
አገዛዝ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መሰል የእርስ በእርስ ግጭት መለኮሱን በመቀጠል በቡኖ በደሌ ዞን ሁለት ወረዳዎች ሰሞኑንም የማፈናቀል ርምጃ እንዲወሰድ አድርጓል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በህወሃት አገዛዝ ስውር ተልዕኮ የተሰጣቸው አንዳንድ የአካባቢው የመንግስት ሹመኞች በተለይ የአማራ ተወላጅ በሆኑ ነዋሪዎች ላይ ስልታዊ የማፈናቀል ርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው። በገቺና ዲዴሳ ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ንብረታቸውን ሸጠው ከአካባቢው እንዲለቁ ስውር በሆነ ስልት ዘመቻ መከፈቱን ለማወቅ ተችሏል። የአማራና የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን በህወሃት አገዛዝ የተቀነባበረውን ሴራ እያመከኑ፣ አንድነታቸውን ይበልጥ እያጠናከሩ መሆናቸው ያላስደሰተው አገዛዙ ከዚህም የከፋ የተንኮል ርምጃ ሊወሰድ ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከአካባቢው ለኢሳት በደረሰው መረጃ ላይ ተመልክቷል። በሌላ በኩል ዛሬ ጠዋት በምዕራብ ሀረርጌ ዳሮ ለቡ ወረዳ የሶማሌ ልዩ ሃይል ከአጋዚ ሰራዊት ጋር በመሆን ህብረተሰቡን እያሸበሩት መሆኑን ከስፍራው ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ የነዋሪውን እንቅስቃሴ በመገደብ የስነልቦና ሽብር የፈጠሩት የልዩ ሃይሉና የአጋዚ ሰራዊት አባላት በአንዳንዶቹ ላይ ድብደባ መፈጸማቸውም ታውቋል። ህዝቡ የአጸፋ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን የከፋ አደጋ ሊፈጸም እንደሚችልም ተገልጿል። ከቅትር በኋላ ስላለው ሁኔታ ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ኦፌኮ አንድ የወረዳ የአመራር አባሉ መገደሉን አስታውቋል። በቄለም ወለጋ የፓርቲው የምርጫ ተወዳዳሪ የነበሩትና የሁለት ልጆች አባት አቶ ተመስጌን ሳፎ ተገድለው መገኘታቸውን የጠቀሰው ኦፌኮ የግድያውን ሁኔታ እያጣራሁ ነው ብሏል። በርካታ አባላቱ ከስራ እንደሚፈናቀሉበትም አስታውቋል። ፓርቲው በቅርቡ እንደገለጸውም አባላቱ የትምህርትና የስራ እድል ይነፈጋሉ። ብድርና እርዳታ እንዳያገኙም ይደረጋል።
No comments:
Post a Comment