ሳዲያ አህመድ በድብደባ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አንድዋ መሆኗን የአፋር ሰብዓዊ መብት ታጋይ ወጣት አካድር ኢብራሂም ገልጸዋል። የአፋር ክልል፣በኢትዮጵያ ኋላቀር ክልል ተብለው ከማእከላዊ መንግስት ተጨማሪ በጀት ከሚመደብላቸው ክልሎች አንዱ ቢሆንም፣ የክልሉ ነዋሪዎች አሁንም የልማቱ ተጠቃሚዎች መሆን አልቻሉም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ለተገኙት ተሰብሳቢዎች ባሰሙት ንግግር “የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ የሚፈጠሩ ዘርፈ-ብዙ ችግሮችን ለመፍታት በአንድነት ከጎናችን ሆናችሁ ጥንካሬ እንደምትጨሩረልን አንጠራጠርም። ምክንያቱም አንድም ቀን ለኢትዮጵያ ፍቅርን ለባንዲራ ፍቅርን አሳንሳችሁ አታውቁምና!” በማለት የአፋር ህዝብ ለኢትዮጵያዊነት ምስረታ ላበረከቱት አስተዋጾ አመስግነዋል። ወደፊትም የተለመደው አጋርነታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Wednesday, June 27, 2018

በአሶሳ ከተማና አካባቢው ግጭት ተቀሰቀሰ

Image may contain: one or more people and shoesኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማና አካባቢው ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ።
የግጭቱ መንስኤ በውል ባይታወቅም ችግሩ ከማንነት ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል። በግጭቱ ሰባት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊጨምር ይችላል ብለዋል የኢሳት ምንጮች ከስፍራው።
በክልሉ ማኦ ኮሞ ወረዳ በቶንጎ ከተማም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ ፖሊስ በከፈተው ተኩስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳ ከተማ ከፍተኛ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በከተማዋ እንደገና ጸጥታ መስፈኑ ይነገራል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ስለተነገራቸው አካባቢው ጸጥ ረጭ ማለቱም ነው የተነገረው።
በከተማዋ የበርታ ተወላጆች በሌሎች ብሔሮች ላይ ተቃውሞ በማሰማት በተወሰኑት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
እስካሁን ከሆስፒታል የተገኙት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት 7 ሰዎች ተገድለዋል።

ኢ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ስርጭቱን ሊያቋርጥ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010) ኢ ኤን ኤን የተባለው ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ ስርጭቱን ሊያቋርጥ መሆኑ ተሰማ።
በመጪው አርብ 110 የሚሆኑ ቋሚ ሰራተኞቹን በይፋ ሊያሰናብት መዘጋጀቱም ታውቋል። ጣቢያው በሕወሃቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ቦርድ ሰብሳቢነት ሲመራ መቆየቱ ይታወሳል።
የኢ ኤን ኤን ከስርጭት መውጣት ምክንያት የመንግስት መስሪያቤቶች መረጃ ለጣቢያው መስጠት በማቆማቸው መሆኑ ይነገራል።
ለጣቢያው ስፖንሰር የሆኑት ኢትዮ ቴሌኮም እና ንግድ ባንክ በድንገት ውላቸውን ማቋረጣቸው የጣቢያውን ገቢ ማሳጣቱንም የኢ ኤን ኤን ምንጮቻችን ለዋዜማ ጠቁመዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል ተባለ

Bildergebnis für dr.abiy ahmed(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010) በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት በመደገፍ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ሰልፎች መቀጠላቸው ታወቀ።
ዛሬ በሆሳዕና በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ህወሃት ከደኢህዴን ላይ እጁን እንዲያነሳ ተጠይቋል።
ነገ በወልቂጤ ከተማ ተመሳሳይ ዓላማ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ነዋሪው ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በባህርዳርም ለፊታችን እሁድ የድጋፍ ሰልፍ የተጠራ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜናም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት እየታየ ያለውን የለውጥ ሂደት በመደገፍ ሰልፍ ሊያደርጉ መዘጋጀታቸው ታውቋል።
ዛሬ የሀዲያ ዋና ከተማ ሆሳዕና የድጋፍ ሰልፍ ማድረጓ ተሰምቷል። በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለመደገፍና ከቀልባሾች ለመታደግ በሚል የተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሀት የተወገዘበት መሆኑን ነው የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው።

አንድ አማራ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጥሪ ተቀብያለሁ አለ

No automatic alt text available.(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010)የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በውጭና በሃገር ውስጥ ለሚገኙ በአማራ ስም ለሚንቀሳቀሱ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበለው አንድ አማራ የተሰኘው ድርጅት አስታወቀ።
በቅርቡ የተመሰረተውና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው አንድ አማራ ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ያቀረቡትን የአብረን እንስራ ጥሪ በቅን ልቦና መቀበሉን አስታውቋል።
ምንም እንኳን የአካሄድ ልዩነቶች ቢኖሩንም ስለሕዝባችን ህልውና አንድ አማራ ከብአዴን ጋር በጋራ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ያረጋግጣል ይላል አንድ አማራ ለኢሳት በላከው መግለጫው።

የጎንደር ሕዝብ የወልቃይትን ጉዳይ የማንሳት መብት የለውም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 19/2010) የጎንደር ሕዝብ የወልቃይት ጉዳይን የማንሳት መብት እንደሌለው የሕወሃቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል ገለጹ።
የወልቃይት ነዋሪዎች ጎንደሮችን የሚያስታግስልን መንግስት አጣን እያሉን ነው ሲሉ ዶክተር ደብረጺዮን አማረዋል።
ድንበራችን ተከዜ ነው የሚሉት ጎንደሮች ሀሳባቸው ኋላቀር ቢሆንም ሕገመንግስቱ ግን ሌላ ነው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ስለወልቃይት የጻፉት ደብዳቤም የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴን በእጅጉ አስቆጥቷል።
የወልቃይት ጉዳይን በተመለከተ በውክልና ወይንም በደብዳቤ የሚጠየቅ ሳይሆን በሕገመንግስት የተቀመጠና ጉዳዩ የተቋጨ መሆኑን የህወሃቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ተናግረዋል።

ብአዴን የሕወሃት ወኪሎችን የማጥራት ስራ እሰራለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010)የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ በመጪው ሃምሌ በሚካሄደው የድርጅቱ ጉባኤ በማዕከላዊ ኮሚቴና በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ የሚገኙ የሕወሃት ወኪሎችን የማጥራት ስራ እንደሚሰራ ምንጮች ገለጹ።
አቶ በረከት ስምኦንን ጨምሮ በለውጥ ሒደቱ እንቅፋት ሆነው የቆሙትን ብአዴኖች ሙሉ በሙሉ ከድርጅት አመራርነት ለመጥረግ መዘጋጀቱም ተመልክቷል።
እንደ ኢሳት ምንጮች ገለጽእ ብአዴን በአሁኑ ወቅት ካሉት 65 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የለውጡ እንቅፋትና የሕወሃት ድጋፊ ተብለው የሚታወቁት 14 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ናቸው።
አቋማቸው የማይታወቅና የሃይል ሚዛን አይተው የሚንሸራተቱት ደግሞ ዘጠኝ ብቻ እንደሆኑም ተመልክቷል።
እነዚህ በጠቅላላ በአንድነት ቢቆሙ እንኳን ብአዴንን ከለውጡ ጉዞ መግታት የሚያስችል ድምጽ አይኖራቸውም ተብሏል።

Tuesday, June 26, 2018

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠውን መልስ ተቃወመ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ኮሚቴው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓም የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት አስመላሽ ኮሚቴ ያቀረበው የማንነት ይከበርልኝ ጥያቄ ህግን ተከትሎ ያልተካሄደ ነው በማለት ውድቅ ማድረጉን በጽኑ ተቃውሞአል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በመግለጫው የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሒም ጥያቄያቸውን ውደቅ ያደረጉባቸውን ምክንያቶች አቅርቧል። ምክንያቶቹም ጥያቄው ፣ በክልሉ በሚገኙት የተለያዩ የመስተዳድር እርከኖች ቀርቦ አጥጋቢ መፍትሔ ያልተሰጠው ስለመሆኑ ከቀረበው ማመልከቻ ማረጋገጥ ባለመቻሉ ፣ የነዋሪው ሕዝብ ወይም የብሔር፣ብሔረሰቡ መሆኑን ለማመልከት ከነዋሪው መሐከል ቢያንስ አምስት ከመቶ(5%) ወይም ከብሔር ፣ብሔረሰቡ አባላት ቢያንስ አምስት ከመቶ ስም ዝርዝር ፊርማ እና አድራሻ የያዘ ባለመሆኑ፣ እንደአስፈላጊነቱ ጥያቄ ባቀረበው የመስተዳድር አካል ባለስልጣን የተፃፈ ፌርማ እና ማሕተም ያረፈበት ባለመሆኑ፣ እንዲሁም ለምክር ቤቱ ጥያቄ ለማቅረብ የሚመጣ ግለሰብ ወይም ግለሰቦች ከጠያቂው ብሔር፣ብሔረሰብ፣ሕዝብ የተወከሉ ለመሆናቸው በቂ ማረጋገጫ ያላቀረቡ የሚሉት ይገኙበታል። ኮሚቴው

በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት በስልጣን ላይ የነበሩ የህወሃት አባላት በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በርታና ጉምዞች በአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደርገው 3 ሰዎች መሞታቸውንና ከ20 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የህወሃት ሰዎች በአካባቢው እንደነበሩ እና ባምባሲና እና አሶሳ ዙሪያ እየዞሩ የበርታ ልጆቹን ሲቀሰቅሱ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ ትናንት እንዲፈጸም የተደረገው ዛሬ ለዶ/ር አብይ የተጠራውን የድጋፍ ሰልፍ ለማደናቀፍ እንደበር እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የተወሰነ ጉዳት እንደደረሰበት፣ የተወሰኑ ባጃጅ መኪናዎች እንደተሰባበሩና እስከ 3 ሰኣት ድረስ ወደ አዲስ አበባና ሌሎችም አካባቢዎች የሚካሄደው የትራንስፖርት ፍሰት ተቋርጦ እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። አሁንም በአካባቢው ውጥረት እንዳለ ታውቋል።

