ፋይል ነባሮቹን መንደሮች ለማፍረስ ደግሞ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ታውቋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲህ አይነቱ ስትራቴጂ የሕወሃት አገዛዝ አብሮ የኖረውን ሕዝብ በመበታተን ራሱ የሚፈልጋቸውን ሰዎች ለማስፈር በየጊዜው የሚነድፈው እኩይ እቅድ ነው ሲሉ እቅዱን አውግዘዋል። ሕብረተሰቡም እንዲህ አይነቱን እኩይ ተግባር በጋራ በመሆን ማስቆም ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በቅርቡ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዶባቸው ይፈርሳሉ የተባሉት ቤቶች 78 ሔክታር መሬት ላይ ያረፉ ናቸው ተብሏል። የከተማዋ የመሬት ልማትና ማደስ ኤጀንሲ እንደሚለው ከሆነ እነዚህ ቤቶች ሲፈርሱ የተነሺዎችን መብት ባስከበረ መልኩ ነው። ይህን የማፍረስ ስነስርአት ለማካሄድም ኤጀንሲው ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል ሲል ሪፖርተር በዘገባው አስፍሯል።–ቀጣዩ ስራ ከነዋሪዎች ጋር መወያየት መሆኑን በመጠቆምም ጭምር በ2010 ሁለተኛው ግማሽ አመት ላይ ለመፍረስ እቅድ የተያዘላቸው አካባቢዎችም በአራዳ ክፍለ ከተማ አሜሪካ ግቢ ቁጥር ሁለትና ገዳም ሠፈር፣ በየካ ክፍለ ከተማ ከሾላ እስከ መገናኛ ድረስ፣ በልደታ ክፍለ ከተማ ጌጃ
ሠፈር፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ ቁጥር ሦስት ቶታል ነዳጅ ማደያ አካባቢ ያሉ መንደሮች ናቸው፡፡ እቅዱ በሌላ በኩልም ከቦታው የሚፈናቀሉ ተነሺዎችን የካሳ መጠን ከመቼው ጊዜ በበለጠ ተመጣጣኝ እንዲሆን አደርጋለሁ።–ተነሺዎቹ አቅም ካላቸው ብሎም ቦታቸው በማስተር ፕላኑ ለሌላ አገልግሎት የማይፈለግ ከሆነ በዛው በአካባቢያቸው እንዲያለሙ እድሉ ይሰጣቸዋል ይላል። ኤጀንሲው ሌላ የያዘው እቅድ ደግሞ ከዚህ በፊት ይነሳሉ ተብለው በይገባኛልና በፍርድ ቤት ዕግድ ምክንያት ሊነሱ ያልቻሉ ቤቶች መልሶ ማልማቱን በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማካሄድ እንቅፋት መሆናቸውን ይገልጻል። ስለሆነም የፍትሕ ሒደቱን የተፋጠነ ለማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ አማካኝነት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራዎች ተጀምረዋል ብለዋል፡፡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ ይሄ የሕወሃት አገዛዝ ስትራቴጂ በየጊዜው ተሳስቦና ተከባብሮ የሚኖረውን ሕዝብ ለመነጣጠል የሚነድፈው እኩይ እቅድ ነው። በተደጋጋሚም በመልሶ ማልማት ሰበብ ደሃውን ሕዝብ ከሚኖርበት ቀዬ እያፈናቀለና ቦታቸውን ለራሱ ደጋፊዎችና ባለሃብቶች ሲያከፋፍል ቆይቷል። አሁንም ቀጣዩ እቅድ ነባር የከተማዋን ነዋሪ ከከተማዋ ማራቅና ከተማዋን በራሱ ደጋፊዎችና ባላሃብቶች እንድትሞላ ማድረግ ነው ይላሉ። ይህንን እኩይ እቅዱን ለማፍረስ ሁሉም በጋራ ሊነሳ ይገባል ሱሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በፍርድ ቤት ይግባኝ የተጠየቀባቸው ቤቶች ላይም እዘምታለሁ ያለው የሃገሪቱ ይፍትህ ስርአት በማንኛውም ጊዜና በማንኛውም አካል እደፈለገ የሚቀየር መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉም ያክላሉ። እናም ነዋሪው በሚሰነዘርለት የመደለያ ቃል ሳይዘናጋ የአገዛዙን የመነጣጠልና የዘረፋ እቅድ እንዲያከሽፍ ጥሪ አቅርበዋል።

No comments:
Post a Comment