
ማዕረግ የኮሚኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የኤሌክትሮኒክስ መልዕክት ሳጥናቸው ጋር በተያያዘ መበርበሪያ/ብራውዘር/ የሚያደርጉት የድረ ገጽ አሰሳም የቴክኖሎጂ እውቀታቸውንም ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል። በተለያዩ የአለም ክፍሎች በሚያደርጉት ጉዞ የዝሙት አዳሪዎችን አድራሻ በቋሚነት የማሰስ ተግባራቸውም ይበልጥ ትኩረትን የሳበ ሆኖ ተገኝቷል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሚያዚያ 24/2012 በካይሮ በተካሄደው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድርቅን መሰል አደጋዎችን ለመከላከል ያለውን ሚና የዘረዘሩ ቢሆንም በዕለቱ ኮምፒዩተራቸውን ከፍተው ከመረጃ ባህር ሲበረብሩ የነበሩት በካይሮ የሚገኙ በዝሙት የሚተዳደሩ ሴቶችን የሚያገናኙ ድረገጾችን እንደነበር ከተሰበረው የመልዕክት ሳጥናቸው የተገኘው መረጃ አጋልጧል። በቅርቡ የዛሬ ስድስት ወር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም 26/2017 አለም አቀፉ የቴሌኮሚኒኬሽን ዩኒየን ባዘጋጀውና በደቡብ ኮሪያ ቡሳን በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገኙት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በቆይታቸው በኢንተርኔት ሲበረብሩት የነበሩት በቡሳንና በርዕሰ መዲናዋ ሴኡል የሚገኙ በዝሙት የሚተዳደሩ ሴቶችን የሚያገናኙ ድረገጾችን እንደነበርም በሰነዱ ላይ በዝርዝር ተመልክቷል። ለመንግስታዊ ስራና ሃላፊነት በተለያዩ የአለም ክፍሎች ሲጓዙ ከሄዱበት መንግስታዊ ሃላፊነት ይልቅ የየከተሞቹን የሴተኛ አዳሪዎችን አድራሻ ሲበረብሩ የሚያጋልጠው ሰነድ በቀንና በሰአት በዝርዝር ተቀምጧል። ከግብጽ ካይሮ እንዲሁም ከደቡብ ኮሪያ ቡሳን ባሻገር በካሜሮን ያውንዴ፣በታይላንድ ባንኮክ፣በጃፓን ሄሮሽማና ቶኪዮ፣በሕንድ ሙምባይ፣በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ዱባይ፣በአሜሪካ ላስቬጋስ ከተሞች ለመንግስታዊ ስራ በተጓዙበት ወቅት የዝሙት አደር ሴቶችን አድራሻ ሲበረብሩና አገናኝ ድረገጾችን ሲያስሱ እንደነበርም ይፋ ሆኗል።
No comments:
Post a Comment