የኤርትራ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኤርትራ የመጣውን ልኡካን ቡድን በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የማነ ገብረዓብ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌህና በአፍሪካ ህብረት የአገሪቱ አምባሳደር የሆኑት አርዓያ ደስታ ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ይገኙበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኤርትራ የመጣውን ልኡካን ቡድን በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል፡፡ ኤርትራ ጠ/ሚኒስትር አብይ አቅርበውት ለነበረው የሰላም ጥሪ አወንታዊ ምላሽ በሰጠች በአጭር ጊዜ ውስጥ ዲፕሎማቶቿን መላኳ በሁለቱ አገራት መካከል የቆየውን ችግር ለመፍታት ቁርጠኝነት ማሳየቱዋን ታዛቢዎች ይናገራሉ። የልኡካን ቡድኑ ጠ/ሚኒስትር አብይ ኤርትራን እንዲጎበኙ ግብዣ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲሉ እነዚህ ወገኖች አክለው ገልጸዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የቆየው ችግር ከተፈታ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እንደሚቻል ይታመናል።

Monday, June 25, 2018

ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ።
የደኢሕዴን ሊቀመንበር ከሆኑ ሶስት ወር ያልሞላቸው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የለቀቁበት ምክንያት ግን አልታወቀም።
በቅርቡ በሃዋሳ በተፈጠረው ግጭት የሲዳማ ዞን እና የወረዳ አመራሮች በፈቃዳቸው ስልጣን እንዲለቁ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 226 ሰዎች መታሰራችውም ታውቋል።
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት ከዶክተር አብይ አህመድ ጋር መወዳደራቸውም ይታወሳል ።
አቶ ሽፈራው በአሁኑ ወቅት የግብርና ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ሲሆን፣ይህንን ስልጣናቸውን ስለመልቀቃቸው የታወቀ ነገር የለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ሙፍሪያት ከማል የደኢሕዴን ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ታውቋል።

በሃዋሳ ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) በሃዋሳ ከተማ በተነሳው ግጭት ለ10 ሰላማዊ ሰዎች ሞትና ለ80 ሰዎች መቁሰል ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በግጭቱ 3ሺ 500 ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ሆስፒታል አልጋ ላይ የነበሩ ሰዎች ጭምር በጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውም ታውቋል።
የሲዳማ ዞን አስተዳደር አቶ አክሊሉ አዱላ አዲስ አበባ ለሚታተመው ሪፖርተር የእንግሊዝኛ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ በግጭቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 226 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
ግጭቱ የሲዳማንም ሆነ የወላይታን ሕዝብ የማይመለከት እንደሆነም አስተዳዳሪው ጨምረው ገልጸዋል።

ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርመራ ላይ እገዛ ያደርጋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) በአዲስ አበባ ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ የፈነዳውን ቦምብ በተመለከተ የአሜሪካው የምርመራ ተቋም /ኤፍ ቢ አይ/ በምርመራው እገዛ እንደሚያደርግ ተገለጸ።
የአሜሪካው የፌደራል የምርመራ ቢሮ ከሚያደርገው እገዛ በተጨማሪ ሃገራቸው ያልተገለጸ የውጭ ሃገር የምርመራ ባለሙያዎች ሒደቱን ለማፋጠን ኢትዮጵያ መግባታቸውን መንግስት አስታውቋል።
የቅዳሜውን የቦምብ ጥቃት ተከትሎ የተቀነባበረ ጥቃት መፈጸሙን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “ኢትዮጵያ ከጀመረችው የፍቅርና የይቅርታ መንገድ ሊገታት የሚችል ሃይል የለም”በማለት ርምጃው የለውጥ ጉዞውን እንደማይገታ አረጋግጠዋል።
ምርመራው እንደተጠናቀቀም ጉዳዩ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል። በዚሁም መሰረት የምርመራውን ስራ የሚያካሂዱ የውጭ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ መግባታቸው ተዘግቧል።
የአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮም በምርመራው ሒደት እገዛ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

በውጭ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እደግፋቸዋለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010)በውጭ ሃገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እንደሚደግፍና ከጎናቸው እንደሚቆም ይፋ አደረገ።
እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ማህበርም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጎን በመቆም አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 ባወጣው መግለጫ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጎን እንደሚሰለፍ ከማረጋገጥ ባሻገር በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን የቦምብ ጥቃት አውግዟል።
“በሃገራችን ሕዝብ ዘንድ እየታየ ያለው ፍቅርና አንድነት የማያስደስታቸውና እኩይ ተግባር የተጠናወታቸው ክፉዎች የዚህን ታላቅ ሕዝብና ታላቅ መሪ አላማ እንዲሁም የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማደናቀፍ በመስቀል አደባባይ ያደረሱትን የቦምብ ጥቃት ቅዱስ ሲኖዶሱ ያወግዛል”ያለው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ሁሉም የእምነት መሪዎች ድርጊቱን እንዲያወግዙም ጥሪ አቅርቧል።
ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ለተጎዱት ምህረትን የተመኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ በእለቱ የነበረው ደስታ በሃገራችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ነበር ሲል ገልጿል።

በውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ላይ የተጠራው ዘመቻ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋረጠ

No automatic alt text available.(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) በውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ላይ የተጠራውን ዘመቻ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን ዓለም ዓቀፍ የኢትዮጵያውያን ግብረ ሃይል አስታወቀ።
ግብረሃይሉ ለኢሳት በላከው መግለጫ እንደገለጸው በአሁኑ ወቅት የህወሃት አገዛዝ ተጽዕኖ እየተዳከመና የፖለቲካ አመራሩ በለውጥ ፈላጊዎች እጅ የወደቀበት ሁኔታን ከግምት በማስገባት የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦው ዘመቻ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በለውጥ ቀልባሾች ሊደርስባቸው የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ታሳቢ መደረጉን የገለጸው ዓለም አቀፍ ግብረሃይሉ ለስድስት ወራት የዘለቀው ዘመቻ በጊዜያዊነት መነሳቱ አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኘው አስታውቋል።
አለም አቀፉ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረ ሀይል ላለፉት ስድስት ወራት የሬሚታንስ ተአቅቦ ዘመቻ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

Thursday, June 21, 2018

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ገተርስ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመካከላቸው የነበረውን ውዝግብ ለመፍታት እና ወደ ሰላም ለመምጣት መስማማታቸውን አደነቁ።

(ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም)ዋና ጸሀፊው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በመካከላቸውና በአጎራባች ሀገራት ጭምር ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ስምምነት ለማምጣት እያደረጉ ያለውን ጥረትም አወድሰዋል።. ከዋና ጸሀፊው ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንደሚለው፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሱ፣ በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሰላም ለማስፈን አስተዋዖው ከፍ ያለ ነው። ሀገራቱ ሰላም ለመፍጠር በሚከተሏቸው ሂደቶች ተመድ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ሁሉ ላማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አንቶኒዮ ገተርስ አስታውቀዋል።.

ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የጌዲዮ ተወላጆች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ከምዕራብና ከምስራቅ ጉጂ ዞኖች የተፈናቀሉ ከ500,000 በላይ የሚሆኑ የጌዲዮ ተወላጆች በቂ የምግብ እርዳታ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው ይገኛሉ። ሰሞኑን በይርጋጨፌ ወረዳ አንድ የ65 ዓመት አባት በረሃብ ሕይወታቸዉ ማለፉን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። በመንግሥት በኩል የተሰጡት እርዳታዎች በቂ አለመሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የደቡብ ክልል ባለስልጣናት በአካባቢው ያለው ችግር እንደተቀረፈ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቢቆዩም፣ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ግን ችግሩ መኖሩን በማመን አፋጣኝ መልስ እንሰጣለን ብለዋል።

በነዳጅ እጥረት የሚሰቃዩ የወልድያ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም)አሸክርካሪዎቹ በየጊዜው በሚጨምረው የነዳጅ ዋጋ መማረራቸውን ሲገልጹ ከቆዩ በሁዋላ ዛሬ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ ቶታል ነዳጅ ማደያ፣ ኦይል ሊቢያ እና ኖክ የነዳጅ ማደያዎች መታሸጋቸው ታውቋል። አጋጣሚውን በመጠቀም በሰልፉ ላይ የተቀላቀሉ ወጣቶች፣ “በዶ/ር አብይ ሙስና የለም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል።

የምህረት አዋጁ በቅርቡ እንደሚጸድቅ ተነገረ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም) በሚቀጥለው ሳምንት ፓርላማው ያጸድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው የምህረት አዋጅ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ምህረት እንደሚደረግላቸው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ገልጸዋል። አዋጁ ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ቀድም ብሎ የተመራ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ እስካሁን መልስ አልሰጠበትም። ይሁን እንጅ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ አዋጁ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አርበኞች ግንቦት7 በዶ/ር አብይ አህመድ የቀረበውን የሰላም ጥሪ አወንታዊ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የንቅናቄው ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ በኢቲቪ ቀርበው ማብራሪያ ስጥተዋል። ዶ/ር ታደሰ ድርጅታቸው አርበኞች ግንቦት7፣ ከመጀመሪያውም ጀምሮ በአገር ውስጥ ገብቶ መታገል አላማው እንደነበርና አሁን በዶ/ር አብይ የተጀመሩት የለውጥ እንቅስቃሴዎች፣ ድርጅቱ ከሚታገልለት አላማ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ፣ ለተግባራዊነቱ አወንታዊ መልስ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። ዶ/ር ታደሰ ድርጅቱ ራስን የመከላከሉን እርምጃ ጥቃት እስካልተፈጸመበት ድረስ እንደሚያቆምም ገልጸዋል። ድርጅቱ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ አባል ዶ/ር ታደሰ ብሩ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንዲሰጡን አነጋግረናቸዋል፦

የአርበኞች ግንቦት 7 ልዩ መግለጫ “የሰለጠነ ፓለቲካ” የምንመርጠው፣ የምናውቀውና የምንመኘው የትግል ስልት ነው!!!

ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን የሥራ ዘገባ እና ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ በአንክሮ ተከታትለናል።
ዶ/ር አቢይ በዚሁ ማብራሪያቸው የኢህአዴግ መንግሥት የፀጥታና የደህንነት ኃይሎች የአሸባሪነት ተግባራትን የሚፈጽሙ እንደሆኑ በይፋ ከመናገራቸውም ባሻገር ፤ ፓርቲና መንግሥት ተቀላቅለው ነፃ ተቋማት እንዳይኖሩ መደረጉን እና የዳኝነት ሥርዓቱ ከፍተኛ ችግር ያለበት መሆኑን ገልጸዋል። ንቅናቄዓችን ለዓመታት ሲናገር የነበረውን ሀቅ እሳቸው መናገራቸው፣ በአንድ በኩል እሳቸው በግላቸው ከእውነት ጎን ለመቆም ያላቸውን ቁርጠኝነት ሲያመለክት -በሌላ በኩል ደግሞ እሳቸው የሚመሩት የለውጥ ቡድን ለሀገራዊ መግባባት እያሳየ ያለው ዝግጁነት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ያመለክታል የሚል እምነት አሳድሮብናል። እነዚህ ቀድሞ ሲካዱ የነበሩ እውነታዎች በእርሳቸው አንደበት በምክር ቤቱ ስብሰባ መገለፃቸው፣ እስካሁን ሲፈፀሙ የነበሩ በደሎችን ለማስቀረት እና ጉድለቶችን ለማረም ብርቱ ፍላጎት እንዳላቸው ያሳያል ብለን እናምናለን። ዶ/ር ዓቢይ እስካዛሬ በኢትዮጵያ የምክር ቤት ታሪክ ውስጥ ያልታየ ሀቀኝነት በማሳየታቸውም አድናቆቻችን ከፍተኛ ነው።

Wednesday, June 20, 2018

ዶክተር ዓቢይና የለውጥ ቡድናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም በሚያደርጉት ትግል አብረናቸው መሆናችንን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምላሽ ሰጠ።

(ኢሳት ዜና ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓ/ም) “የሰለጠነ ፓለቲካ” የምንመርጠው፣ የምናውቀውና የምንመኘው የትግል ስልት ነው” በሚል ርዕስ አርበኞች ግንቦት ሰባት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ ዶክተር አብይ አህመድ ለምክር ቤት ያቀረቡትን የሥራ ዘገባ እና ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ በአንክሮ እንደተከታተለው በመጥቀስ፣ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢህአዴግ መንግሥት የፀጥታና የደህንነት ኃይሎች የአሸባሪነት ተግባራትን የሚፈጽሙ እንደሆኑ በይፋ ከመናገራቸውም ባሻገር ፤ ፓርቲና መንግሥት ተቀላቅለው ነፃ ተቋማት እንዳይኖሩ መደረጉን እና የዳኝነት ሥርዓቱ ከፍተኛ ችግር ያለበት መሆኑን መግለጻቸውን አድንቋል። “ንቅናቄዓችን ለዓመታት ሲናገር የነበረውን ሀቅ እሳቸው መናገራቸው፣ በአንድ በኩል እሳቸው በግላቸው ከእውነት ጎን ለመቆም ያላቸውን ቁርጠኝነት ሲያመለክት -በሌላ በኩል ደግሞ እሳቸው የሚመሩት የለውጥ ቡድን ለሀገራዊ መግባባት እያሳየ ያለው ዝግጁነት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ያመለክታል የሚል እምነት አሳድሮብናል” ብሏል ንቅናቄው። ” እነዚህ ቀድሞ ሲካዱ የነበሩ እውነታዎች በእርሳቸው አንደበት በምክር ቤቱ ስብሰባ መገለፃቸው፣ እስካሁን ሲፈፀሙ የነበሩ በደሎችን ለማስቀረት እና ጉድለቶችን ለማረም ብርቱ ፍላጎት እንዳላቸው ያሳያል ብለን እናምናለን” ያለው ንቅናቄው፣ ዶ/ር ዓቢይ እስካዛሬ በኢትዮጵያ የምክር ቤት ታሪክ ውስጥ ያልታየ ሀቀኝነት በማሳየታቸውም አድናቆቻችን ከፍተኛ ነው”ሲል ግልጿል። እንደ አርበኞች ግንቦት በሥራ ላይ ያለውንና ቋንቋን መሠረት ያደረገውን የክልል አስተዳደራዊ መዋቅር በተመለከተ የተናገሩትም ትኩረት የሚስብ ነው። በተለይ ቋንቋን መሠረት ያደረገ ማካለል በየቦታው ለሚነሱ የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች አስተዋጽኦ ማበርከቱን፤ የሕዝብ መፈናቀልና መገፋት ማስከተሉን፤ ዘረኝነትን በማባባስ በሀገራችን ውስጥ በአስደንጋጭ ሁኔታ ግጭት እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ማበርከቱን እና ክፍለ አህጉራዊ እይታን ነስቶ ዜጎች ስለመንደራቸው ወሰን አብዝተው እንዲጨነቁ ማድረጉን የሚገልጸው የንግግራቸው ክፍል- ለአብዛኛውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ የሰጠ እና የወደፊት መንገዳቸውን አመላካች ተደርጎ እንደተወሰደ ንቅናቄው

የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለጠ/ሚኒስትሩ አቀረቡ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ስብሰባ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል። “የጉራጌ ህዝብ የክልል ጥያቄ መልስ ያግኝ፣ የጉራጌ ምሁራንን ማግለል ለምን ተፈለገ? ጉራጌን ከንግድ አለም ለማስወጣት አሻጥር ሲፈጸምበት ደኢህዴን የት ነበር? በቀቢናና ጉራጌ ብሄረሰቦች መካካል ግጭት የቀሰቀሱት ለፍርድ ይቅረቡ” የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ዶ/ር አብይ ሰሞኑን በክልሉ ግጭት የቀሰቀሱ አካላት በራሳቸው ጊዜ ስልጣን ይለቃሉ ብለው እንደሚያምኑና ስልጣንም እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ አንድ የልኡካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩ አስታወቁ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት በየዓመቱ በሚከበረው የሰማዕታት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግር ነው። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ሁኔታ አዲስ ትብብር ለመመስረት ምቹ ነው ብለዋል። ህወሃት የውጭ ሃይሎችን አጀንዳ ለማራመድ ባደረገው ጥረት በሁለቱ አገራት መካከል ግጭት መቀስቀሱን የተናገሩት አቶ ኢሳያስ፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ጥፋት ህዝቡ ለአመጽ እንዲነሳና የህወሃት ሴራ ፍጸሜ እንዲያገኝ አድርጎታል ሲሉ ተናግረዋል። የህወሃት መሪዎች አገዛዛቸው እንዳበቃ ቢረዱትም፣ አሁንም ስልጣናቸውን ለማቆየት ከኤርትራ ጋር ያለው ውጥረት እንዲቀጥል ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ ስልቶችን ይጠቀማል የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ከእነዚህ ስልቶች አንዱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዳይሰፍን ማድረግ ነው ብለዋል። አገራቸው ይህንን መንገድ ለመዝጋትም ማሰቡዋንም ተናግረዋል። ህወሃት በሁለቱ አገራት መካከል የረጨው የጥላቻ መርዝ በቀላሉ ሊጠፋ እንደማይችልም አቶ ኢሳያስ አክለው ገልጸዋል። ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያን መንግስት የእርቅና ድርድር ጥሪ ለሰጡት ምላሽ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኤርትራን የልዑካን ቡድንን በታላቅ አክብሮት ተቀብላ ለማስተናገድ ዝግጁ ናት ብለዋል። የኤርትራ የሰጠቸው

Tuesday, June 19, 2018

ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ተዘጋጀ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍና ለማበረታታት የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ይደረጋል። አስተባባሪዎቹ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰልፉ አላማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰዷቸውን ጅምር የማሻሻያ ሀሳቦች ለመደገፍ፣ለማመስገንና ይበልጥ ለማበረታታት ነው። ከዚህ በተረፈ ሰልፉ የማንንም ፓርቲ አጀንዳ አያስተናግድም ብለዋል ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት አቶ ጉደታ ገላልቻ። በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ ብቻ በቂ ቢሆንም፣ ለዚህ እጅግ በርካታ የመዲናዋና አጎራባች ነዋሪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ለሚጠበቀው ሰልፍ ፈቃድ ለማግኘት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ጥያቄ ማቅረባቸውንም አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል። በአቶ ጉደታ ገላልቻ ከሚመራው እና ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ከሰጠው የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት መካከል፦ ከዓመታት እስር በኋላ በቅርቡ የተፈታው አቶ አበበ ቀስቶ፣ የአምቦ ዩኒቨርሲቲው መምህር የሆነው አክቲቪስት ስዩም ተሾመ፣ አክቲቪስት ስንታዬሁ ቸኮል እና አቶ አየለ ደጋጋ

የወላይታ ህዝብ በህዝብ ላይ ለደረሰው ሞት የክልሉን መሪን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረገ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሰሞኑን በሲዳማ እና በወላይታ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዛሬ በጉታራ አዳራሽ የወላይታ ከተማ ነዋሪዎችን ባወያዩበት ወቅት ፣ ህዝቡ ግጭቱን ያስነሱት የደቡብ ክልል ባለስልጣናት ናቸው ብሎአል። ህዝቡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከስብሰባ አዳራሽ እንዲወጡ ቢጠየቁም እርሳቸው ግን ስብሰባውን እስከመጨረሻው ተካፍለዋል። የወላይታ ሶዶ ዪኒቨርስቲ የወላይትኛ ቋንቋ መምህር የሆኑት አልማዝ አንጁሎ “የጨምበላላ በአል በክልል በጀት መከበር የለበትም በማለት የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ በዞን በጀት እንዲከበር ስላደረጉ የሲዳማ ባለስልጣናት ጥርስ ነክሰዉ እያስገደሉ ነዉ” በማለት ተናግረዋል። “እኛ ወላይታዎችን እየገደሉ ያሉት ሲዳማዎች ሳይሆኑ፣ ዛሬ ከርሶ ጋር የመጡት የክልሉ ፕሬዝደንት ናቸው በማለት መምህርት አልማዝ አክለዋል። ስብሰባውን ከተከታተሉት መካከል አንዱን አነጋግረነዋል። ዶ/ር አብይ ሃዋሳ ላይ ከሲዳማ ማህበረሰብ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት ደግሞ ግጭት ያስነሱት ሃይሎች ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል ።

