Wednesday, January 31, 2018

የፓርላማ አባላት ኮንትሮባንዲስት እየተባሉ የሚጠሩት ሰዎች ስም እንዲገለጽ ጠየቁ

 ጥር 22 ቀን 2010 ዓም የግማሽ አመት ሪፖርታቸውን ለፓርላማ ያቀረቡት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሞገስ ባልቻ፣ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎችን መቆጣጠር ካልቻለ፣ ትልቅ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስ እንደሚፈጠር አስጠንቅቀዋል። የፓርላማ አባላቱም እነዚህ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ስማቸው እንዲገለጽላቸው ለባለስልጣኑ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ባለስልጣኑ ግን መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ሪፖርተር እንደዘገበው አንድ የፓርላማ አባል ስሙ የማይጠራው ኮንትሮባንዲስት ማነው?” ሲሉ ሌላው የፓርላማ አባል ደግሞ ገቢዎችና ጉሙሩክ በእነዚህ ሃይሎች ጡንቻ መታሰሩን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት አንድ ብሔር ነጥሎ የማጥቃት ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ናቸው የተባሉት ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች መሆናቸውን በመጥቀስ የተናገሩት የፓርላማ አባሉ፣ የውጭ ንግድ በሚካሄድባቸው መስመሮች ድንገት መብራት ከጠፋ፣ ኮንትሮባንድ የጫኑ መኪኖች እያለፉ መሆኑ በገሃድ ይታወቃል ብለዋል።
የበላስልጣኑ የህግ ማስከበር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ዘመድ ተፈራ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎችን ስም ከመግለጽ የሚወሰደውን እርምጃ መጠበቅ የተሻለ ነው ብለዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ለተቋቋመው ግብረ ኃይል የኮንትሮባንዲስቶችን ስም ዝርዝር ማቅረባቸውንም ጠቅሰዋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮንትሮባንዲስቶቹ የራሳቸው መጋዘን ያላቸው፣ በኔትወርክ የተደራጁና ተግባራቸውም በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ነው ብለዋል።

No comments:

Post a Comment