
በማጋለጥ በሳል የሆኑ ጽሁፎችን በተከታታይ በማውጣትም ብዙ አድናቂዎችንና ተከታዮችን አፍርቷል። በተለይም አዲስ ጉዳይ የተሰኘው ሳምንታዊ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ በመሆን መስራቱ ከአገዛዙ ተደጋጋሚ ወከባ እንዲደርስበት አድርጓል። አዲስ ጉዳይ በህወሀት አገዛዝ በደረሰበት ጫና ሲዘጋ ጋዜጠኛ ኢብራሂምም የመታሰር አደጋ ውስጥ መግባቱን የቅርብ ጓደኞቹ ይገልጻሉ። በ2014 እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር ወደኬኒያ የተሰደደው ጋዜጠኛ በስደት ህይወቱም በተለይ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ በሸዋሮቢት በደረሰበት ድብደባ ምክንያት የገጠመው ጉዳት በስደት እያለ ወደጽኑ ህመም ተቅይሮ በመጨረሻም ለህልፈት አብቅቶታል። የጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ የቀብር ስነስርዓት በሀገር ቤት እንደሚፈጸምም ለማወቅ ተችሏል። በሌላ በኩል አንጋፋው የህክምና ባለሙያ ፕሮፌሰር ዕደማርያም ጸጋ ተሻለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በአውሮፓ፣በሰሜን አሜሪካና በኢትዮጵያ በከፍተኛ የህክምና ተቋማት በማስተማርና በምርምር ስራዎች በርካታ ተግባራትን በማከናወን የሚታወቁት ፕሮፌሰር ዕደማርያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ፋኪሊቲ ለ23 ዓመታት ማገልገላቸውን ከህይወት ታሪካቸው ለመረዳት ተችሏል። በካናዳ፣ በለንደንና በስዊዲን ተከታታይ የህክምና ትምህርታቸውን በመከታተል ለከፍተኛ ማዕረግ እንደበቁም የታሪክ ማህደራቸው ላይ ተጠቅሷል። በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የመጀመሪያውን የኢንዶስኮፒ አገልግሎትም በማቋቋም የሚታወቁ ናቸው። በ1927 በጎንደር የተወለዱት ፕሮፌሰር ዕደማርያም ጸጋ ተሻለ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፕሮፌሰር ዕደማርያም ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ነበሩ።
No comments:
Post a Comment