በአርጎባና የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች መሃከል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ደረሰ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ በአርጎባ ማህበረሰብ ተወላጆችና በፈንታሌ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩ የከረዩ ማህበረሰቦች መካከል ከመሬት ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ። ትናንት በነበረው ግጭት ቢያንስ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 7 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የአካባቢው ናሪዎች ተናግረዋል። ግጭቱ አንድ ህጻን መገደሉን ሰበብ አድርጎ የተነሳ ቢሆንም፣ የኦሮምያ ልዩ ሃይል አባላት በግጭቱ ሳይሳተፉ እንዳልቀረ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። የሰሜን ሸዋ ዞን የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ተፈራ ግጭት መነሳቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ትክክል ቢሆንም፣ ከኦሮምያ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት የኦሮምያ ልዩ ሃይል መሳተፉን ለማረጋገጥ እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

የብሄራዊ ባንክ ገዢው ከሥልጣን ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 12/2010)የብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከሥልጣን ተነሱ በምትካቸው የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ተሹመዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ተመልክቷል።
አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ሹመቱ ያልተጠበቀ እና ከሙያው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለሌላቸው የተሰጠ ሲሉ ተችተዋል።
ከ10 ዓመታት በላይ በብሄራዊ ባንክ ገዢነት የቆዩትና አሁን ከሃላፊነት የተነሱት አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው መሾማቸውም ተዘግቧል።
ትናንት ሰኔ 11/2010 የብሄራዊ ባንክ ገዢ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ይናገር ደሴ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ቀደም ሲልም በተለያዩ ሃላፊነቶች ማገልገላቸው ተመልክቷል።
ዶክተር ይናገር ደሴ በሙያቸው ኢኮኖሚስት ቢሆኑም ፣ትምህርታቸው እንዲሁም ልምዳቸው ለተሰጣቸው ስልጣን የማያበቃቸው መሆኑን አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ይሰራል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 12/2010) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ሕዝብን የሚያገለገል ተቋም እንደሚሆን አዲሱ የተቋሙ ዋና ዳየሬክተር ገለጹ።
በቅርቡ በጠቅላይ ሚንስትር አብየ እህመድ የተሾሙት የቀድሞው የአየር ሐይል አዣዥ ጄኔራል አደም መሀመድ እንደገለጹት ተቋሙ የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ በመደራጀት ማሻሻያ ይደረግበታል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ትናንት ለፓርላማው ባደረጉት ገለጻ ደሕንነትና መከላከያው የፖለቲካ ወገንተኞችና የአፈና መሳሪያ ሆነው መቆየታቸውን መናገራቸው ይታወሳል።
ጄነራል አደም መሃመድ አዲሱ የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ትውወቅ አድርገዋል።

Monday, June 18, 2018

ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሽብር ድርጊት ሲፈጽም ቆይቷል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ራሱ በኢትዮጵያውያን ላይ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም መቆየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
መከላከያና ደህንነቱ ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ እንዲሆን ሕገ መንግስቱ ቢያዝም በተግባር ግን ይህ ሳይፈጸም መቆየቱንም ይፋ አድርገዋል።
ግንቦት 7፣ኦነግና ኦብነግ ግዜ ካለፈበት የመሳሪያ ትግል ራሳቸውን አቅበው ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዶክተር ብርሃኑ እኔን ገድለው ወይንም አስገድለው ስልጣን ቢይዙ እኔም እሳቸውን ብገድል ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ጉዳይ አይደለም ሲሉ አመልክተዋል።
በአሸባሪነት የታሰሩ ሰዎች የሚፈቱበትን ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ በፓርላማው ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሽብር ምንድን ነው አሸባሪስ ማነው የሚለውን በማብራራት ምላሻቸውን ጀምረዋል።
ሕገ መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣንን ለመያዝ የሚደረግ እንቅስቃሴ አሸባሪነት ከሆነ ሕገ መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረገውስ አካሄድ ምን ይባላል ሲሉ መልሰው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የወሰነው አዲስ ነገር የለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የተወሰነ ምንም አዲስ ጉዳይ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
ሕዝብ ሳይወያይበት ለምን በአደባባይ ተገለጸ በሚል ሕወሃት ያቀረበውን ጥያቄ በተመለከተም ከእንግዲህ የመደበቅ ፖለቲካ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
አሰብን ስንሰጥስ ሕዝብን አወያይተናል ወይ በማለት ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ ውጥረቱ ሊረግብ በድንበር ላይ ያለውም ሕዝብ እፎይ ሊል ይገባል ብለዋል።
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስከፊው ጦርነት እንደሆነ ዛሬ በፓርላማ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ላለፉት 20 አመታትም ሃገራቱ በውጥረት ውስጥ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል።

በለኩ በነበረው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ደረሰ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ቅዳሜ ከሃዋሳ 25 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ለኩ ከተማ ፣ የአብይ አህመድን አስተዳደር ያልተቀበሉ የደቡብ ክልል መሪዎች እንዳስነሱት በሚነገረው ግጭት በርካታ ጥፋት ደርሷል። የሲዳማ ወጣቶችን በማደራጀት በሌሎች ብሄሮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው የተደረገ ሲሆን፣ በርካታ የንግድ ቤቶች ወድመዋል። የአካባቢው የፖሊስ ሃይል ድርጊቱን በዝምታ መመልከቱን የአካባቢው ተወላጆች በጽኑ አውግዘዋል። ምንም እንኳ ግጭቱ ትናንትና ዛሬ ጋብ ያለ ቢመስልም፣ አሁንም ውጥረት መኖሩን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጻዋል።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ግልጽነት የተሞባለትና በብዙዎች የተወደሱበትን የመጀመሪያ ሪፖርት አቀረቡ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን፣ ትንተናዎቻቸውና ገልጽነታቸው ንግግሩን በስሜት ያዳምጡ በነበሩ የማህበራዊ ሚዲያ ታዳሚዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል። ዶ/ር አብይ ከዚህ በፊት የነበሩ ሁለት ጠ/ሚኒስትሮች ያደርጉ እንደነበረው ከፓርላማ ወንበራቸው ላይ ሆነው ሳይሆን፣ ሚኒስትሮችና የመምሪያ ሃላፊዎች መልስ ሲሰጡ ከሚቀመጡበት አፈጉባኤዋ ጎን ተቀምጠው መልስ መስጠታቸው የ26 አመታትን የፓርላማ ባህል ለመቀየር የታሰበ በጎ ጀምር ተደርጎ ተወስዷል። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መንግስታቸው ያከናወናቸውን ጉዳዮች ሪፖርት ያቀረቡት ጠ/ሚኒስትር አብይ፣ ከሪፖርታቸው በሁዋላ የተለያዩ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል። መንግስት የልማት ድርጅቶችን ለመሸጥ የወሰነባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ አንዱ ምክንያት ባላፉት ጊዜያት አገሪቱ ከፍተኛ ብድር በመውሰዱዋና የመክፈያ ጊዜው በመቃረቡ መሆኑን ገልጸዋል። ቀድም ብለው የተገነበሩት መሰረተ ልማቶች ጥራት በሌላቸው እቃዎች መገንባታቸውን ፣ ሙስናና አድሎ የተፈጸመባቸው መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አብይ አሁን ደግሞ የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ በፊት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሲሸጡ በጥቂት ሰዎች እንዲያዝ መደረጉ ትክክል አለመሆኑን በተለይ የማእድን ሽያጭ ለአንድ ግለሰብ መሸጥ እንዳልነበረበትና ህብረተሰቡ ቢያንስ ከ10 እስከ 15 በመቶ ሊገዛ ይገባው እንደነበርና ይህንንም ለመቀየር መንግስት ማሰቡን ተናግረዋል። የቡና እርሻዎችም በተመሳሳይ መንገድ መሸጣቸው አግባብ እንዳልነበር ገልጸዋል። አሁንም ቴሌ፣ መብራት ሃይልና አየር መንገድ የመሳሰሉ ድርጅቶች ሲሸጡ 5 በመቶ ለኢትዮጵያውያን እንደሚከፋፈል፣ አንድ ግለሰብ ብቻውን 5 በመቶ የሚሆነውን አክሲዮን መግዛት እንደማይፈቀድለት፣ ከ30-40 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ በሙያው ከፍተኛ ልምድ ላላቻው ኩባንያዎች እንደሚሰጥ፣ ዋናው አክሲዮን ግን በመንግስት እጅ እንደሚቆይ ዶ/ር አብይ ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ሲደወሉ የኢትዮጵያ ቁጥር የሚወጣው

Friday, June 15, 2018

300 የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እና በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩ ከእስር ተፈቱ

Image may contain: 2 peopleየአየር ሀይሎቹ መ/አ አንተነህ እና ዳንኤል ዛሬ ከተፈቱት ውስጥ መሆናቸው ታውቋል። 

Image may contain: 1 person, standing



















እግዚአብሔር ይመስገን!ከእንግሊዝ ቤተሰብ ጥየቃ አዲስ አበባ በሄደበት ተይዞ የነበረው እና አንዳርጋቸው ላይ መስክር እንለቅሃለን ቢሉትም አልመሰክርም በማለት ለእውነት የአምስት አመት መከራን የተቀበለው ወንድማችንን አበበ ወንድማገኝ መፈታቱ ታውቋል! ! !



Image may contain: 1 person

























የፅናት ተመሳሌት ብዙ መከራ እና ስቃይ የደረሰበት ጀግናዬ አበበ ካሴ በህይወት ወጥቷል











Govt blames deadly violence on “saboteurs of change” as mob kills several people in Southern Ethiopia

ESAT News (June 15, 2018)
The towns of Awassa (Hawassa) and Sodo in Southern Ethiopia have seen deadly mob attacks against innocent residents as federal and regional security forces in the area refuse to intervene to stop the bloodshed.Although exact figures are not known, several people were believed to have been killed today by an unidentified mob in Wolayta. According to a resident who spoke to ESAT from Sodo town, 20 people were killed in the violence today. ESAT could not verify the killings but the resident also said upto twenty homes were set ablaze.
Some blame the Sidamas for attacking the Wolaytas and other ethnic groups, while critical observers of the developments in Southern Ethiopia blamed saboteurs and groups supported by the regional ruling party, the South Ethiopian People’s Democratic Movement, and the TPLF, that is losing its grip on power in the federal government. The critics accuse agents supported by the TPLF of instigating violence across the country to discredit the administration of Prime Minister Abiy Ahmed.

በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት የለውጥ ሂደቱ ባልተዋጠላቸው አካላት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8/2010) በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ።
የፌዴራል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የመንግስትን አቋም በሚያመለክተው መግለጫው እንዳለው አካባቢያዊ ወሰንና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ለግጭት የሚያነሳሱ ሴራዎች እየተስተዋሉ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለምበአዋሳ የተጀመረው ግጭት ግድያን ዘረፋን ጨምሮ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በወላይታ ሶዶ ግድያውን በማውገዝ በተካሄደ ትዕይንተ ህዝብ ላይ ስዎች ተገድለዋል።
በተያያዘ ዜና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን በአጭር ጊዜ ወደ ቦታቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገረሳ ገለጸዋል፡፡
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው በግጭቱ የተሳተፉትን አካላት መርምሮ ርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ተደርጓል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የተፈጠረው ግጭት በሃገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ መሆኑን ነው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት የገለጸው።

300 ያህል እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) በሽብር ወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸው 300 ያህል እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ።
መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት እስረኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ከወህኒ ቤት እንደሚወጡም ተመልክቷል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው እስረኞች በአጠቃላይ 304 ሲሆኑ ፣ከነዚህ ውስጥ ከአስራ አምስቱ በቀር ሁሉም የአሽባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸው ናቸው።
አበበ ካሴ እና ከለንደን ሄዶ አዲስ አበባ ላይ የታሰረው አበበ ወንድም አገኝ እንዲሁም ጥላሁን አበጀ ከተፈቱት ውስጥ ይገኙበታል።
በአጠቃላይ በአሽባሪነት ተከሰው ተፈርዶባቸው እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው 289 እስረኞች ዘጠኙ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው መሆናቸውም ተመልክቷል።
እስረኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ከወህኒ ቤት እንዲወጡ የተወሰነ ሲሆን ፣ከተፈቺዎቹ ውስጥ ሶስት የኬኒያ ዜጎች እንደሚገኙበትም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በተመሳሳይ ሌሎችንም እስረኞች የመፍታቱ ሂደት እንደሚቀጥልም ከመንግስት ኮሚኒኼሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መግለጫ መረዳት ተችሏል።
በኢትዮጵያ የተካሄደውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ በኢሕአዴግ ውስጥ ብቅ ያለው የለውጥ ሃይል ባደረገው ግፊት ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎች፣ጋዜጠኞች ፣ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንዲሁም አክቲቪስቶችና ሌሎች በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ከየካቲት ወር ጀምሮ መፈታታቸው ይታወቃል።
መንግስት ከፌደራል ወህኒ ቤት በቅርቡ የተፈቱ እስረኞች ቁጥር 1105 መሆኑንም አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ጅቡቲ ዛሬ 45 ኢትዮጵያውያንን ከወህኒ ቤት መፍታቷን አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢን ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው ይችላሉ ተባለ

Image may contain: 1 person(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ የሆኑትን አቶ ተክለውልድ አጥናፉን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው እንደሚችሉ ተዘገበ።
በአዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ አዲስ ፎርቹን እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት ዶክተር ይናገር ደሴን ይሾማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተወስኗል።
ሆኖም አቶ በቃሉ ዘለቀ ከንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትነት ተነስተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ሊሆኑ እንደሚችሉም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ምንጮችን በመጥቀስ አዲስ ፎርቹን ዘግቧል።
ኢሳት የውስጥ ምንጮችን በመጥቀስ የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እንዲነሱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መወሰኑን መዘገቡ ይታወሳል።
በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ውስጥ የአፍሪካ ሃላፊ የሆኑት አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት መጠየቃቸውን ሆኖም ባሉበት ሃላፊነት ሳቢያ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በኢሳት መዘገቡም አይዘነጋም ።
የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ዶክተር ዮሃንስ አያሌው ቀደም ሲል ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል

ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንደሚመልሱ አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ

Bildergebnis für ለማ መገርሳ(ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው የለማ አስተዳደር የተፈናቀሉትን ዜጎች ወደ ነበሩበት ቀዬ ለመመለስ ስራዎችን እየሰራ ነው። አቶ ለማ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ባደረጉ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል። የኦሮምያ ክልል የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በባህርዳር ተገኝተው ከተፈናቀሉት ዜጎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የክልሉ ሚዲያ ዘግቧል።

ህወሃት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ታወቀ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ህወሃት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ስምምነትን በተመለከተ ኢህአዴግ በቅርቡ የወሰነውን ውሳኔ ለመቃወም እንዲሁን በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር የተወሰዱ ምደባዎችን ለመቃወም የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርጋል። ለሰለፉ ማካሄጃ ከፍተኛ ገንዘብ የተመደበ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ከትግራይ ክልል በህወሃት ወጪ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ምንጮች ገልጸዋል። ዜናውን እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ አልተሰጠም፣ ይሁን እንጅ ህወሃት ሰልፉን በጉልበት እንደሚያካሂድ ሲዝት መዋሉት የመስተዳድሩ ምንጮች ገልጸዋል። ህወሃት በአደባባይ በባድመ ዙሪያ የተላለፈውን ውሳኔ እንደደገፈው ቢገልጽም፣ አጋጣሚውን የትግራይን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ በአብይ አስተዳደር ላይ ጫና ለመፍጠር ማሳቡ ተነግሯል።

በወላይታ ሶዶ በተደረገው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ጠፋ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዋሳ ከተማ የተካሄደውን የሲዳማ ማህበረሰብ አመታዊ የመን መለወጫ በአልን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት የተገደሉ ዜጎችን ድርጊት ለመቃወም ዛሬ በወላይታ ሶዶ በተካሄደው ተቃውሞ እስከ 5 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን በርካታ የመንግስት መስሪያቤቶችና መኪኖች መውደማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የሶዶ ከተማ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም፣ የዞኑ ባለስልጣናት ፈቃድ በመከልከላቸው በቁጣ ገንፍሎ መውጣቱንና ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆን ማድረጉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በኦሮሚያ ባንክ ዘበኛ የነበረ ሰው ወጣቶቹ በባንኩ አካባቢ ሲያልፉ ሁለት ወጣቶችን ተኩሶ መግደሉን፣ በዚህም የተነሳ የሕዝቡ ቁጣ አይሎ ወጣቶችን የገደለውን ዘበኛ ወጣቶች እንደገደሉት የአይን እማኞች ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶችም ቆስለው ሆስታል ገብተዋል። በሃዋሳ የተነሳውን ግጭት ወደ ብሄር ግጭት ለመለወጥ የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ ቁጥራቸውን በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል። በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል። ወታደሮች ከተማዋን የተቆጣጠሩ ቢሆንም፣ አሁንም ውጥረት እንዳለ የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በከተማዋ ያለው የስልክ አገልገሎት በመቋረጡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አልቻልም። መንግስት ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ የለውጡን ሂደት ለማደናቀፍ የሚፈልጉ ሃይሎች በእየቦታው ግጭቶችን እያስነሱ መሆኑን ጠቅሷል። በእነዚህ ሃይሎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ቢገልጽም፣ ለውጡን ይቀለብሳሉ የሚላቸውን ሃይሎች በዝርዝር አልገለጸም። አርበኞች ግንቦት7 ትናንት ባወጣው መግለቻ ደግሞ “የኢህአዴግ ፀረ-ለውጥ ኃይል የለውጡን ሂደት ለማደናቀፍ በሚያደርገው ጥረት የረዥም ጊዜ ተጎጂ ራሱ እንደሆነ መገንዘብ ይጠቅመዋል። ከእንግዲህ እንደቀድሞው ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ መግዛት አይቻልም፤ ከእግዲህ የሕዝብ ሀብት በግላጭ መዝረፍ አይቻልም። ይህን በጊዜ አለመገንዘብ ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላል። “ ብሎአል።

የኢድ አልፈጥር በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው

(ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) 1 ሺህ 439ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነስርዓቶች በመከበር ላይ ሲሆን ሙስሊም ኢትዮጵያውያውን የተፈናቀሉ እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ዜጎችን እንዲያስቡ የሃይማኖቱ መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። በዓሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያለ ጸጥታ ችግር ተከብሯል። በጅጅጋ በአቶ አብዲ አሌ ትዕዛዝ በከተማው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢድ በአል በአደባባይ አለመከበሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሌሎች ከተሞች ያሉ የክልሉ ተወላጆች ግን ከኢድ በአል በሁዋላ አብዲ ኢሌን የሚያወግዙ መፈክሮች በማሰማት ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።

Thursday, June 14, 2018

Ethiopia: Over 200 killed in ethnic violence Southern Ethiopia

ESAT News (June 14, 2018)
Over 200 people were killed in ethnic violence in Guji Zone in Southern Ethiopia over the past ten days while over 300,000 have been displaced. The violence between the Guji and Gedeo groups that began in April has also resulted in the destruction of schools, churches and private properties.The Association of Gedeo Community in North America has documented the names of 137 ethnic Gedeos who were killed by the Gujis in West Guji Zone.
The report by the Association, sent to the office the Prime Minister, and copied to media outlets show that women were also gang-raped.
“The nature of the attack is horrifying,” the document said and added that “apart from firearms, machete and spears are used in the killings. Several ethnic Gedeos were beheaded, thrown into rivers or burnt in their locked houses.”
The over 200 killed since June 3, 2018 is on top of the over 125 people killed since mid-April.

Ethiopia: Andy Tsege says PM puts his job on the line for his release

  A high profile Ethiopian political prisoner recently released after four years in jail said the country’s Prime Minister told him that he had threatened to resign from his post if the ruling party would not release him.

The death row prisoner, Andargachew (Andy) Tsege, told the BBC’s Hardtalk Zeinab Badawi that he was surprised the Prime Minister, Abiy Ahmed, raised the stakes high for his release.
“He said to the ruling party that either he would resign or i would be released,” Andy said, “those were exactly his words.”

በወልቂጤ ህዝባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) በወልቂጤ ህዝቡ ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ። የመከላከያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ ወጣቱን በማፈስ እያሰሩ ቢሆንም ነዋሪው ቁጣውን በመግለጽ ላይ ነው። በእስከሁኑ ተቃውሞም ሶስት ሰዎች ተገድለዋል።
ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ የህክምና ማዕከላት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ከ30 በላይ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን አራት የመንግስት ተሽከርካሪዎችም በእሳት መጋየታቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በሀዋሳ በተነሳው ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ዛሬ በአንዳንድ የከተማዋ አከባቢዎች ግጭቶች መከሰታቸውም ታውቋል። ማክሰኞ ድንገት የተጀመረው የእርስ በእርስ ግጭት ወደአጠቃላይ ቀውስ ተሻግሯል።
በህወሀት አገዛዝ በተተከለው ብሄር ተኮር መዋቅር ምክንያት ውዝግብ ተለይቶት የማያውቀው የጉራጌ ማህበረሰብ በማንነት ጥያቄ ሰበብ ወደ ከፋ የእርስ በእርስ ግጭት ያመራል የሚለው ስጋት እየተሰማ ነው።

በጌዲዮ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ቀጥሏል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጅ በጌዲዮ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል መቀጠሉ እንዳሳሰበው በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የጌዲዮ ማህበረሰብ ማህበር አስታወቀ።
ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ለሚመለከታቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ባለፈው 10 ቀናት ብቻ ከ2 መቶ በላይ የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ሲገደሉ ከ3መቶ ሺህ በላይ ደግሞ ከሚኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለዋል።
ማህበሩ ከ137 የሚበልጡና በግፍ የተገደሉ የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላትን ስም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።
በደቡብ ክልልና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጅ ዞን የሚኖሩ የጌዶ ማህበረሰብ አባላት ቁጥራቸው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን እንደሚደርስ በ1999 በተካሄደው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ተረጋግጧል።
እነዚሁ የብሔረሰቡ አባላት በእርሻ ስራና በቡና አምራችነታቸው ይታወቃሉ።

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ወጡ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው በመውጣት ላይ መሆናቸው ተገለጸ።
የአማራ ተወላጆች የሚደርስባቸው ጥቃት እንዲቆም በመጠየቅ ባለፉት አራት ቀናት የተጀመረው ተቃውሞ በክልሉ ልዩ ሃይል የሃይል ርምጃ መወሰዱን ተከትሎ ተማሪዎቹ ሻንጣቸውን ይዘው ከግቢ መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ትላንት ግቢው ድረስ ዘልቆ የገባው ልዩ ሃይል በተማሪዎች ላይ ድብደባ በመፈጸም ከባድ ጉዳት ማድረሱም ታውቋል።
መንገድ ላይ የተገኘ ነዋሪም ሲደብደብ መዋሉን በቪዲዮ ተደግፎ ከወጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ተቃውሞ ሲደርግ ቆይቷል።
በዩኒቨርስቲው አራቱ ካምፓሶች ተማሪዎች የጀመሩት ተቃውሞ ከግቢያቸው በመውጣት ወደ ባህርዳር ከተማ ያመራ ሲሆን ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በተፈጠረ ግጭት ወደ መሀል መዝለቅ ሳይችል መቅረቱ ታውቋል።

የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ቅሬታውን አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ላይ ቅሬታውን አቀረበ።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባድመን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሁም ግዙፍ የመንግስት ተቋማት በከፊል ወደ ግል እንዲዞሩ የተደረሰበትን ስምምነት ግን እንደሚቀበለው አረጋግጧል።
የእስከዛሬው ድላችንም ሆነ የነገው ስኬታችን በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ብቻ ነው ብሏል የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ።
ይህ ተግባራዊ መስመር በኢሕአዴግ አመራር እየተሸረሸረ ነው ሲልም ማዕከላዊ ኮሚቴው ቅሬታውን አቅርቧል።
እየተካሄደ ያለውን የስልጣን ድልድል በተመለከተም ከኢሕአዴግ ሕገ ደንብ ያፈነገጠ ነው ያለው ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለድርጅታችን ነባር አመራሮች እውቅና እንዲሰጥና አስቸኳይ ጉባኤ እንደጠራ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
የሕወሃትና ማዕከላዊ ኮሚቴ ነባሮቹን አመራሮች አቶ ስብሃት ነጋን፣አቶ ስዩም መስፍንና አቶ ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ ከሰኔ 3 እስከ 5 በመቀሌ ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ ተከትሎ ያወጣው መግለጫ በፓርቲውና በስርአቱ ውስጥ ያለውን ጥርጣሬና ቅሬታ በግልጽ አንጸባርቋል።

Wednesday, June 13, 2018

ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበለት ሜቴክ የሚሰራው የመልካ ሰዲ ሃይል ማመንጫ ባለበት መቆሙ ታወቀ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ሜቴክ የሚሰራው ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የመልካ ሰዲ የእንፋሎት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከማጠናቀቂያ ጊዜው 2 ዓመት ቢዘገይም እስካሁን የተሰራው ከ25 በመቶ እንደማይበልጥ መረጃዎች አመለከቱ። ፕሮጀክቱን የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በዋና ተቋራጭነት እንዲሁም ግሬስ ኢንጂነሪንግ በንጹስ ተቋራጭነት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢንጂነሪን ቢሮ ደግሞ በአማካሪነት ይሰሩታል። ፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪው በመንግስት በሚሸፈን 4 ቢሊዮን 160 ሺ ብር የተጀመረ ሲሆን ፣ ሰኔ 9 ቀን 2006 ዓም ተጀምሮ፣ ሰኔ 2008 ዓም ይጠናቃል ተብሎ ታቅዶ ነበር። በተባለው ጊዜ ባለመጠናቀቁ ተጨማሪ የመጣናቂያ ጊዜ እስከ ጥር 2009 ዓም ተሰጥቷል። ከሁለት አመታት መዘግየት በሁዋላ በአሁኑ ሰዓት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸምም 27 በመቶ ብቻ ሲሆን፣ በሜቴክና በመንግስት መካከል የስራን አካሄድ በተመመለከተ መግባባት ላይ ሊደረስ አልቻለም።የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በውል ለመግለጽ እንደማይችልም መረጃዎች ያሳያሉ። ለችግሩ መፍትሄ ለመሻት የተደረገው ሙከራም በሜቴክ ባለስልጣናት መደናቀፉ ታውቛል። ከአዲስ አበባ በ270 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዞን ሶስት አሚባራ ወረዳ ላይ የእርሻና የግጦሽ መሬትን በስፋት በመውረር በግጦሽና በሰብል መሬት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረስ የሚገኘውን ፕሮስፒስ ደሊን ፕሎራ ተብሎ የሚጠራውን መጤ አረም መንጥሮ በማቃጠል የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚከናወን ፕሮጀክት ነው።

በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከሆሊስቲክ ፈተና ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የጀመሩትን አድማ ተከትሎ ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በምህንድስና ግቢ የሚማሩ ተማሪዎች የጀመሩት አድማ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ተማሪዎች ግቢ በመግባት ድብደባ ፈጽመዋል። አንዳንድ የተጎዱ ተማሪዎች ወደ ህክምና ጣቢያዎች ተወስደዋል።የፖሊስና መከላከያ ሃይሎች ተማሪዎችን ከግቢ ለማስወጣት በአጥር ዘለው ሲገቡ የአይን ምስክሮች የተመለከቱ ሲሆን፤አብዛኞች ተማሪዎች ዩኒቨረስቲው ግቢ አቅራቢያ ባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የግለሰብ ሆቴሎች አካባቢ በመጠለል ሁኔታውን እየተከታተሉ ነው፡፡ ተማሪዎች በአንድ ፈተና ከሃምሳ በታች ካመጣችሁ ከግቢው ትባረራላችሁ በሚል ዩኒቨርስቲው በአዲስ ያወጣውን መመሪያ በመቃዎም ወደፈተና ክፍል አንገባም በማለታቸው አመራሮች የማትፈተኑ ከሆነ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚል ልዩ ሃይል አስገብተው ለማስወጣት በተደረገው ሙከራ ግጭት መነሳቱን ወኪላችን ዘግቧል። ከከተማ ወደ አባይ ማዶ የሚወስደው ዋናው አስፓልት ተዘጋ ሲሆን ግቢው በልዩ ሃይል ፖሊሶችና መከላከያ አባላት ተወሯል፡፡ ሰኞ ዕለት ተጀምሮ የነበረው የማጠቃለያ ፈተናም በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ተቋርጧል፡፡ተማሪዎች ከምኝታ ክፍላቸው አንዳይወጡ በመደረጋቸው አልፎ አልፎ የህብረት ጩኸት ያሰማሉ፡፡

በይርጋጨፌ ትናንት በነበረው ግጭት ቤቶች ተቃጠሉ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) በጉጂና በጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ አንዳንድ የደኢህአዴን አመራሮች ያሰማሯቸው የአካባቢው ባለስልጣናት “እኛ ተረጋግተን ሳንኖር እናንተ በእኛ ቦታ መኖር አትችሉም” በሚል የአካባቢውን ወወጣቶች አደራጅተው በጉራጌ፣ በአማራና በሌሎች ብሄረሰቦች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ማድረጋቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት የተለያዩ ሰዎች ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ዛሬ፣ ብዙዎቹ የንግድ ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ውለዋል። ተጨማሪ ጥቃት ይፈጸማል በሚል የከተማ ነዋሪዎች በስጋት እያሳለፉ መሆኑን ተናግረዋል። በአካባቢው ወታደሮች የሌሉ በመሆናቸው ስጋታቸውን እንዳባባሰው ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።

በሀዋሳ እና ወልቂጤ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010) በደቡብ ክልል ሀዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
በሃዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች ግጭቶች ተከስተዉ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል።
በሁለቱም ከተሞች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎም ሰዎች መገደላቸው እየተነገረ ነው። በሃዋሳ የሚከበረው የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨንበላላ በአል ሲከበር በከተማዋ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ተገኝቶ ነበር።
ይሕንኑ የዘመን መለወጫ በአልን ምክንያት በማድረግ የተሰበሰበው ሕዝብ የሲዳማ ዞን በክልልነት እንዲዋቀር የሚጠይቅ መፈክር ሲያሰማ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
የሲዳማ ዞን ዋና ከተማው ሀዋሳ ሆኖ በክልልነት ካልተዋቀረ ሰላም አይኖርም ሲሉ የሚዝቱ እና በሌሎች ብሄረሰቦች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ እንደነበርም ነው የተገለጸው።

የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ ዛሬ ባደረገው አስቸካይ ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው ማንሳቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

(ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ሐረሪ ብሔራዊ ሊግ አመራሮች ለ 27 አመታት በክልሉ በሚኖሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት ጭቆና እንዲቆም በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ ቁጥራቸው ከ 600 በላይ የሚሆኑ የብሔረሰብ አባላት ባደረጉት አስቸካይ ስብሰባ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ እንደማይወክላቸው በሙሉ ድምጽ ገልጸው ነበር። የቀድሞውን የፖርቲው ሊቀ-መንበር የነበሩት እና ከድርጅት ተባረው የነበሩት አቶ ዘይዳን በክሪ የግዜያዊ ባላደራ ኮሚቴ ሰብሳቢ በማድረግ እንዲሰሩ ሲመደብ፣ ሌሎች 20 የኮሚቴ አባላት ሆነው እንዲሰሩ ተመርጠው ነበር። ዛሬ ደግሞ የሊጉ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ሃረርን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በወልቂጤ በተነሳው ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ንብረትም መውደሙን ነዋሪዎች ገለጹ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው እሁድ የእግር ኳስ ጨዋታን ሰበብ በማድረግ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ ዛሬ ግጭቱ ተባብሶ የሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች መውደማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ትናንት ማክሰኞ ደግሞ ካምፕ 99 በሚባለው አካባቢ ከህገወጥ ግንባታ ጋር በተያያዘ የከተማው ሹሞች ቤቶችን ሂደው በሚያፈርሱበት ሰዓት የቀቤና ተወላጆች፣ የመዘጋጃቸው ሹሞች ጉራጌዎች ናቸው በማለት ተቃውሞ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ዛሬ ግጭቱ በከፍተኛ ደረጃ ተባብሶ በመቀጠሉ በርካታ ቤቶችና መኪኖች ተቃጥለዋል። በግጭቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነዋሪዎች ህይወታቸው አልፏል። ዘርማ እየተባሉ የሚጠሩ የጉራጌ ተወላጅ ወጣቶችን ቤቶችና መኪኖችን ማቃጠላቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ በድርጊቱ የተበሳጩት የጉራጌ ተወላጆች ራሳችንን እንከላከላለን በማለት ጥቃት መፈጸማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ግጭቱን የአዲሱን የዶ/ር አብይ አመራር ለመቀበል ፍላጎት ያጣው ደቡብ ክልልን የሚመራው የህወሃት ደጋፊ የሆኑ የደኢህዴን ቡድን አባላት ናቸው በማለት ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች አምስቱ ታፍነው ተወሰዱ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010) ለአቤቱታ አዲስ አበባ ከሚገኙት የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች መካከል አምስቱ ታፍነው መወሰዳቸው ተገለጸ።
ላለፉት ሁለት ወራት አዲስ አበባ ሆነው በሶማሌ ክልል ህዝብ ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አፈናና ግድያ እንዲቆም ለመጠየቅ እያደረጉ ያሉት ጥረት በህወሃት ደህንነቶችና የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ባሰማራቸው አፋኝ ሃይሎች ምክንያት ሊሳካ እንዳልቻለ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ በህወሃት ደህንነቶች ወከባ እየተፈጸመባቸው ያሉት የሃገር ሽማግሌዎቹ የፌደራል መንግስት ጥበቃ ያድርግልን የሚል ጥሪ እያቀረቡ ባሉበት ጊዜ ነው አምስቱ ሰዎች የታፈኑት። ወዴት እንደተወሰዱ ለማወቅ እንዳልተቻለም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ የድረሱልን ጥሪ ሰሚ ያገኘ አይደለም ይላሉ ጉዳዩን እየተከታተሉ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች።
ባለፈው ሳምንት ከሀገር ሽማግሌዎቹ አንደኛው በአብዲ ዒሌ የተሰማሩ ሰዎች አፍነው ከወሰዷቸው በኋላ ባሰሙት የድረሱልን ጥሪ የፌደራል መንግስት በአፋጥኝ የደህንነት ጥበቃ ያድርግልን ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ኦህዴድ ከ2ሺ የሚበልጡ አባላቱን አባረረ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ባካሄደው 8ኛ ጉባኤው ከ2ሺ የሚበልጡ አባላቱን አባረረ።
ከ500 የሚበልጡ የድርጅቱ አባላትን ደግሞ ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ ማድረጉ ተሰምቷል።
ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደገለጹት ኦሕዴድ ምንጠራ ያካሄደባቸው እነዚህ ግለሰቦች ነዋሪዎችን በአስተዳደር የበደሉ የሌላ አካባቢ ተወላጆች ናቸው ያሏቸውን ሰዎች ደሞ ከቀያቸው ያባረሩና ያቆሳቆሉ ናቸው።
ትላንት ማክሰኞ የሶስት ቀናት ድርጅታዊ ጉባኤውን ያጠናቀቀው የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦሕዴድ/ በክልሉና በአጎራባች ክልሎች መካከል ያለውን የድንበር ግጭት እንዲሁም በክልሉ በሚኖሩ የሌላ አካባቢ ተወላጆች በሚል የሚፈናቀሉ ነዋሪዎችን በተመለከተ መነጋገሩ ታውቋል።
ሕገወጥ የመሬት ወረራን ጨምሮ በክልሉ ይካሄዳሉ ያላቸውን ሕገ ወጥ ድርጊቶችና የውሸት ሪፖርቶችን ጭምር የገመገመው የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦሕዴድ/ በዚህ ሒደት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ከ2000 የሚበልጡ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮችን አባሯል።
540 የሚሆኑትንም ከደረጃ ዝቅ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደብዳቤ ላከ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010)ኢሕአዴግ የአልጀርሱን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበሉን በመቃወም የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደብዳቤ ላከ።
መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ኮሚቴው በላከው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው በበቂ ማስረጃ ባልተደገፈ መልኩ የተደረገው ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢህአዴግ በኩል የተወሰነውን ውሳኔ እንዲያጤኑት ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት በህወሃት በኩል እየተደረገ ያለውን ሴራ እንዲያስቆሙትም በደብዳቤው ጥሪ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላከው ደብዳቤ ሲጀምር በዶክተር አብይ በጎ ተግባራት የተሰማውን ደስታ በመግለጽ ነው።
ኮሚቴው በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተደረጉ ያሉ ጅምር እንቅስቃሴዎች ተስፋ የሚሰጡ በመሆናቸው አድናቆት የሚቸራቸው እንደሆነ ገልጿል።
በመቀጠል በኢህአዴግ በኩል የተወሰደውንና የአልጀርሱን ስምምነት የተመለከተውን ውሳኔ እንዲሁም ለሱዳን ተላልፈው የተሰጡና ሊሰጡ

ከአቢሲኒያ ባንክ የተዘረፈው ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ተያዘ

(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 6/2010) በአቢሲኒያ ባንክ ከ5ሚሊዮን ብር በላይ ተዘርፎ በኋላ ላይ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ቦሌ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ ቴሌ መድሃኒያለም ቅርንጫፍ 5 ሚሊየን ስድስት መቶ ሺህ ብር ተዘርፎ በፖሊስ እና በአካባቢው ማህበረሰብ ትብብር ዘራፊዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አረጋግጧል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንደገለጹት ዘረፋው የተፈፀመው የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኛ ከነበሩት ግለሰብ ጋር ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ተባብረው ነው።
በአሁኑ ጊዜ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው አጠቃላይ የተወሰደው ገንዘብም ተመልሷል ብለዋል።
የአቢሲኒያ ባንክ የማርኬቲንግ፣ የኮሚኒኬሽንና ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አስቻለው ታምሩ በበኩላቸው የዘረፋ ሙከራው የተፈፀመው መኪና ይዘው በመደራጀት መሆኑን ገልጸዋል።
በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሌሎች ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ነው የተናገሩት።

Ethiopia: Bank heist fails, suspects apprehended

by Engidu Woldie
ESAT News (June 13, 2018)
A bank robbery in Ethiopia’s capital Addis Ababa went on the blink when a driver carrying the alleged crooks drove on the wrong way and hit another vehicle.The robbers tried to runaway after the crash but were caught by passersby, who thought it was just a case of a hit and run.

Tuesday, June 12, 2018

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ እንዲታገድ ጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 5/2010)የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ባሳለፍነው ሳምንት 14 ሰዎች መግደሉን ተከትሎ አምንስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ አወጣ።
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራክረው አምንስቲ ኢንተርናሽናል የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ካልታገደ በሰዎች ላይ የሚደርሰው ግፍና ሰቆቃ ማቋረጫ የለውም ብሏል።
የሶማሌ ልዩ ፖሊስ በጭናቅሰን ወረዳ በፈጸመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋግጧል።
ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚል በሶማሌ ክልል የተቋቋመው ልዩ ፖሊስ እርሱ ራሱ ሰዎችን አሸባሪ ከሆነ ሰነባብቷል።
የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ከተቋቋመ ወዲህ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው ነው የሚነገረው።

ኩባንያዎችን ለመሸጥ የተወሰነው በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ– ሰኔ 5/2010) የኢትዮጵያ መንግስት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ለመሸጥ የወሰነው በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መሆኑን ይፋ አደረገ።
የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ ለፋና ተሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በተፈጠረው የእዳ ጫና እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መንግስት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ለመሸጥ ተገዷል።

ከሜቴክ በቅርቡ ከተገዙት 500 አውቶብሶች 200 የሚሆኑት ከጥቅም ውጭ መሆናቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 5/2010) የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሜቴክ በቅርቡ ከገዛቸው 500 አውቶብሶች 200 የሚሆኑት ከጥቅም ውጭ መሆናቸው ተገለጸ።
የከተማው አስተዳደር በሕወሃት የጦር ጄነራሎች ሲመራ የነበረውን ሜቴክን በድርጊቱ ያወገዘ ቢሆንም ፣ የ 3.5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ሥምምነት ማድረጉ ተዘግቧል።
አዲስ ፎርቹን የከተማው አስተዳደር አንድ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሜቲክ ለአዲስ አበባ ከተማ አንበሳ አውቶብስ ድርጅት የተገዙት አውቶብሶች የጥራት ችግር ያለባቸው ፣ሲበላሹም መለዋወጫ የማይገኝባቸው ናቸው።

የሲዳማ ፍቼ ጨምበላላ በዓል መከበር ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 5/2010) የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል መከበር መጀመሩ ተገለጸ።
ፍቼ ጨምበላላ በሚል መጠሪያ የሚከበረው በዓል በብሄረሰቡ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ባህላዊ ፌስቲቫል ነው።
ከሀዋሳ ዙሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ የብሄረሰቡ ተወላጆችና የአከባቢው ነዋሪዎች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው እያከበሩት መሆኑንም የደረሰን ዜና ያመለክታል።
ፍቼ ጨምበላላ የማይዳሰሱ ቅርሶች በሚል በመንግስታቱ ድርጅት የባህልና የሳይንስ ተቋም ዩኒስኮ ከተመዘገቡ የሀገራችን በዓላት አንዱ እንደሆነም ይታወቃል።
የሲዳማ ሴት ከጋብቻ በኋላ በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ቤተሰቦቿ የምታደርገውን ጉዞ በማስታወስ የሚከበር በዓል ነው ፍቼ ጨምበላላ።
ይህቺ ሴት ወደ ቤተሰቦቿ ስታመራ በቆጮና በቅቤ የሚሰራ ቡርሳሜ የተሰኘ ባህላዊ ምግብ አዘጋጅታ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ቡርሳሜውን ቤተሰቦቿ ከጎረቤቶቻቸው ጋር በመሆን እየተመገቡ ጊዜውን በደስታ የሚያሳልፉበት ልዩ ወቅት ነው።
ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የቆየው ታሪክ የሲዳማ ህዝብ በዓመት አንድ ጊዜ የሚውለውን የፍቼ ጨምበላላ በዓል መነሻ ተደርጎ ተመዝግቧል።

በሶማሊ የአገር ሽማግሌዎች ላይ የሚደርሰው ወከባ ጨምሯል

(ኢሳት ዜና ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ/ም) የህወሃት ታጣቂዎች የአብዲ አሌን አገዛዝ በመቃወም ለፌደራል መንግስቱ አቤቱታ ለማሰማት በተንቀሳቀሱ የአገር ሽማግሌዎች ላይ አሁንም ዛቻና ማስፈራሪያ እያሰሙ ነው። ዛሬ 10 አሮ አብዲ አሌን የሚቃሙ የክልሉ ተወላጆች በታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአነጋገርናቸው የክልሉ ተዋላጆች ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሼክ አብዲ ዱብ እና ሼክ አብዲ ቡሉህ የተባሉ የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ኦሮሞዎች ከሶማሊ ክልል ሲፈናቀሉ በመቃወማቸው ብቻ ከአንድ አመት በላይ በእስር ሲሰቃዩ ከቆዩ በሁዋላ፣በጅግጅጋ ከተማ በተሰየመው ፍርድ ቤት እያንዳንዳቸው በ5 አመት ጽኑ እስራት ተቀጠዋል። የሶማሊ ክልል ህዝብ በአቶ አብዲ አሌ ላይ የጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

በአማሮ ወረዳ ትናትን በነበረው ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ/ም) ከድንበር ማካከለል ጋር በተያያዘ በጉጂና በኮሬ ማህበረሰቦች መከካል የተጀመረውና ለአንድ አመት የዘለቀው ግጭት ደም አፋሳሽ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፣ ከአማሮ በኩል ከዶርባዴ ቀበሌ ልዩ ስሙ በርበሬ ከሚባል አካባቢ አንድ አርሶአደር ሲቆስል፣ ምንም እርምጃ አልወሰዱም በሚል ህዝቡ ተቃዉሞ ያስነሳባቸው ሁለት የመከላከያ አባላትም ሲጎዱ፣ አንደኛው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወታደሮች ሶስት የጉጂ ኦሮሞ ማህበረሰቦችን ሲገድሉ ሰባት ደግሞ አቁስለዋል። በጉጂ በኩል የሞቱትን ለማወቅ ባይቻልም፣ ግጭቱ ከተጀመረበት ከሃምሌ 2010 ዓም ጀምሮ በኮሬ በኩል 52 ሰዎች ተገድለው ከ100 በላይ ቆስለዋል። ከቡሌ ሆራና ከወረዳዉ ቆላማ ቀበሊያት/በተለይ ከዶርባዴና ጀሎ/ የተፈናቀሉ ከ 20፣ ሺ በላይ ዜጎችም እገዛ በማጣት ለከፋ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከአማሮ ዲላ የሚወስድ መንገድ ዛሬም ዝግ እንደሆነ ነው።

በሃዋሳ ከተማ የጨምበለላን በዓል ተከትሎ ግጭት ተነሳ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች የሚከበረው የሲዳማ ማህበረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ፣ ጨምበለላ፣ በአዋሳ ከተማ በሚከበርበት ወቅት ያልታሰበ ግጭት ተነስቷል። በግጭቱ የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከተማዋ በታጠቁ ሀይሎች ተሞልታለች። ሲዳማ ወጣቶች በባህላዊ ዜማ በቡድን በቡድን ሆነው እየዘመሩ ተቃውሞአቸውን ቢያሰሙም፣ ባለ ቀይ መለዮ ወታደሮች በዱላ እና በሰደፍ እየደበደቡ ለመበተን ሲጥሩ መታየታቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ግጭቱ ሆን ተብሎ በደኢህዴን ባለስልጣናት እንደተነሳ፣ በተለይም የአዲሱን ጠ/ሚኒስትር ወደ ስልጣን መምጣት ያልተቀበለው የደኢህዴን ቡድን ፣ የዶ/ር አብይን ምስል የያዘ ቲሸርት እንዳይለበስ በመከልከላቸው ውዝግብ መፈጠሩን ይናገራሉ። የሲዳማ ተወላጆች ሃዋሳ በክልል ደረጃ እንዲዋቀር ጠ/ሚኒስትሩ ከተማዋን በጎበኙበት ወቅት መጠየቃቸውን፣ ይህንኑ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ሲጠየቁ መዋላቸውን ነገር ግን የክልሉ ባለስልጣናት ግጭት እንዲፈጠር ሆን ብለው የተደራጁ ቡድኖችን መላካቸውን ስፍራው ላይ የነበሩና ድርጊቱን ሲከታተሉ የነበሩ ለኢሳት ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ የደኢህዴን ባለስልጣናት የሰጡት መግለጫ የለም። ጨምበለላ የሲዳማ ተወላጆች ባህላዊ ልብሶችን ለብሰው፣ አዛውንቱ መልካም ምኞታቸውን በምርቃት እየገለጹ፣ ወጣቶች እየጨፈሩ የሚያከብሩት ባህል ነው። ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች “የቄጣላ” ጨዋታ፣ የፈረስ ጉግስን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችን ያከናውናሉ። ይህ አለማቀፍ እውቅና ያገኘው በዓል፣ ለሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ይከበራል።

Monday, June 11, 2018

ኮሎኔል አበበ ገረሱ አዲስ አበባ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4/2010)በምርጫ 1997 በሕዝብ ላይ የደረሰውን ግድያ በመቃወምና የሕዝብ ድምጽ መሰረቁን በማውገዝ ሰራዊታቸውን ይዘው ኤርትራ ከገቡት ከፍተኛ መኮንኖች አንዱ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አዲስ አበባ ገቡ።
ስርአቱን አውግዘው በተመሳሳይ ከሃገር የወጡት የኦሕዴድ መስራች አቶ ዮናታን ዲቢሳም በተመሳሳይ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተሰምቷል።
ስርአቱን ተቃውመው ከሃገር የወጡትና በትግል ላይ የቆዩት ኮለኔል አበበ ገረሱና አቶ ዮናታን ዲቢሳ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ነው።
በግብጽ ካይሮ የነበሩት ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በአንድ አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
የኦሕዴድ መስራች የነበሩት አቶ ዮናታን ዲቢሳ በኢትዮጵያ በሕወሃት የበላይነት በሀገሪቱ ውስጥ የማይፈጸመውን ግፍና ጭቆና በመቃወም በተለይም በኦሮሞ ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥቃት በማውገዝ ስርአቱን ጥለው ከተሰደዱ ወደ 20 አመታት አስቆጥረዋል።

በኢትዮጵያ የገንዘብ እጥረት የኢኮኖሚ ቀውስ እያስከተለ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4 /2010)የገንዘብ እጥረት ቀውስ የኢኮኖሚ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ገለጸ።
የ2011 በጀትም 59 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዳለበት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ገልጸዋል።
የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የገንዘብ እጥረት ቀውስ እንደገጠመው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ገልጿል።
እጥረቱ በፍጥነት መፍትሔ ካልተገኘለት ኢኮኖሚውን በመጉዳት ማህበራዊ ችግር ሊፈጥር እንደሚችልም ነው የተገለጸው፡፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶር አብርሃም ተከስተ የ2011 ረቂቅ በጀትን ሐሙስ ግንቦት 30 / 2010 ለፓርላማ አቅርበዋል።
በተለይም ከ2008 ጀምሮ ግን የገንዘብ እጥረቱ ጎልቶ በመውጣት ወደ ኢኮኖሚ ቀውስነት የመሸጋገር አዝማሚያ እየታየበት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ጣሊያን ስደተኞችን አገደች

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4/2010) ጣሊያን በባህር ድንበሯ ተሻግረው ሊገቡ የነበሩ ስደተኞችን አገደች።
አዲሱ የጣሊያን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር እገዳውን ያስተላለፉት በነፍስ አድን ሰራተኞች ከባሕር ላይ ሕይወታቸው ተርፎ ወደ ጣሊያን ሊገቡ የነበሩ 629 ስደተኞችን ነው።
ከሊቢያ አቅራቢያ ከተለያዩ ጀልባዎች በነብስ አድን ሰራተኞች ድጋፍ ከአደጋ የተረፉትን 629 ስደተኞች ነው የጣሊያን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደማይቀበል ያስታወቀው።
ስደተኞቹ ከ6 የተለያዩ ጀልባዎች በጀርመን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ርብርብ የተረፉ መሆናቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።
ነገር ግን ጣሊያን በሩዋን በመዝጋቷ ሳቢያ ሜዲትራኒያን ባህር ላይ በጀልባቸው ውስጥ ሆነው መጪውን ጊዜ መጠባበቅ ግድ ብሏቸዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤትና የአውሮፓ ህብረት በጋራ በጣሊያንና ሊቢያ መካከል እየደረሰ ስላለው የሰብአዊ ቀውስ አፋጣኝ መፍትሄ ለመፈለግ ጥሪ ማድረጋቸው ታውቋል።